“Our true nationality is mankind.”H.G.

የኦዲት ግኝቶች አይድበስበሱ

ርዕሰ አንቀፅ

ወዲህ ወደ አዲስ አበባ ሲመጣም የከተማ አስተዳደሩ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ይፋ ባደረገው የ2009 በጀት አመት ሪፖርት መሰረት በርካታ ግድፈቶች መገኘታቸው ታውቋል፡፡ እንደ ሪፖርቱ ከሆነ በ2010 በጀት አመት በአስራ አንድ ተቋማት በወቅቱ ያልተሰበሰበ የተሰብሳቢ ሂሳብ ብር 329 ሚሊዮን 677 ሺ 934.80፤ በሁለት ተቋማት ከማን እንደሚሰበሰብና የመቼ ሂሳብ እንደሆነ የማይታወቅ ሂሳብ ብር 3ሚሊዮን 959ሺ 339.19፤ በሶስት ተቋማት ብር 123ሚሊዮን 321ሺ 342.50 ለማን እንደሚከፈል የማይታወቅ የተከፋይ ሂሣብ፤ በዘጠኝ ተቋማት በወቅቱ ያልተከፈለ የተከፋይ ሂሳብ ብር 137ሚሊዮን 886ሺ 646.43፤ ኦዲት ከተደረጉ ተቋማት ውስጥ በሰባት ተቋማት ያለአግባብ ብር 112ሚሊዮን 277ሺ 277.85 ከግዥ ደንብና መመሪያ ውጭ ግዥ ተፈጽሞ መገኘቱ ተረጋግጧል::

ለአብነት የአንድ ክልልና የአንድ ከተማ አስተዳደር አመታዊ የኦዲት ሪፖርት ቀረበ እንጂ፤ በሌሎች ክልሎችም ሆነ የከተማ አስተዳደሮች ተመሳሳይ ግድፈቶች እንደሚፈጸሙ እሙን ነው፡፡ ሪፖርቶቹ የአንድ አመት ቢሆኑም በየአመቱ በሚቀርቡ ሪፖርቶች ተመሳሳይ ግድፈቶች መታየታቸው ፤ መታረም ሲገባቸውም ለውጥ አለማሳየታቸው እጅግ አሳሳቢ አገራዊ አደጋ ያስከትላል፡፡
የኦዲት ሪፖርቶች በየአመቱ እየፈተሹ የሚያወጧቸውን ገመናዎች ተከታትሎ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ አለማድረግና ተጠያቂ የሚሆኑ አካላትን በመለየት ለፍትህ አለማቅረብ ሙስናን በማስፋፋት በአገሪቱ ለሚታዩት ቀውሶች አንድ ሰበብ መሆናቸው አይቀርም፡፡ በተለይ የፖለቲካ አመራሩን ተአማኒነት በማሳጣት ረገድ ለሚፈጠረው ክፍተት የራሳቸውን ሚና ይጫወታሉ፡፡
ከፍተኛ የህዝብና የመንግስት አደራ በመብላት የተጣለባቸውን ኃላፊነት ዘንግተው በቸልተኝነት ወይም ሆን ብለውም ይሁን ሳያውቁ መመሪያ የሚጥሱ፣ ለብክነት በር በሚከፍቱ አሰራሮች የተነሳ ከፍተኛ ገንዘብ የት እንደገባ የማያውቁ ኃላፊዎችና ፈጻሚዎች መበርከታቸው አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡ አንዳንዶቹ እንደ ርስት በሚቆጥሩት ቦታ ለዘወትር ተቀምጠው መገኘታቸው በመንግስት ላይ የሚኖረውን ተአማኒነት የሚሸረሽር ብሎም ህዝብን ለተቃውሞ የሚያነሳሳ ነውና የኦዲት ሪፖርቶችን ሰምቶ ማድበስበስና ተገቢውን እርምጃ አለመውሰድ አደጋው ከፍተኛ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡
በአንዳንድ የመንግስት ተቋማት አመራሩ በርካታ ጉድለት እየታየበት በአንድ ቦታ ‹‹ተረስቶ›› የመተዉ ጉዳይ እንዳለ ሆኖ፤ በሌሎች የመንግስት መስሪያ ቤቶች ደግሞ ጥፋት ያጠፉ እንዳይጠየቁ በሚመስል ሁኔታ ቶሎ ቶሎ መቀያየሩም የኦዲት ሪፖርቶች መክነው እንዲቀሩ መንገድ የሚያመቻች በመሆኑ ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ተቀይረው የሚመጡ አመራሮች ‹‹እኔ ስለ ጉዳዩ አላውቅም፤ ይህ የተደረገው በቀድሞው ኃላፊ ነው … ወዘተ›› የሚሉ ምክንያች እየደረደሩ በስንት ድካም የተሰሩ የኦዲት ግኝቶች ባለቤት አጥተው የሚቀሩበትን አጋጣሚ ይፈጥራሉና ተጠያቂነት የሰፈነበት ሰንሰለታዊ አሰራር መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡
የኦዲት ሪፖርቶች ተገቢው ትኩረት ተሰጥቷቸው ምላሽ ካላገኙ የሚፈጥሩት ኢኮኖሚያዊ ችግር አያሌ ነው፡፡ በጋምቤላ ክልልና በአዲስ አበባ መስተዳድር የተጠቀሱት ቁጥሮች ጋር በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች የሚፈፀሙትን ጉድለቶች ብንደምራቸው በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ለብክነት እንደሚጋለጥ መገመት አያዳግትም፡፡ ሪፖርቶቹ ምላሽ ሳያገኙ እየተድበሰበሱ የሚቀሩ ከሆነ ደግሞ ከደንብና መመሪያ ውጭ ግዥ መፈጸም፤ ከውል በላይ መክፈልና ሌሎችም ህገ ወጥ ተግባራት የተነሳ ኢኮኖሚዊ ፈተናው ተባብሶ መቀጠሉ አይቀርምና የሚመለከታቸው አካላት የቅንጅት ስራ ማከናወን አለባቸው፡፡
በአገሪቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ በብዛት ረገድ ለውጥ ቢያመጡም በጥራት እየተፈተኑ የሚገኙት የማህበራዊ አገልግሎቶቸ ችግሮች እንዲፈቱ የኦዲት ሪፖርቶቸን በአጽንኦት ተከታትሎ እርምጃ መውሰዱ አዋጭ ነው፡፡ ደረጃቸውን ያልጠበቁ የህክምናና የትምህርት ግብአት ግዢዎች እንዲሁም ግንባታዎችና አገልግሎቶችን በተመለከተ የፌዴራል፣ የከተማ አስተዳደሮችና የክልል ኦዲት መስሪያ ቤቶች በየጊዜው ሪፖርት ቢያወጡም ለውጦች በሚጠበቀው ደረጃ አለመታየታቸው አሁንም የአፈጻጸም ውስንነት ስለመኖሩ አመላካች ነው፡፡ ስለዚህ ሪፖርቶቹን ተከታትለው እርምጃ መውሰድና ማስወሰድ ያለባቸው አካላት ጠበቅ ያለ ክትትል ግድ ይላል፡፡
የኦዲት ሪፖርቶች ሰሚ አግኝተው አጥፊዎች እንዲቀጡ፣ ቸልተኞች እንዲታረሙና የመንግስትና የህዝብ ሀብት ከብክነት ለመታደግ እንዲቻል በዋናነት ኃላፊነት የተሰጣቸው የፌዴራል እና የክልል አቃቤ ህግ ቢሮዎችና ምክር ቤቶች ከመቼውም ጊዜ በላቀ መልኩ ኃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው፡፡ የኦዲት ሪፖርቶችን በመከታተል ተቋማትን መሞገት ዋና ስራቸው ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የኦዲት መስሪያ ቤቶችም ሪፖርቱን ከማዘጋጀትና ግብረ መልስ ከመስጠት የዘለለ ሚና ባይኖራቸውም ይህንኑ አጠናክረው መቀጠል ይገባቸዋል፡፡

Share and Enjoy !

0Shares
0
0Shares
0