እኔ የመጣሁት የአማራ እና የኦሮሞን ህዝብ ተፈጥሯዊ ትስስር ለማጠናከር ነው፡፡ኦሮሞ እና አማራ ለኢትዮጵያ ትልልቅ መሰረቶች ናቸው።›› ጃዋር ሙሃመድ  

የኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ እና አክቲቪስት ጀዋር ሙሃመድ በባሕር ዳር አቫንቲ ብሉ ናይል ሆቴል ተገኝቶ ከወጣቶችና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው፡፡

• በራሳችን መፋቀድ በዚህ ፍጥነት ተቀራርበን በመስራታችን መሰረት ለሆኑ ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች ታላቅ ምስጋና አለኝ።
• ለውጡን እውን ለማድረግ ተቀራርበን መስራት ይስፈልጋል። ለዚህም ነው ለለውጡ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከከፈሉ ህዝቦች ጋር ለመወያየት የመጣሁት ። 
• ባለፉት ዓመታት አማራ እና ኦሮሚያን ለመከፋፈል እሳት እና ጭድ ያቀበሉን ሙተንም ቢሆን አሁን የምንፈልገው ኢትዮጵያዊነት ላይ ደርሰናል።
• የሁለቱ ህዝቦች መቀራረብ እንደ አባት እና ልጅ ነው። ምሁራን እና አክቲቭስቶች ህዝቡን ለማቀራረብ መስራት የሚያስፍገን ጊዜ ነው።
የኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ እና አክቲቪስት ጀዋሪ ሙሃመድ በብሉ ናይል ሆቴል ውይይቱ ተሳታፊዎች ጥያቄ ማቅረብ ጀምረዋል።

‹‹ እኔ የመጣሁት የአማራ እና የኦሮሞን ህዝብ ተፈጥሯዊ ትስስር ለማጠናከር ነው፡፡ኦሮሞ እና አማራ ለኢትዮጵያ ትልልቅ መሰረቶች ናቸው።›› ጃዋር ሙሃመድ ›› 

ባሕር ዳር፡ነሀሴ 03/2010 ዓ.ም(አብመድ) የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ ጃዋር ሙሀመድ እና ሌሎች አክቲቪስቶች ባሕር ዳር ገቡ፡፡

በባሕር ዳር አውሮፕላን ማረፊያ የአማራ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ በአቀባበሉ የተገኙት የአማራ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ.ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ጥላሁን ‹‹ኦኤምኤን በአማራ ክልል ያለውን ልማትና ዴሞክራሲ ለማስፈንና ለውጡን ለማጠናከር አጋር ነው፤ከአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እና ከክልሉ ህዝብ ጋርም በጋራ ይሰራል›› ብለዋል፡፡

ጃዋር ሙሀመድ በአቀባበል ስነ-ሰርዓቱ እንደተናገረው በአሁኑ ወቅት ላለው ለውጥ የአማራ ህዝብና መንግስት ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ ‹‹የአማራ እና የኦሮሞን ህዝብ ተፈጥሯዊ ትስስር ለማጠናከር ነው የመጣሁት›› ነው ያለው አቶ ጃዋር፡፡ ‹‹የሁለቱን ህዝቦች ትስስር ለማጠናከር የምችለውን አደርጋለሁም›› ብሏል፡፡
አቶ ጃዋር ሙሀመድ ከአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ዘጋቢ፡- ግርማ ተጫነ

Amhara Mass Media Agency

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ወርቃማ ድል የተጎናጸፍነው ትልቁን ስዕል ማየት የሚችሉ ፣ ችግሮቻቸውን የመፍታት ልምድ ያላቸው እናትና አባቶች ስላሉን ነው – ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *