የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ከዛሬ ጀምሮ የተናጠል የተኩስ አቁም ማድረጉን አስታወቀ። በሶማሊ ክልል የአብዲ ኢሌ ታታቂዎችና እሱ ያደራጃቸው ሃይሎች በንጹሃን ላይ የፈጸሙትን ወንጀል ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊት ባደረገው እንቅሳቃሴ የኦብነግ ታጣቂዎች እንደሆኑ የተነገረላቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ዘብጥያ የወረደው የሶማሌ ክልል መሪና አበሮቹ የተፈጠረውን ቀውስ ተንተርሰው ሲንቀሳቀሱ የነብሩ ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት በስማሌ የሰላም ማስከበር ላይ ያሉ የአገር መከላከያ ሰራዊት ወደ ድንበር እንዲመለሱ መታዘዙን ተከትሎ እንደሆነ ከተላያዩ መረጃዎች ለማረጋገጥ ተችሏል።

ONLF

ሰፊ ሕዝባዊ ቁጣ ያስነሳውና በሰብአዊ መብት ረገጣ፣ በዘር ማጥፋትና በከፋ ሙስና ከነግብረ አበሮቹ ክስ የሚመሰረትበት አብዲ ኢሌ ላይ እርምጃ መወሰዱን በመቃወም ኦብነግ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። ይህንኑ መግለጫ አንድ የግንባሩ ስንጣሪ የሆነ ክንፍ እንዳወጣው መገለጹን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት በድርድር ላይ እንዳለ መረጃዎች ተሰምተው ነበር።

ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር ግንባር የፈጠረው ኦብነግ ይሁን ሌላ ባይታወቅም አሁን የተሻለ ሃይል አለው የሚባለው ክፍል የተኩስ አቁም ማወጁን በኦፊሳል አስታውቋል። አዲሱ የዶክተር አብይ አስተዳደር ከየትኛውም ዓይነት አፈብጋጭና ተቀናቃኝ ሃይል ጋር ለመደራደር በያዘው አቋም የተነሳ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መነግስትን በተለያዩ ደረጃ የሚቀናቀኑ ወደ አገር ቤት ገብተዋል። ለመግባትም ቀጠሮ ይዘዋል።

ኦብነግ ዛሬው ባወጣው መግለጫው ያወጀው የተናጥል ተኩስ ማቆም ውሳኔ ነው።ውሳኔ ላይም የደረሰው የኢፌዴ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባቀረቡት ጥሪ መነሻ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። በኦጋዴን ያለውን ማናቸውን ዓይነት ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ ለመጨረስ ከመንግስት ጋር የጀመረውን እንቀሳቃሴ እንደሚቀበልም ግናብሩ ይፋ አድርጓል። 

በዚሁ መነሻ ግንባሩ ማናቸውንም ዓይነት ወታደራዊ ጥቃትም ሆነ የማስተጓጎያ እርምጃ ሙሉ በሙሉ ማቆሙን አውጇል። በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የሚመራው መንግስትም የተጀመረው የሰላማዊ ንግግር በሚፈለገው መልኩ እስኪጠናቀቅ ድረስ በተመሳሳይ ከማናቸውን አይነት እርምጃዎች እንዲቆጠቡ ጠይቋል።

ይህ በንዲህ እያለ አቶ አህመድ ሽዴ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢሶህዴፓ/ ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸውን የመንግስት መገናኛዎች አመልክተዋል። አቶ አህመድ የተመረጡት ድርጅቱ ላለፉት ሶስት ቀናት ያደረገውን ጥልቅ ግምገማ ተከትሎ ነው። የተመረጡትም በሙሉ ድምጽ ነው።

አቶ አህመድ ሽዴ የኢሶህዴፓ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ

ውሳኔው አቶ አህመድ ቀጣይ የክልሉ ሊቀመንበር ይሆናሉ የሚለውን ግምት አጉልቶታል። አብዲ ኢሌን የተኩት አዲሱ የክልሉ መሪ ቀደም ሲል ከገንዘብና ከኢኮኖሚ ጉዳዮች ጋር ካነበራቸው ሃላፊነት ጋር ተያይዞ በበርካታ ጉዳይ የሚጠረጠሩ፣ ገጭቱን በቪዲዮ ያስተባበሩ፣ ከፈተኛ የሆነ ሃብት ያከማቹ፣ መንግስት ለባለስልጣናት ያሰራው ቤት አይመጥነኝም በሚል ከስድስት መቶ ሺህ ብር በላይ በማውጣት ማሻሻያ ያደረጉ፣ በልምድም ሆነ በአመራር ደረጃ ብስለት የሌላቸው፣ አብዴ ኢሌ በጭነት መኪና ብር ጭኖ ሲያድል አርፈው ሂሳብ የሚያወራርዱ፣ እንዲሁም በተለያዩ የሰብአዊ መብት ጉዳይ የሚከሰሱ መሆናቸውን በቅርብ መረጃ ያላቸው እየገለጹ ባለበት ሁኔታ ይህ መሆኑ የአቶ አህመድን ወደ መሪነት መምጣጥ ያመላክታል።

ምስል የኦብነግ ሰራዊት

 

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *