ሰኔ 16 ቦምብ በማፈንዳት ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የዋለው ጥላሁን ጌታቸው የተባለው ግለሰብ ክስ ሊመሰረትበት መሆኑ ታውቋል። በፖሊስ የምርመራ መዝገብ እንደተመለክተው ግለሰቡ ቦምቡን ሲያፈነዳ ትከሻው ላይ ጉዳት ደርሶበታል።

ቦምቡን በማፈንዳት የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በተሽከርካሪ ጭኖ ወስዷል ፣እንዲሁም ቦምቡን ላፈነዳው ሰው የማቀበል ድርጊት ፈፅሟል በሚል የተጠረጠረው ብርሃኑ ጃፋርም ክስ ይመሰረትበታል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የምርመራ ቡድን በተጠርጣሪዎች ላይ ሲያካሂድ የነበረውን ምርመራ አጠናቆ ለአቃቢ ህግ አስረክቧል።አቃቢ ህግ  የ15 ቀን ክስ የመመስረቻ ጊዜ ቢጠይቅም፣ ፍርድ ቤቱ የሰባት ቀን የጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል።

Related stories   አፍሪካ ህብረት ቁርጠኛነቱን አሳይቷል፤ አውሮፓ ህብረት ምርጫ አልታዘብም አለ

ተጠርጣሪዎቹ  የዋስትና መብታቸው እንዲሰጣቸው የጠየቁ ሲሆን ግራ ቀኙን የመረመረው ችሎቱ የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ ክስ ለመመስረቻ ለዓቃቢ ህግ ሰባት ቀን ፈቅዷል።

በተመሳሳይ ከትናንት ወደ ዛሬ በተሸጋገረው ችሎት  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ላስመዘገቧቸው ለውጦች በተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ላይ በመስቀል አደባባይ በደረሰው የቦንብ ፍንዳታ የአሰራር ክፍተት አሳይተዋል ተብለው በሚል ምርምራ እየተካሄደባቸው የነበረው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ ዋስትና ተፈቀደላቸው።

Related stories   እንግሊዝ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እቅዷን ይፋ አደረገች፤ ዶክተር ዳንኤል የማይካድራን ጂኖሳይድ ዝም ማለቱ ክህደት ነው

አቃቤ ህግ ምክትል ኮሚሽነሩን ጨምሮ ሌሎች 11 የፖሊስ አመራሮችም በዋስ ቢለቀቁ እንደማይቃወም ትናንት ማስታወቁ ይታወሳል። የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎትም ዛሬ ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ በ15 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፈቅዷል።

ኮማንደር ገብረኪዳን አስገዶም፣ ኮማንደር ገብረስላሴ ታፈረ፣ ኮማንደር ግርማይ በርሄና ኮማንደር አንተነህ ዘላለምን ጨምሮ ሌሎች የአሰራር ክፍተት አሳይተዋል ተብለው የነበሩ ግለሰቦች ከ6 ሺህ ብር እስከ 9 ሺህ ብር በሚደርስ ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ ፈቅዷል። በዚህም የዋስትና ጉዳይን የሚመለከተው መዝገብ መዘጋቱን ነው ፍርድ ቤቱ ማስታወቁን ፋና ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *