“Our true nationality is mankind.”H.G.

ጸረ-ሽብር ህጉና በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት የማሻሻያ ግብዐት ሊሰበሰብ ነው ተባለ።

በጸረ ሽብር ህጉና በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ህጎች የተመለከተ የማሻሻያ ግብዐት ለመሰብሰብ ዝግጅት መደረጉን ጠቅላይ አቃቢ ህግ አስታወቀ።


ይህንን በማስመለከት ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷአል። በቅርቡ የማሻሻያ ሀሳብ ለማድረግ በተጀመረው እንቅስቃሴ መሰረት በጸረ ሽብር ህጉና በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ረቂቅ አዋጅ ላይ ከህብረተሰቡ ግብዐት ለማሰባሰበ ፕሮግራሙ ዛሬ ይፋ ሆኗል።
በመሆኑም ከነሀሴ 25 እስከ መስከረም 10/2011 የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራትን የተመለከተ ግብዐት የሚሰበሰብ ሲሆን ከመስከረም 7 እስከ 14/2011 ደግሞ የጸረ-ሽብር ህጉን አስመልክቶ ግብዐት ይሰበሰብበታል በማለት ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫው ሲሰጥ ተገልጿል።
በጠቅላይ አቃቢ ህግ የጸረ ሽብር ህጉ አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በመግለጫው እንደገለጹት ከዚህ በፊት የነበረው በዋናነት የመደራጀት፣ ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብትን፣ የመሰብሰብና የመደራጀት መብቶችን በአለማቀፍ ህጎችና በህገ መንግስት ያሉትን መብቶች የሚጥሱ አዝማሚያ እንደነበረው በይዘቱም በአተገባበሩም በጥናት ተለይቷል ብለዋል።
በጠቅላይ አቃቢ ህጉ የሚመራ የፍትህ ማሻሻያ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ግብዐት በሚሰበሰብበት መድረክ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የግብአት ሀሳብ በመስጠት መሳተፍ ይችላል ያሉት ዶ/ር ጌዲዮን በመድረኩ ለመሳተፍ እድል ያላገኙ አካላትም ካሉ ሀሳባቸውን በኢሜልና በኤሌክተሮኒክስ አማካኝነት ሀሳባቸውን መላክ እንደሚችሉም አሳስበዋል።
በጉባኤው ላይ ህግን የሚመለከተው አስተባባሪና የህግ ባለሞያ የሆኑት አቶ ደበበ ኃገብርኤል በበኩላቸው በሀገሪቱ በእነዚህ አዋጆች የህግ ረቂቅ ዙሪያ የመልካም እሰተዳደር ችግር ሲፈጥሩ እንደነበር በጥናት በመረጋገጡ በሚሻሻለው አዋጅ መሰል ችግሮች ይፈታሉም በማለት አሳስበዋል።
ጉባኤው ላይ የተለያዩ መንግስታዊ አካላት፣ ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች የሚገኙ ሲሆን ሚዲያዎች ደግሞ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ በኩል ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል በማለት በጠቅላይ አቃቢ ህግ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ታየ ደንዳአ አሳስበዋል ።
የጸረሽብርተኝነት አዋጁ ላይ የግብዐት ሀሳብ ለመላክ atp.ljaac@gmail.com መጠቀም የሚቻል ሲሆን የበጎ አድራጎትና ማህበራት ድርጅቶች csp.ljaac@gmail.com መጠቀም ይችላሉ።
ነሀሴ፣ 23/2010 (መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት)

ምስል ፋና

0Shares
0