በቀጣይ አመት መታወቂያ ለነዋሪዎች የሚሰጥበት መንገድ ማሻሻያ እንደሚደረግበት የከተማ አስተዳደሩ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ አስታወቀ።

ዋና ዳይሬክተር አቶ አስናቀ ተሾመ፥ በተለይ መታወቂያው በአሻራ የተደገፈ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን ነው ያስታወቁት፡፡

ከዚህ ባለፈ በመታወቂያዎች ላይ የነበሩ አንዳንድ ነጥቦች ማሻሻያ ተደርጎባቸው እንደሚወገዱ ዳይሬክተሩ መግለፃቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።

በሁሉም ክፍለ ከተሞች የመታወቂያ  አገልግሎት እንደሚሰጥ የተነገረ ሲሆን፥ ከፋይናንስ ተቋማትና ከሌሎች መስርያ ቤቶች ጋር በዲጂታል ስርዓት ትስስር እንደሚኖረው አመልክተዋል፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   የዓለም ጤና ድርጅት ለቻይናው ክትባት ይሁንታውን ሰጠ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *