የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባን ጨምሮ 100 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ። የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት የተከሳሾቹን የክስ ሂደት እየተመለከተ ይገኛል።

ግለሰቦቹ በሃዋሳ ከተማና አካባቢዋ በአንዳንድ የሲዳማና የወላይታ ብሄረሰብ መካከል ግጭት እንዲፈጠር በማድረግ፥ የበርካታ ሰወች ህይወት እንዲጠፋና ዜጎች እንዲፈናቀሉ በማድረግ እጃቸው አለበት በሚል የተጠረጠሩ ናቸው።

የፌደራል አቃቤ ህግም ክሱን በሁለት መዝገብ ያቀረበው ሲሆን፥ ጉዳያቸውም በሃዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፌደራል ተዘዋዋሪ ችሎት እየታየ ይገኛል።

በዛሬው እለት ችሎት ከቀረቡት መካከል የሃዋሳ ከተማ ማረሚያ ቤት ሃላፊን ጨምሮ ስድስት የማረሚያ ቤቱ ሰራተኞች ይገኙበታል።

ችሎቱም በማረሚያ ቤት ውስጥና በሃዋሳ ከተማ እና አካባቢዋ ለረጅም አመት በአብሮነት የኖሩትን የሲዳማነ ወላይታ ብሄረሰብን በማጋጨት ለሰው ህይወት መጥፋትና ለንብረት መውደም እጃቸው አለበት የተባሉ ተጠርጣሪዎች ጉዳይ እየተመለከተ ይገኛል።

FBC

Related stories   " የህግ የበላይነት ከሌለ ዘመናዊ መንግሥት አይገነባም"

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *