የሰብአዊ መብት ተሟጋች ፣አክቲቪስት እና አርቲስት ታማኝ በየነ ዛሬ ምሽት በአቫንቲ ብሉናይ ሪዞርትና ሰፓ በተካሄደው የእራት ግብዣ የባሕር ዳር ነዋሪዎች  150 ግራም ወርቅ አበርክተውለታል፡፡


የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማህበር ደግሞ በስሙ የተሰራ ጭራ አበርክተውለታል፡፡ለባለቤቱ ወ/ሮ ፋንትሽ በቀለ የአካባቢውን የሚገልጽ የባህል ልብስ ተበርክቶላታል፡፡ 

‹‹የበደሉ ሁሉ ኢትዮጵያውያንን ይቅር የሚሉበት ስርዓት መፈጠር አለበት ››የሰብአዊ መብት ተሟጋች፣አክቲቪስት እና አርቲስት ታማኝ በየነ
‹‹አርቲስት ታማኝ በየነ ከአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ጋር ባደረገው ቆይታ የወዲፊቷ ኢትዮጵያ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ እጅ ናት፡፡ለዚህ ደግሞ ወጣቶች ከአሁን በፊት የነበረውን መቃቃር ወደ ጎን ትተው በህግ ብቻ መዳኘት አለባቸው፡፡የበደሉ ሁሉ ኢትዮጵያውያንን ይቅር የሚሉበት ስርዓት መፈጠር አለበት›› 
‹‹የቡድን ፖለቲካ ሳይሆን ሁላችንንም ተጠቃሚ ሊያደርግ የዜግነት ፖለቲካ ተግባራዊ መደረግ አለበት፡፡ ለአንዳችን ብቻ ሳይሆን መላውን ዜጋ የሚያስተዳድር ህግ መተግበር አለበት፡፡ በተረቀቀልን ሳይሆን ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል አሳታፊ ያደረገ ህገ-መንግስት መረቀቅ አለበት፡፡››
ባሕር ዳር፡-ነሀሴ 28/2010 ዓ.ም(አብመድ)

Related stories   የእምብርት ዘመን ሲሄድ የቂጥ ዘመን መጣ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *