የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ለዜና ማጠናቀሪያ የሚጠቀምበትን ቢሮ በስድት ቀን ወስጥ አስረክቦ እንዲወጣ የትግራይ ማስ ሚዲያ ኤጀንሲ አሳሰበ። በተባለው ጊዜ ውስጥ የማያስረክቡ ከሆነ እርምጃ እንደሚወስድ ኤጀንሲው የጻፈው ደብዳቤ አመልክቷል። ውሳኔ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሚያቀርባቸው ያልተለመዱ ዘገባዎች በህወሃት ደረጃ ከፈጠረው ስሜት አንጻር የሚወሰድ እርምጃ እንደሆነ ተሰምቷል።

tigray mass media.png

መስከረም 4ቀን 2011 ዓ.ም በቁጥር 668/ ኤ5/ጠ- 31 ኤጀንሲው በላከው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ኮርፖሬሽኑ ዜና የሚያጠናቅርበትን ቢሮ እስከ መስከረም 10/2011 ለቆ ካልወጣ ግህ በሚፈቅደው አስፈላጊው ሁሉ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል። ስለሚወስደው ህጋዊ የተባለ እርምጃ ግን ያለው ነገር የለም።

Related stories   መንግሥት ቢቢሲና ሮይተርስን ጨምሮ ሰባት ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ትግራይ ክልል ገብተው እንዲዘግቡ ተፈቀደ

ቀደም ሲል በ10/1/2011 ተመሳሳይ የለቃችሁ ውጡ ማሳሰቢያ መላኩን ያስታወሰው ደብዳቤ ሁለት ቢሮዎችና አንድ የሰራተኞች ማረፊያ ያለክፍያ መስጠቱን ያስረዳል። ከመቼ ጀምሮና ለስንት ዓመት ቢሮውን በውሰት እንደሰጠ ያላመለከተው ደብዳቤ፣ ቢሮው ለመረከብ ምክንያት ያደረገው ” ሰራተኞቻችን ቢሮ አጥተው እየተቸገሩ ስለሆነ” የሚል ነው።

ደብዳቤውን በማህበራዊ ሚዲያ ገጹ ያሰራጨው ዳንኤል ብርሃኔ ከደብዳቤው በላይ ” ውሸታሙ ኢቲቪ ቢሮህን ለቀህ ውልቅ በል ተብሏል…ገና ከትግራይ ይወጣል ብራቮ ብራቮ …እንደዚ ቆፍጠን ያለ እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠል ኣለበት..” የሚለውን አስተያየትም አትሟል። ከስሩም በርካታ አስተያየት የተሰነዘረ ሲሆን ውሳኔው አሁን ከተያዘው አቋምና ከሚተላለፉ ዘገባዎች ጋር በተያያዘ በህወሃት አመራሮች ዘንድ ቅሬታ በመኖሩ ነው።

Related stories   US Attempt To Make Pronouncements On Ethiopia’s Internal Affairs Regrettable :MoFA

ለዛጎል አስተያየት የሰጠ የቀድሞ የኮርፖሬሽኑ ሰራተኛ ” ነገሩ አሁን ኢቲቪ ከያዘው አቋምና የተነሳ የተወሰደ የፖለቲካው ውሳኔ እንደሆነ አሁንም በስራ ላይ ያሉ ባልደረቦቼ ነገረውኛል” ብሏል። ኮርፖሬሽኑ ሌላ ቢሮ ለመከራየት ቢፈልግ እንኳን ሊያጣ እንደሚችል ግምት እንዳለው ይኸው አስተያየት ሰጪ ገልጿል።

 

 

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *