አዲስ አበባን እሳት ለማድርገ የተሸረበው ሴራ ከሸፈ። የኦነግ አመራሮችን ለመቀበል የተጠራው የድጋፍና የአቀባበል ስነ ስርዓት ያለ አንዳች ኮሽታ ተጠናቀቀ። አዲስ አበባም ዜጎቿን አቅፋ ሰላም ውላ ሰላም አምሽታለች። የኦነግ መሪ አቶ ዳውድ ኢብሳ ከለውጡ ሃይል ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘው እንደሚሰሩና ድርጅታቸው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከማናቸውም የፖለቲካ ፓርቲ ጋር አብሮ ለመስራት ፈቃደኛ መሆኑንን አበሰሩ።

ከኦነግ ጋር በተያያዘ የሚነሱትን በርካታ የሁዋላ ታሪኮች በመንተራስ የአቀባበል ስነ ስርዓቱ ከሚካሄድበት አንድ ቀን ቀደም ብሎ ሁከትና ብጥብጥ፣ እንዲሁም ግጭት ተከስቶ ነበር። በማን እንደሚደገፉና ማን እንደሚደራጃቸው በግልጽ የማይታወቁ፣ ነገር ግን ከፍተኛ የገንዘብ ድጎማ የሚቀርብላቸው ወገኖች የጀመሩት ነውጥ በህዝብና በጸጥታ ሃይሉ ብርታት በቁጥጥር ስር ከዋለ በሁዋላ የተፈራው ዝግጅት ፍጹም ሰላምዊ ሆኖ ተጠናቋል።

ለሁለት አስርት ዓመታት ኤርትራ የነበሩት አቶ ዳውድ ኢብሳ የአገራቸውን ምድር እንደረገጡ፣ ለውጡን ማገዝ፣ መጠበቅና ከመንግስት ጋር ተደጋግፎ ለመስራት አገር ቤት መግባታቸውን ይፋ አድርገዋል። የቄሮ ሃይል በሳቸው በሚመራው ኦነግ እንደሚታዘዝና እንደተደራጀ ቀደም ሲል አስመራ እያሉ አስታውቀው የነበሩት አቶ ዳውድ፣ የሚከተሉትን ቁልፍ ጉዳዮች አስተላልፈዋል። ዶከተር አብይንም ሆነ አዲሱን የለውጥ ሃይል አመስግነዋል። ባቋራጭ በደጋፊነት ስም ለተቀላቀሉት ” ምኛችሁን ፈልጉ” አይነት ምላሽ ሰጥተዋል። አገር በጋራ ለመገናብተም እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።

• የዶ/ር ዐቢይ መንግስትን አመሰግናለሁ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን አመሰግናለሁ፡፡

• አገራችን እኩልነት የሚሰፍንባትና የህዝብ ድምጽ የሚከበርባት አገር እንዲትሆን እንሰራለን፡፡

• ከመንግስት ጋር ያደረግነው ስምምነት እንዲሳካ የኦነግና የህዝባችን ፍላጎት ነው፡፡

• ከዚህ በኋላ ህዝቡ የመጣውን ለውጥ ያስጠብቃል ብለን ለህዝቡ አደራ እንላለን፡፡

• እውነትና፣ አንድነት ሁሌም ያሸንፋል፣ ይህ የተፈጥሮ ሕግ ነው፡፡

• ኦነግ በአገር ግንባታ ውስጥ የድርሻውን እንደምወጣ ማረጋገጥ እንወዳለን፡፡

• ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ያለ ምንም ቅድሚያ ሁኔታ ጋር መስራት የተሻለ ለውጥ ያመጣል ብለን እናምናለን፡፡

• በኢትዮጵያ ውስጥ የሰብአዊና ዴሞክራሲያ መብቶች እንዲከበሩ ከመንግስት ጋር ስምምነት አድርገናል፤ ይህንን ተግባራዊ ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት ነው፡፡

የአቶ ዳውድ ኢብሳንና የዕለቱን ስነ ስርዓት የተከታተሉ እንዳሉት ቀኑንን ተገን በማድረግ አዲስ አበባን እሳት ለማድረግ ታቅዶ የነበረው እቅድ ብመክሸፉ መደሰታቸውን ለዛጎል ተናግረዋል። በሰልፉ ላይ የክቡር ለማ መገርሳ፣ የክቡር ገዱ አንዳርጋቸው፣ የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ፣ የአቶ ዳውድ ኢብሳ ምስል ያለበት ባነር በስፋት ታይቷል። 

[wpvideo 391nvz0f]

Related stories   በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 110 ሺህ ዶላር ተያዘ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *