1. ኢንትራሃምዊ የተቋቋመው ከኤም.አር.ኤን.ዲ (MRND) ከተሰኘው ፓርቲ በተውጣጡ ወጣቶች ነው::

2. “የእነ ጃዋር ቄሮና የኦነግ ሽኔ” የተቋቋሙት ከኦነግ ቅሪተ አካል ነው::

3. ኢንትራሃምዊ የተደራጀው የሁቱን ጎሣ በጠላትነት በመፈረጅና በጎሣው ላይ መጠነ ሠፊ የጥላቻና የጥፋት ቅስቀሣ በማድረግ ነው::

4. “የእነ ጃዋር ቄሮና የኦነግ ሽኔ” የተቋቋሙት በፀረ-ኢትዮጵያ ባጠቃላይ: በፀረ-አማራ በተነጥላ በተነጣጠረ የፕሮፓጋንዳ ሥራ ነው::

5. ኢንትራሃምዊ ሮበርት ካጁጋ በተሰኘ ፕሬዝዳንት እና ጆትጅስ ሩታጋንዳ በሚባል ም/ፕሬዝዳንት ነበር::

6. “የእነ ጃዋር ቄሮና የኦነግ ሽኔ” የሚመሩት በጃዋር መሃመድና ፀጋዬ አራርሳ እንዲሁም በተከታዮቻቸው ግርማ ጉተማ: እዝቂኤል ጋቢሣ: ጋዲሣ ዶሪ ወ.ዘ.ተ. ነው::

7. ኢንትራሃምዊ ይህን እኩይ የፀረ-ቱትሲ የቅስቀሣና ፕሮፓጋንዳ ሥራ ይሠራ የነበረውና የሁቱ መራሽ የዘር ጭፍጨፋ ያቀናበረው አር.ቲ.ኤል.ኤም [Radio Télévision Libre des Mille Collines (RTLM)] አማካይነት ነው::

8. “የእነ ጃዋር ቄሮና የኦነግ ሽኔ” የፀረ-ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ዘረኛና የዘር ጭፍጨፋን ኢላማ ያደረገ የቅስቀሣና ፕሮፓጋንዳ ሥራ የሚሠራው በጃዋር መሃመድ በሚመራው ኦ.ኤም.ኤን (OMN) አማካይነት ነው::

9. የሁቱዎቹ ኢንትራሃምዊ ግብ የቱትሲን ጎሣ በማጥፋት የሁቱን የበላይነት ማስፈን ነበር::

10. “የእነ ጃዋር ቄሮና የኦነግ ሽኔ” ተልዕኮም ኢትዮጵያን በማፍረስ “የኦሮሞ ግዛት” መመስረት ይህም ካልተቻለ ጎሣዊ የብዝሃን አምባገነንነትን በኢትዮጵያውያን ላይ መጫን ነው::

11. “የእነ ጃዋር ቄሮና የኦነግ ሽኔ” እንዲሁም የሩዋንዳው ጭፍጨፋ መሐንዲስ ኢንትራሃምዊ አንድነትና ልዩነት ምንድነው?

ሁለቱም በበታችነት ስሜት የሚነዱ፣ በፈጠራ ትርክትና አፈ-ታሪክ የተሞሉ አክራሪና ጎጠኛ ጠባቦች እንዲሁም በዴሞክራሲያዊ እሴቶች የማያምኑ መሆናቸው ነው:: ሁለቱም በዘር ማፈናቀል፣ ማፅዳትና ጭፍጨፋ የሚያምኑና የተገበሩ ወንጀለኞች ናቸው:: ልዩነታቸው ኢንትራሃምዊ ሩዋንዳዊ፤ “የእነ ጃዋር መሃመድና ፀጋዬ አራርሳ ቄሮና የኦነግ ሽኔ” ኢትዮጵያዊ መሆናቸውም ነው::

ቱትሲዎች ተደራጅተውና ተጠናክረው የተገበሩት የዘር ማፈናቀል፣ ማፅዳትና ጭፍጨፋ እንጂ ዴሞክራሲያዊ ማህበረሰብን አልነበረም:: የኦሮሞ አክራሪ የጎሣ ፓለቲከኞች አላማ የቱትሲዎቹ ቅጂ ነው::

ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ለመታደግ ኢትዮጵያዊያን ይህን ከፊታቸው የተደቀነውን የኦሮሞ አክራሪ የጎሣ ፓለቲከኞች ፍጅትና የጥፋት ድግስ ለመመከትና ለመቋቋም ብሎም ለማምከን ልዩነታቸውን በማቻቻል ሐገራዊና ሕብረ ብሔራዊ የትግል ግንባር በመስረት በአንድነትና በፅናት መቆም የወቅቱ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው:: ተደራጅቶና ተሰባስቦ ለጥፋት የተሠለፉ ኢንትራሃምዊ “የእነ ጃዋር መሃመድና ፀጋዬ አራርሳ ቄሮና የኦነግ ሽኔ” ደባ ማክሸፍ የሚቻለው በኢትዮጵያውያን ሕብረት ብቻ ነው:: የሕግ የበላይነት እንዲከበርና የዴሞክራሲያዊ ሥርዐት ለመገንባት መነሣት ነው::

“የእነ ጃዋር ቄሮና የኦነግ ሽኔ” የወያኔው “የጎሣ ፌደራሊዝም” እና መርዛማው የጎሣ ፓለቲካ ውጤት ናቸው:: ይህ መርዝ ሥር ሳይሠድ ማምከን የሚቻለው በኢትዮጵያዊ ሕብረትና በዴሞክራሲያዊ የፓለቲካ ሥርዐት ነው::

“የጎሣ ፌደራሊዝም” እና መርዛማው የጎሣ ፓለቲካ እንጠየፍ:: ዴሞክራሲያዊ እንጂ የጎሣ ፓለቲካ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን አይመጥንም::

የሃሣብ የበላይነትን በማንገሥ የጎሣ ፓለቲካና እሣቤውብ የጎሣ የበላይነትን ሕልም እናጨናግፍ!

እንደ ሐገር ዴሞክራሲያዊ ሆነን መኖር ካልፈቀድን እንደ ሕዝብ እንጠፋለን!

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   የምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ አቅል ያጣ ፍላጎት ግን ምንድን ነው!?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *