ቴዲ ሙለታ
ዘረኝነት ይሚለውን ቃል የእንግሊዝኛው መዝገበ ቃላት በዚህ መልኩ ይገልፀዋል :: prejudice, discrimination, antagonism directed against someone of different race based on the belief that one’s own race is superior . እያንዳንዱ ምን ማለት እንደሆነ እንደሚከተለው ለማየት እንሞክር
1) prejudice meaning
preconceived opinion that is not based on reason  or actual experience ይህም ማለት በመረጃና እውነት ያልተደገፈ ጠቃሚ ይልሆነ አመለካከት ማለት ነው:: እስቲ ካሁኑ ወይም የኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር አዛምደን እንመልከተው ::
ኢትዮጵያ ውስጥ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ስር የሰደደ የፍውዳሊዝም(የአፄዎች ስርአት) እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው :: እንደምናውቀውም ሆነ እውነታው አፄዎቹ ዘርም የላቸውም :: ምንም እንበል ምንም ሀቁ ይህ ነው :: እንደኔ አመለካከት ይህንን የሚያጠናክር ይምለውን ምክንያት ላቅርብ :: እኔ የዘር ምደባ ብልድግፍም በዘመኑ አጠራር አማራውም ኦሮሞውም ትግሬውም ይብዛም ይነስም የአፄነት ተራ ደርሷቸዋል :: በበቂ ሁኔታ ስለምናውቅ ማስረዳት አይጠበቅብኝም::  እኛ የተመረጥነው ለመግዛት ነው እንደውም ስዩመ እግዚአብሔር ብለው ራሳቸውን የጠሩም አለ:: ይህም የኢትዮጵያ ህዝብ ፈራሂ እግዚአብሄር እንደሆነ የተረዱት አፄዎቹ ይህ አመለካከታቸው በሚገዙት ህዝብ ላይ የስነ ልቦና ጦርነት የከፈተላቸው ይመስለኛል በኔ አመለካከት:: እነሱን የተቃወመ አምላክን እንደመቃወም ይቆጠራል በሚል እሳቤ :: ያም ሆነ ይህ ህዝቡ አፄዎቹን መቃወሙንም አላቆመም:: በትጨማሪም በአፄዎቹ መካከልም የእኔ እበልጣለሁና በስልጣን ሽኩቻ ምክንያት የተለያዩ ጦርነቶች ተደርገዋል :: በበቂ ሁኔታ ስለምናውቀው ማስረዳት የሚጠበቅብኝ አይመስለኝም :: ከጦርነቶቹ መካከል አንዱን ማንሳት ግን እፈልጋለሁ::  እጅግ ጎልቶ የሚወጣውና የወቅቱ ሬዝስታንስ(resistance)ነበረውና በገዳ ስርአት ስር ይተዳደር የነበረው የኦሮሞ ማህበረሰብ(society) ለአፄዎቹ ባለማጎብደዱና ትእዛዝ አልቀበልም በማለቱ ጦርነት መቀስቀሱ ነው :: እኔ በግሌ በአይኔም ያየሁት ብዙ ምርምር ያልተደረገበት ነገር ግን የዴምክራሲና የዘመናዊ አስተዳደር ምሳሌ ሊሆን የሚችል በአለም ላይ ቀድሞ ሊጠቀስ የሚችል ስርአት ባለቤት በመሆናችን ል ኮራበት ይገባል :: ይህም ስርአት ነው የዛሬውን ቄሮ ያፈራው :: ለዚህም ያበቁን ልናመስግናቸው ይገባል :: አመስግነናልም ::  የአፄ ምኒሊክ መንግስት እራሱን ለማስፋፋት በማሰብና አንድ አድርጎ ለመግዛት እንዲሁም መንግስታቸው እውቅና እንዲያገኝ የተለያዩ ጦርነቶችን ከፍተዋል ::
ከተለያዪ ማህበረሰባት ጋር ጦርነት እድርገዋል :: ልብ በሉ ከአማራ ማህበረስብ ጋር ተውግተዋል ከትግሬ ጋር ተዋግተዋል ከወላይታ ማህበረስብ ጋር ተዋግተዋል ከተለያዩ ማህበረሰቦች ጋር ውጊያ ገጥመዋል :: ለሳቸው መንግስታቸውን የማያውቅና የማይገብር ከሚሉት ጋር ሁሉ ጦርንት ገጥመዋል::ለመንግስታቸው እውቅና ከነፈጉት ጋር ሁሉ ተዋግተዋል: ከኦሮሞ ማህበረሰብ ጋር ተዋግተዋል:: ከከፈቷቸው ጦርነቶች ሁሉ ይህኛው በጣም አስቸጋሪውና ብዙ ውስብስብ ችግር ያመጣባቸው መሆኑን መገመት አያዳግትም:: በገዳ ስርአት የታገዘው የኦሮሞ ማህበረሰብ በጣም ይተደራጀ ከመሆኑም በላይ አልበገሬነትን ፈጥሮ ነበር :: ጦርነት መልካም ገፅታ የለውም :: የሚዋጋ ሁሉ ሰው ይገላል :: ገዳይም ጀግና ነኝ ብሎ ይፎክራል ይሸልላል:: ከብዙ አስከፊ ጦርነት በኃላ አፄ ምኒሊክ አሸንፈው ነግሰዋል :: አፄ ምኒሊክ ጡት ቆረጠ እያሉም የጦርነቱን አስከፊ ሁኔታ የሚገልፁም አሉ :: እስካሁን ይህንን የሚደግፍ መረጃ አላገኘሁም የተከበሩ ቡልቻ ደመክሳም ሆነ የቀድሞ የኦነግ አመራርና የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ነጋሶ ጊዳዳም አርጋግጠዋል :: ውሸት ውሸት ነው :: ውሸት እውነት ሊሆን አይችልም ::
የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሁኔታ በቅርብ የሚከታተሉት አሜሪካዎችም በላይብረሪ ኦፍ ኮንግረንስ የተፃፈ ምንም መረጃ የላቸውም:: በውሸት ላይ ቆመን ብንገኝ እውነቱ የታወቀ እለት ይዞን ይሰምጣል::ጦርነት ያለ መስዋእትነት አይደርግም:: በጦርነት ግዜ ሰው መሞቱ አይቀሬ  ነው :: ጦርነት ይቅር የምንለውም ለዚህነለዚህም ነው ጠቅላት ምኒስትር አብይና ኦቦ መገርሳ ያለፈውን ለታሪክ ትተን ለወደፊቱ እናስብ ያሉት :: በአንድነት የህዝቦችን ህይወት እንለውጥ ያሉት :: ሁለቱም መሪዎች ከማንም የማይተናነስ መስዋትነት ከፍለዋል በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ተቀባይነት አላቸው:: ይህ የ21 ኛው ክፍለ ዘመን ፖለቲካ ነው :: የሚያስፈልገን ዴሞክራሲ ብቻ ነው :: በዚህም ስርአት የሀይማኖትም ሆነ የዜጎች እኩልነት የሚርጋገጠበት ሰዎች በእኩልነት በፍትህ ፊት የሚዳኙበት መሆን አለበት :: የዚህ ሁሉ ትግል አላማው ዴምክራሲን ማስፈን መሰለኝ::  በአንፆሩ በአፄዎቹናእነዚህ ስርአቶች መልካም ነገር ሆነ በአሉታዊ ሊነሱ የሚችሉ በርካታ ችግሮችም ነበሩባቸው :: በመልካም ጎኑ ሊነገር የሚችለው ሁላችንም እንደህዝብ የምንኮራበት እየኮራንበት ያለነውምና ወድፊትም የምንኮራበት ለነፃነቱ በአንድነት እንዲዋደቅ ያደረጉ መሆናቸውን ነው:: ልብ ብለን ይህ ለኛ ምን ማለት እንደሆነ ማየት አስፈላጊ ነው::
አፓርትሃይድም ሆነ የባሪይ ንግድ ከህሊናችን የማይጠፋ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ የሰው ልጅ ላይ የደረሰ ዘግናኝ የታሪክ ክስተትን የምንረሳው አይደለም::  እኛ እድሜ ለተዋደቁት ጀግኖች አባቶቻችን ይህ አይነት ግፍ አልደረሰብንም :: እንደሸቀጥ አልተጏጏዝንንም እንደ ከብት አልተሸጥንም ማንነታችንን አልረሳንም ከየት እንደመጣን እናውቃለን አባቶቻችንን እናውቃለን እናቶቻችንን እናውቃለን አያቶቻችንን እናውቃለን ቅድመ አያቶቻችንን እናውቃለን ቅመ አያቶቻችንን እናውቃለን ባጠቃላይ ዘርማንዘራችንን እናውቃለን እነሱ በተዋደቁባት እና ትተውልን ባለፊት ምድር ላይ እየኖርን ነው ::( በተለይ በአሜሪካ የምንኖር ሰዎች የጥቁሮች African- American የዘር ምንጫቸውን ፍለጋ ሲኳትኑ ማየት እንዴት ልብ እንደሚነካ ያየነው ይምንመሰክረው ሀቅ ነው ::) የኛን የመሰለ በአለም ላይ አኩሪ ታሪክ የለም :: ምስክርም አያስፈልገንም:: እንደዚህ አይነት ያለ ዝግናኝ ነገር አልተፈፀመብንም:: የትኛው በደል ከባሪያ ንግድ ጋር እኩል አይደለም :: የትኛውም በደል ከአፓርታይድ ጋር እኩል አይደለም የትኛውም በደል ከናዚ የአይሁዶች ፍጅት ጋር እኩል አይደለም ::
ሳጠቃልል አፄዎቹ ለሚለው …አፄዎቹ አማሮችም ኦሮሞችም ትግሬዎችም ነበሩ :: አፄዎቹ ብሄር የላቸውም :: ስልጣ ነው የሚፈልጉት :: ምንም ምንም አድርጎ ስልጣን ላይ መቀመጥ ….ይህንን ደግሞ አፄ ይልሆኑትም ፈፅመውታል :: ይህንን ነው እንግዲህ ቄሮ የተቃወመው .: የታገለው :: ትግሉ በሁሉም ህዝ ቦች ተደግፎ የተደረገዉ :: ስለዚህ አፄዎቹን ከአንድ ማህበርሰብ የተውጣጡ አድርጎ መመልከት ውሸት ነው የምለው ::: ይህን ዉሸት ማናፈስም ዘረኝነት ::
ይቀጥላል!

[facebook url=”https://www.facebook.com/907126906053338/videos/258469771469300/” /]

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *