“Our true nationality is mankind.”H.G.

የጋሞ ጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በጋሞ ብሔር ተወላጆች ላይ የደረሰውን ጥቃት በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት

የጋሞ ጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኢሳያስ እንድሪያስ በአዲስ አበባ ዙሪያ እና በኦሮሚያ ልዩ ዞን አንዳንድ አከባቢዎች በጋሞ ብሔር ተወላጆች ላይ የደረሰውን ጥቃት በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት
ጋሞ
• ዳዳና አርሼ ቦንኬ ጋሞ
• ገቶና ተንኬሌ ዶርዜ ጋሞ
• ኦይታና ጉቼ ኤዞ ጋሞ
• ሳና ጎሎና መጋሮ ቦሮዳ ጋሞ
• አይሳና ቶይቶ ዶኮ ጋሞ
• ባተና ማንዶ ዲታ ጋሞ
• ቱፋዬና ማርቴ ጎዛ ጋሞ

ታሳ ታሳ ጋሞ ታሳ ታአየናው ታሳ

• ኦሮና ጋሞ ወይዛ ጋሞ
• ሸንደሮና ቶሮ ዛዳ ጋሞ
• አዋገና ጉጌ ሻማ ጋሞ
• አዛይነና ዳልኮ ካምባ ጋሞ
• ካኦና ካምባ ኦቾሎ ጋሞ
• ባረስና ቶሮ ከሌ ጋሞ
• ካረና ካማ ዛይሴ ጋሞ
• ካልሳና ጩባሮ ጋንታ /ጋሮ ጎዳው /ጋሞ

ታሳ ታሳ ጋሞ ታሳ ታአየናው ታሳ ታና ሞ

• ማጀና ፀጎ ዝጊቲ ጋሞ
• ሃሊላና ፓሻ ባልታ ጋሞ
• ማሮና ሻላዬ ጨንቻ ጋሞ
• ሃንዶሎና ኮቴ ኤሌ ጋሞ
• ሃሪናጋና ኮቴ ኤሌ ጋሞ
• አማይና ሾቴ ዋጫ ጋሞ
• ቃራ ቃለና ኮንቴ ጉጌ ጋሞ
• አልቤና አሸ ደዮ ወባራ ጋሞ
• ወንጃለና ቱቆ አንድሮ ጋሞ

ታሳ ታሳ ጋሞ ታሳ ታአየናው ታሳ

• ፓሻና ጎበና ቁጫ ጋሞ
• ጋንቶና ድሜ ኦቶሎ ጋሞ
• ዳቼና ሌቃ ሻራ ጋሞ
• ማረቆና ማኬ ጋርዳ ጋሞ
• እርባቶና ፔራ ማርታ ጋሞ
• ኮንታና ቶጋ ሱሌ ደራ ጋሞ
• ጋንታና ወርቃ ጮዬ ጋሞ
• ማይና ጠና ዛርጉላ ጋሞ
• ሣላና ገርግሳ ብርብረ ጋሞ
• አንችሌና ቦቾ ዶቃማ ጋሞ

ታሳ ታሳ ጋሞ ታሳ ታአየናው ታሳ

• ወላና አርባ ሱልአ ጋሞ
• ጎበና አጫ ካይፀ መናና ጋሞ
• አድዮና አርባ ሼላ ጋሞ
.
.
.
ጋሞ አሳ ኦየና ፣ ጋሞ አሳ ባይራ ጋሞ
ጫሬያ ጎዳው ጋሞ ፣ አባ ጎዳው ጋሞ
ጉጌ ዙማ ጎዳው ፣ ፑልቶ ጎዳው ጋሞ
ሃርጳ ጎዳው ጋሞ ፣ ጢባባ ጎዳው ጋሞ
ማታው ጎዳው ጎግዳ ሀታ ጎዳው ፣ 
ዱንጉዛ ጎዳው ሌላሼ ጎዳው 
ጋሞ ታአየናው ታሳ ጋሞ
ታናሞ ታአየናው ፣ ታናሞ ታሳ ታሳ

የጋሞ ብሔር በ42 ዴሬዎች የሚኖርና ከ2.6 ሚሊየን ህዝብ በላይ ቁጥር ያለው ነው፡፡ ጋሞ ብሔር የሌላውን ብሔር ህዝብ የሚያከብር ጋሞነቱና ኢትዮጵያዊነቱ አንድም ጊዜ ተወሳስቦበት የማያውቅ ክቡር ህዝብ ነው፡፡

ጋሞ መለያ ባህሪው ሥራ ነው፤ ጋሞ አይገድልም፤ጋሞ አይሰርቅም ፤ጋሞ አይዋሽም ፤ ጋሞ መላ ኢትዮጵያ ሀገሩ ነው፤ ወዳጁም የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፡፡

በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች በሚከሰተው ሁከትና ግጭት ሰለባ እየሆነ ያለው ይህ ክቡር ህዝብ መብቱ በህገ መንግስቱ በተደነገገው መሰረት እንዲከበር የዞኑ አስተዳደር አበክሮ ይጠይቃል፡፡

በአዲስ አበባ ዙሪያ እና በኦሮሚያ ልዩ ዞን ብሔር ተኮር ጥቃትና ግድያ የሚፈፅሙ አካላት ከእኩይ ተግብራቸው እንዲታቀቡ እና ወንጀል የፈፀሙ አካላት ለህግ እንዲቀርቡ የሚመለከተው የፌደራል እና የኦሮሚያ ክልል መንግስታት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱና የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እንጠይቃለን፡፡

ጋሞ ሆይ

የጋሞ ጎፋ ዞን አስተዳደርና መላው ህዝብ የደረሰብህ ጉዳት ጉዳታችን ሀዘናችሁ ሀዘናችን እንደሆነ እየገለፅን ውድ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖቻችን በአብ ቀኝ እንዲያስቀምጣቸው እንማፀናለን፡፡በሀዘን ላሉ ወገን ዘመዶቻቸው እና ለመላው ጋሞ ህዝብ መጽናናትን እንመኛለን፡፡

የአካል እና የሞራል ጉዳት ለደረሰባችሁ እንዲሁም ንብረት ለወደመባችሁ ወገኖች ከዞኑ አስተዳደር እና ከጋሞ ጎፋ ልማት ማህበር 1.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ የተበረከተ ሲሆን ተጨማሪ ገቢ ለማሰባሰብ ዞናዊ ኮሚቴ ተዋቅሯል፡፡ መላው የዞናችን ህዝቦችና የሀገራችን ህዝቦች ለተጎዱ ወጎኖች ድጋፍ የሚያደርጉበት የባንክ አካውንት የሚከፈት ይሆናል፡፡

ሚዲያዎች ክቡር የሆነውን የሰው ህይወት አሰቃቂ ግድያና ጭፍጨፋ በማውገዝ ሙያዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ እንጠይቃለን፡፡የተከበራችሁ የሃይማኖት አባቶች ፣የሀገር ሽማግሌዎች ፣ወጣቶችና ሴቶች፣ ሙሁራን ፣የሚዲያ ተቋማት ፣ጦማሪያን በሙሉ ክፉ ለሠራ ክፉ መስራት የለብንም፣የጎዳንን መጉዳት የለብንም ፣ በባህላችን ጎሜ መሆኑን በመገንዘብ በሁሉም የጋሞ አከባቢ ወረዳዎችና ከተሞች እንዲሁም በሁሉም የዞናችን አከባቢዎች ያሉ የሌሎች ብሔር ብሔረሰብ ተወላጆችን በበለጠ ወገናዊ ፣በፍፁም ፍቅር በመተሳሰብ ላይ የተመሰረተ የአንድነት መንፈስ በሰፈነበት በትምህርት ቤት፣ በሰፍር፣ በሃይማኖት ተቋማት እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ አስተዋይነታችሁንና ወገንተኝነታችሁን እንድታሳዩ በዞኑ ሕዝብና አስተዳደር ስም በታላቅ አክብሮት ላሳስባችሁ እወዳለሁ፡፡

በዛሬው ዕለት የተካሄደውን የሀዘን መግለጫ ሰልፍ ለማወክ የሞኮሩ ሃይሎችን በፀጥታ ሃይሉ እና በህዝቡ ትብብር መቆጣጠር የተቻለ ሲሆን ከተማው አሁን ላይ በተረጋጋ ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡በተፈጠረው ሁከትም የ2 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ13 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን በደረሰው ጉዳት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን፡፡

የፀጥታ ኃይሉ የወሰደው ትዕግስት የተሞላበት አመራር እና ህብረተሰቡ ላደረገው ትብብር የዞኑ አስተዳደር ምስጋናውን ይገልፃል፡፡ ህዝቡ ያሳየው አስተዋይነትና ትዕግስት አስተማሪ በመሆኑ መቀጠል እንዳለበትም አበክረን እናሳባለን፡፡

በመጨረሻም በጋሞ ብሔር ተወላጆች ላይ በደረሰው ጥቃት የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅኩ ለመላው የዞናችን ህዝቦች እና ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ፡፡
አመሰግናለሁ

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   አገርን የከዱ ተደመሰሱ፤ የሳተላይት መገናኛና መድሃኒት " ጁንታው" እጅ ሳይገባ ተያዘ
0Shares
0