የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዜብሄር ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፥ ድርጅቱ ባለፉት 5 ወራት ባከናወናቸው ተግባራትና የተደረገውን የአመራር ለውጥ ተከትሎ የታዩ መልካም ጅምሮችን ለማስቀጠል የሚያስችሉ ሀሳቦችን ያካተተ ሰነድ በጉባኤው ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል።
 
የድርጅቱ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር ምርጫም በዚሁ ጉባኤ እንደሚካሄድም ነው ኃላፊዋ የተናገሩት።
 
በጉባኤው የሚቀርቡ አጀንዳዎች ከመስከርም 4 እስከ 5 በተካሄደው የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ የተለዩ መሆኑን የገለጹት ሀላፊዋ፥ በ10ኛው ጉባኤ የተወሰኑ ውሳኔዎች እና አፈፃፀም እንዲሁም እስከ 12ኛው ጉባኤ ድረስ የሚተኮርባቸው ዋና ዋና ሀሳቦች ላይ በስፋት ምክክር እንደሚደረግባቸው አስረድተዋል።
 
በዚህ ጉባኤ ሀገሪቱ ባለፉት 3 ዓመታት ከገባችባቸው ውጣ ወረዶች የሚያስወጡ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም የኢህአዲግ ምክር ቤት ጽ/ቤት ሃለፊ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዜብሄር ተናግረዋል።
 
በሀገሪቱ የተላያዩ አካባቢዎች ተከስተው በነበሩ ወቅታዊ ጉዳዮች ምክንያት ጉባኤው ሳይካሄድ ለተጨማሪ 6 ወራት መራዘሙን ያስታወሱት ሃለፊዋ፥ በኢህአዴግ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት በየሁለት አመቱ ወይንም በየሁለት ዓመት ከ6 ወሩ ድርጅታዊ ጉባኤው መካሄድ የነበረበት መሆኑን ጠቁመዋል።
 
በዚህም መሰረት በነሃሴ ወር 2007 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን ያካሄደው ኢህአዴግ በመጋቢት ወር 11ኛ መደበኛ ጉባኤውም ማካሄድ የነበረበት መሆኑ ገልጸዋል።
 
በጉባኤው ከእያንዳንዱ ብሄራዊ ደርጅቶች ድምጽ የሚሰጡ 250 ተሳታፊዎች በድምሩ ከአራቱ ብሄራዊ ድርጅቶች 1 ሺህ ተሳታፊዎች እንደሚሰታፉም ነው የተገለጸው።
 
ድምፅ የማይሰጡ የፌደራል መስሪያ ቤትና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሃላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ ማህበራትና ፌደሬሽኖች የሚሳተፉ ሲሆን፥ ከ1 ሺህ 800 በላይ ተሳታፊዎች በጉባኤው እንደሚታደሙ ተገልጿል።
(ኤፍ.ቢ.ሲ) 

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   “የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች አለመምጣት የሚያጎለው አንዳችም ነገር የለም፤ እኛም አንጠብቃቸውም” ፕሮፌሰር በየነ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *