በዛሬው ዕለት ይጀምራል ተብሎ የነበረው 9ኛው የኦህዴድ ድርጅታዊ ጉባኤ ለነገ መራዘሙ ተገለፀ። ለዚህም ተሳታፊዎችና የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በጅማ ዩኒቨርስቲ አዳራሽ ውይይት እያካሄዱ ይገኛል። በውይይታቸውም በዘጠነኛው የኦህዴድ መደበኛ ድርጅታዊ ጉባዔ የቀረበ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ሪፖርት ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

በጥቅሉ ሪፖርቱ 158 ገጾች መያዙ የተጠቀሰ ሲሆን÷ የጥልቅ ተሃድሶ ንቅናቄ ግምገማ፣ የስምንተኛው ድርጅታዊ መደበኛ ጉባዔ አቅጣጫ፣ የትራንስፎርሜሽንና የኢኮኖሚ አብዮት ሽግግር አፈጻጸም እና ሌሎችም አጀንዳዎች ላይ ይመክራሉ ተብሏል፡፡

የነገውን 9ኛ የኦህዴድ ድርጅታዊ ጉባኤ የምታስተናግደው ጅማም እንግዶቿን ለመቀበል ዝግጁ መሆኗንም ተነግሯል፡፡

በ9ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ የኦህዴድ ኢህአዴግ ሊቀመንበር ዶክተር አብይ አህመድ እና የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳ እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡

በጅማ ከተማ የሚካሄደው ጉባኤ ‘‘የላቀ ሃሳብ ለተሻለ ድል’’ በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል።

በጉባኤው ላይ በድምጽ የሚሳተፉ 1ሺህ66፣ በታዛቢነት የሚሳተፉ 250 ሰዎች ጂማ ከተማ ተጠቃለው መግባታቸውንም አመላክተዋል።

በጉባኤው ታሪካዊ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉ የተገለፀ ሲሆን፥ ያለፉት ሶስት ዓመታት የውስጠ ድርጅት አፈጻጸም ይገመገማል፤ የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን ሪፖርትም ቀርቦ ውውይት የሚካሄድበት መሆኑን አስረድተዋል።

በጉባኤው ቆይታ የድርጅቱን ስያሜ፣ አርማ እና መዝሙር ለመቀየር የሚያስችል ረቂቅ ቀርቦም ውይይት እንደሚካሄድበት ይጠበቃል።

በድጋፌ ዳኛቸው FBC

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   “የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች አለመምጣት የሚያጎለው አንዳችም ነገር የለም፤ እኛም አንጠብቃቸውም” ፕሮፌሰር በየነ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *