ኬንያዊው ኢሊዩድ ኪፕቾጌ በበርሊን ማራቶን 2 ሰዓት ከአንድ ደቂቃ ከ39 ሰከንድ በመግባት የአለም ሪከርድን ማሻሻል ቻለ።

የ33 ዓመቱ ኤሊድ ኬፕቾጌ ከዚህ በፊት በዴኒስ ኪሜቶ ተይዞ የነበረውን የ2 ሰዓት ከ02 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ ሪከርድ ከአንድ ደቂቃ በላይ በማሻሻል የሪከርዱ ባለቤት መሆን ችሏል።

አትሌቱ ቀኑን ለመግለፅ ቃላት እነዲሚያጥረው በመግለፅ የማራቶን ሪከርድ በማሻሻሉ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማው ገልጿል።

ሌላኛዎቹ ኬንያውያን ሞሰስ ኪፕሮቶ 2 ሰዓት 06 ደቂቃ 24 ሰከንድ እና ኪፕሳንግ 2 ሰዓት 06 ደቂቃ 48 ሰከንድ ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመሆን በበላይነት ርቀቱን አጠናቀዋል።

ይህን ውጤት ተከትሎ ኢሊዩድ ኬፕቾጌ በማራቶፐን ውድድር ድንቅ ታሪክ ካስመዘገቡ አትሌቶች መካከል አንዱ መሆን ችሏል።

በሴቶች የማራቶን ውድድር ግላድየስ ቼሮኖ 2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ በመግባት ያሻነፈች ሲሆን፥ ኢትዮጵያዊቷ ሩቲ አጋና ጥሩነሽ ዲባባ ውድድሩን በሁለተኛና ሶስተኛነት አጠናቀዋል።

ምንጭ፦ቢቢሲ – (ኤፍ.ቢ.ሲ)

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *