ሕዝብን በብሄር አጋጭተው አገርን ለመበታተን ከፍተኛ በጀት የተመደበላቸው የህቡዕ አደረጃጀቶች እና ዋና መሪዎቻቸው ጉዳይ እጅግ አነጋጋሪ በሆነበት በአሁኑ ሰዓት ኦሮሚያ ክልል በተጠርጣሪዎቹ የባንክ አካውንት ስምንት ሚሊዮን ብር መገኘቱን ይፋ አደረገ። 

ሃሰተኛ ኖት፣ ሃሰተኛ ማህተምና ከፍተኛ ቁጥር ያለው ገንዘብ የተያዘባቸው እነዚህ ክፍሎች በከፍተኛ ደረጃ የተደራጁ፣ የተለያዩ አደረጃጀቶች ያሉዋቸው፣ በየአካባቢው መሪ ያላቸው ሲሆኑ ይህ የተያዘው ገንዘብና መረጃ የአንደኛው ቡድን ብቻ መሆኑ አስገርሟል።  ዘራፊ ሊባሉም እንደማይችሉ ተመልክቷል። ኢቢሲ  ዶክተር ነገሪ ሌንጮን ተቅሶ ከታች ያለውን ዘግቧል። 

በዛሬው እለት ቡራዩ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ አከባቢዎች ወደ ሰላም መረጋጋታቸው ተመልሰዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮሙዪኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ በሰጡት መግለጫ፥ ችግሩን በመፍጠር ህዝብን ለአደጋ በማጋለጥ የፖለቲካ አላማቸውን ከግብ ለማድረስ ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ ከአዲስ አበባ ጀምሮ የተንቀሳቀሱ ካላት መኖራቸውን አስታውቀዋል።

የዚህ ጥፋት ሀይል አካል የሆነ 99 አባላት ካለው ቡድን ውስጥ ስድስት ሰዎች የጦር መሳሪያ ማለትም፥ 3 ክላሽ እና 8 ሽጉጥ ሁለት መኪና፣ የባንክ እንዲሁም ደብተር እና የቡራዩ ከተማ መሬት አስተዳደር ሀሰተኛ ማህተም ይዘው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው ያስታወቁት።

የሀሰት ገንዘብን ጨምሮ መጠኑ ከፍ ያለ ገንዘብ መያዙን እና በተጨማሪም በተያዙት ሰዎች የባንክ ሂሳብ ውስጥ 8 ሚሊየን ብር ተገኝቷል ብለዋል።

በዛሬው ዕለትም የቀሩትን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ እየተከታተለ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ከህብረተሰቡ ጋር በመወያየት እስካሁን ከ300 በላይ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው አንዲመለሱ ማድረጉን አስታውቀዋል።

የቀሩትንም ለመመለስ አስፈላጊው ድጋፍ የፌደራል መንግስትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ የክልሉ መንግስት በጋራ እየሰሩ ይገኛሉም ብለዋል።

በግድያና ዝርፊያ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት 200 ሰዎች መካከል በ23 ሰዎች ላይ መረጃ ተመርምሮ እየተጠናቀቀ በመሆኑ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ዶክተር ነገሪ ተናግረዋል።

ንብረታቸው የተዘረፈ ሰዎች ንብረታቸው ከዘራፊዎች ተሰብስቦ ተመልሷል ያሉት ሀላፊው፥ የክልሉ መንግሰት አስፈላጊውን ድጋፍ አድርጎ የተዘረፈውን ንብረት በቦታው ለመመለስ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።ምንጭ:-FBC

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *