“Our true nationality is mankind.”H.G.

“የኦሮሞ ብሄርተኛነት ሼልፍ ላይ ተቀምጦ የበሰበሰ አይደለም – ወደ አዎንታዊነት ተሸጋግሯል”ሕዝቅኤል ገቢሳ

” እኛ የምንነት፣ የሰብአዊ መብትና ይይዞታ ጥያቄ ስናነሳ ለምን ኢትዮጵያን ወደ መበታተን አጀንዳ እንደሚቀየር አይገባኝም። ኦሮሞ ሺልፍ ላይ የበሰብሰ ብሄርተኛነትን እያራመደ እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል” ሲሉ ነው የሚጀምሩት። ዛሬ በአማራ ክልል የማንነት፣ የይዞታ፣ የዴሚክራሲ ጥያቄ አለ። በሌሎችም አካባቢዎች ተመሳሳይ ጉዳይ አለ። ሃሳቡ ወደ ኦሮሞ ሲመጣ ግን ይጣመማል። አይታመንም። ይህ የሚመነጨው ከአጉል ፍርሃት የሚመነጭ በመሆኑ ነው። ይህን ከፍተኛ ችግር ማጥፋት እንኳን ባይቻል መቀነስ ይቻል ዘንድ መነጋገር እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ያክላሉ።

” የኦሮሞ ህዝብ ሌሎች ያልጠየቁትን ጥያቄ አልጠየቀም” የሚሉት ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል በተለይ ኢትዮጵያን እንወዳለን የሚሉ ወገኖች አሁን የኦሮሞ ብሄርተኛነት የደረሰነት ደረጃ በወጉ ሊረዱት ይገባል ባይ ናቸው። የዛሬ አርባ ዓመት በድለን ሲልም የነብረው ብሄርተኛነት ዛሬ ላይ የሚታሰብ እንዳልሆነም አመልክተዋል።

ከባልደረባቸው አቶ ደጀኔ ጣፋ ጋር በመሆን ከኦሮሚያ ሚዲያ ኔት ዎርክ ጋር ዛሬ ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት የዛሬ አርባ ዓመት ሲጠየቁ የነበሩ ጥያቄዎችና የዛኔ የነብረው አስተሳሰብ ዛሬ አለመኖሩን ገልጸዋል። ” ሲጀመር በአሉታዊ ገጽታው የተጀመረው የኦሮሞ ትግል፣ አሁን ወደ አዎንታዊ ተሸጋግሯል” ሲሉም ለማብራራት ሞክረዋል። አክለውም ዛሬ ላይ የኦሮሞ ትግል ጥላቻ ላይ የተመሰረተ እንዳልሆነ ጠቁመው፣ መንግስት ብቻ ሳይሆን የተቃዋሚ ፓርቲዎች በዚህ ጉዳይ ላይ የጠራ አመለካከት በመያዝ ፍርሃቻ የሚወገድበትን አግባብ ሊከተሉ እንደሚገባ ሃሳብ ሰጥተዋል። አጠንክረው መናገር እንደሚፈልጉ ጠቅሰው ጊዜው ኦሮሞ አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመገንባት ከማንም በላይ ሃላፊነት የወሰደበትና ፣ ቀደም ሲል ጀምሮ ለዳር ድንበር መከበርና ለኢትዮጵያ እንደ አገር መቀጠል ዋጋ የከፈለን ህዝብ ማክበር እንደሚገባ፣ አገር በታታኝ የሚል ታቤላ መለጠፍ አግባብ እንዳልሆነና በዚህ አግባብ የሚገኝ ጥቅም የለም እንደሌለ አብራርተዋል።

በተለይም በቡራዩና አካባቢው የተፈጸመውን አስነዋሪ ጥቃት አስመልክቶ አስተያየታቸውን ሲሰጡ ጉዳዩን በሶስት ከፍለውታል። ስልጣን ሲለቁ የኢኮኖሚና የፖለቲካ የበላይነታቸውን ያጡ ነገር ግን ሃብት ያላቸው፣ የቀድሞ አይነት አሃዳዊ ስርዓት እንዲመለስ የሚፈልጉና በስርዓቱ ውስጥ ያሉና ለውጡን በአግባቡ ያልተቀበሉ የአምባ ገነን ቅሪቶች ውጤት እንደሆነ አጠቃላይ ስዕል ሰጥተዋል።

እነዚህ የፖለቲካ የበላይነታቸውን የተነጠቁና በፖለቲካ የበላይነታቸው ያገኙትን የኢኮኖሚ ጥቅም ያጡ ክፍሎች ስርዓት ከያዘው ፍክክር ውጪ በአሻጥር ተግባር ላይ ተሳትፈዋል ብለዋል። በሌላም ወገን አሃዳዊ ስርዓት የመመለስ ህልም ያላቸው ወገኖች ችግር እየፈጠሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ከሁሉም በላይ ግን የአምባ ገነን ሰርዓት ወድቆ የዲሞክራሲያ ግንባታ መጀመሩ ምቾት ያልሰጣቸው አኩራፊ ወገኖች፣ አዲሱን መንግስት አገር ማስተዳደር አይችልም በሚል ለማስፈረጅና ያለውን ተቀባይነት ለማሳጣት ፣ የማተራመስ ድራማ እንደሚጫወቱ መገንዘብ አስፈላጊ መሆኑንን አጽንዖት ሰጥተው አብራርተዋል።

ትግራይ ኦንላይን የሚሰኘው ድረ ገጽ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ራሳቸውን ከሃላፊነት ማግለል እንዳለባቸው አሳስቧል። ካላይ ፕሮፌሰር ህዝቅኤል የትርምሱን ዓላማ እንዳስቀመጡት፣ ድርገጹ ዶክተር አብይን በራሱ እይታ ገምግሞ ህዝብ ራሳቸውን ከሃላፊነት እንዲያነሱ ሲጠይቅ ካነሳቸው ምክንያቶች መካከል ታላላቅ ፕሮጀክቶች፣ የህዳሴውን ግድብ ቸመሮ እንዲቆም ማድረጋቸውን ያነሳል። ይህንን ትግራይ ኦን ላይን በአገሪቱ ስለተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ሙስና፣ ዘርፈው ተደበቁ ስለተባሉት ሃላፊዎችና፣ ሳይሰሩ ገንዝብ በመውሰድ አገሪቱን ለከፋ እዳና ውድቀት ዳርገዋል ስለተባሉት ክፍሎች አላብራራም። ቆሙ ስለተባሉት ፕሮጀክቶች እንዲቆሙ ወይም በተገቢው መንገድ እንዲጠኑ ስለተወሰነበት ምክንያት ያለው ነገር የለም።

በሌላም በኩል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ መፈናቀሉን የዶክተር አብይ የአመራር ጥበብ ችግር እንደሆነ ያመለከተው ትግራይ ኦንላይን፣ በሶማሌ ስለደረሰው እጅግ አሰቃቂ እልቂትና በሚሊዮን የሚቆተሩ ዜጎች እንዲፈናቀሉ ምክንያት መሆናቸውን የክልሉ አዲስ አስተዳደር በግልጽ ያስቀመታቸውን ጀነራሎች ጉዳይ አላነሳም። በክልሉ ከፈተኛ የታጠቀ ሃይል በማሰልተንና በኮንትሮባንድ ንግድ መቋረጥ ሳቢያ ይህ ሁሉ እልቂትና መፈናቀል እንዲደርስ ከጀርባ አሉ ስለሚባሉ ወገኖች አላብራራም። 

ሲጀመር ገና ግድያ የተሞከረባቸው ዶከተር አብይና ኦሮሞ አገር መምራት እንደምይችሉ ለአሜሪካ መንግስት ሃሳብ በማቅረብ ሰላማዊ የመንግስት ግልበጣ ለማካሄድ ለአሜሪካ ጥያቄ መቅረቡ አይዘነጋም። በፓርቲ ደረጃም ” ህዝበኛ” በሚል ሲዘለፉ እንደነበርም አይዘነጋም።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ማጣራቱ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን እንደሚያካትት አስታወቀ፤ መንግስትና አማራ ክልል በማይካድራ ጉዳይ ተኝተዋል
0Shares
0