“Our true nationality is mankind.”H.G.

የጋሞ ብሔረሰብ ተወካይ የሆኑ አባቶች ከቡራዩ እና አካባቢዋ የተፈናቀሉ ዜጎችን ጎበኙ

(ኤፍ.ቢ.ሲ) የጋሞ ብሔረሰብ ተወካይ የሆኑ አባቶች፣ ሴቶችና ወጣቶች ከቡራዩ እና አካባቢዋ ተፈናቅለው በአዲስ አበባ በተለያዩ መጠልያዎች ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ቦታው ድረስ በመገኘት ጎበኙ፡፡

የጋሞ አባቶች የተከሰተውን ችግር በሠላምና በፍቅር መፍትሔ የሚያገኝበትን መንገድ ለማመቻቸት የጋሞን ወርቃማ ባህል በመከተል ዕርቅ መፍጠር ይገባል ብለዋል፡፡ ወጣቱ ትውልድም ባህሉን በማይወክል መልኩ ለሌላ በቀል እንዳይነሳሳ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

የጋሞ ጎፋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ኢሳያስ እንድሪያስ በለውጥ ጉዞ ላይ ድርጊቱ መፈጸሙ እጅግ የሚያሳዝን ተግባር በመሆኑ መወገዝ ያለበት ድርጊት ነው ብለዋል፡፡ የዞኑ አስተዳዳሪ ሰሞኑን ለተከሰተው ችግርም መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

በመጨረሻም ለተፈናቀሉት ዜጎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላደረገው ድጋፍ የጋሞ ብሔረሰብ ተወካዮች ምሥጋና ማቅረባቸውን ከአዲስ አበባ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ፋኦ በትግራይ ክልል ለአርሶ አደሮች የእህል ዝርያዎችን ማሰራጨትና እንስሳቶችን መከተብ ጀመረ
0Shares
0