“Our true nationality is mankind.”H.G.

ያኮረፉ አሮጌ ኦህዴዶች ትሥሥራቸውን ተጠቅመው የታሰሩትን ለማስፈታት እየጠሩ እንደሆነ ተሰማ፤ ጥበቃው በመከላከያ ስር ነው

አገር ለማተራመስና የዶከተር አብይን አመራር ለመገፍተር በህቡዕ የተደራጀው ቡድን ውስጥ ያኮረፉ አሮጌ የኦህዴድ አመራሮች እጅ እንዳለበት የቡራዩ የዛጎል ምንጮች አስታወቁ። እነዚሁ ክፍሎች መረጃ ለመደበቅ በሚል የታሰሩትን የቡድኑን መሪዎች ለማስፈታት እየሞከሩ ነው።

በቡራዩ የተፈጸመው አሰቃቂ ተግባር ከመፈጸሙ በፊት ጀመሮ ለዛጎል መረጃ የሚያቀብሉት የቡራዩና አካባቢው ወጣቶች እንዳሉት፣ ” አሮጌ” ሲሉ የሚጠሯቸው የኦህዴድ አመራሮች ከተጀመረው ለውጥ ጋር መራመድ አይችሉም በሚል ተገምገመው ከተሰናበቱትና ከታገዱት ውስጥ የሚካተቱ ናቸው።

Related stories   ወደ ድርደር ? ከታንክ ወደ አህያ የወረደው ትህንግ በማን ሊወከል?

ኦሮሚያ በእነ ሙክታር አህመድ እና አስቴር ማሞ በመሳሰሉት የበላይነት ይተዳደር በነበረበት ወቅት ኦህዴድ እጅግ የህወሃት ታማኝና ታዛዥ ድርጅት ከመሆኑ በላይ ስለከልሉ የሚሟገት አልነበረም። በክልሉ ተወላጆች ላይ እጅግ የከፋ ግፍ፣ ግድያ፣ እስርና እንግልት እንዲሁም ዝርፊያ ሲፈጸም ተሳታፊ እንጂ ተከራካሪ ሆነው አያውቁም።

እንደ ዜናው ምንጮች ከሆነ የኦሮሚያ ትግል እየተቀጣጠለ በነበረበት ወቅትና ለውጡ በኦፊሳል ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የታገዱትና የተሰናበቱት አሮጌ ኦህዴዶች አላረፉም። ከቀድሞ አንጋሾቻቸው ጋር ባላቸው ግንኙነት ድርጅቱን በቀድሞው ድርጅታዊ መዋቅራቸውና ትሥሥራቸው አማካይነት መገዝገዝ የጀመሩት መሰናበታቸውን ተከትሎ ነው።

Related stories   የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ለአሶሼትድ ኘሬስ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ሰጠ

እጅግ ከፍተኛ ሃብት ያላቸው ዋና ዋና አሮጌ ኦህዴዶች አሁን በቁጥጥር ስር የዋሉትን ቅጥረኞች ለማስፈታት እላይ ታች ቢሉም የሚሆን እንዳልሆነ ምንጮቹ ተናግረዋል። እንደ ምንጮቹ ከሆነ በቁጥጥር ስር የዋሉት ወጀለኞች የሚጠበቁት በመከላከያ አባላትና በጥምር በተቋቋመ ሃይል በመሆኑ ሊሳካላቸው አልቻለም።

መሪ እንደሆኑ የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ “ኦሮሞ ወላዋይ አይፈልግም፤ በህዝቡ የምትነግዱ ለራሳችሁም፤ ለኦሮሞ ህዝብም አትሆኑም፤ ጠዋት እዚህ፤ ከሰዓት ደግሞ እዚያ አትቁሙ”  ያሉት አለቆቻቸው ቢባረሩም ሙሉ በሙሉ ባለመጥራቱ ኦህዴድ ውስጥ ለውጡን አስፈጻሚ እየመሰሉ ከቀድሞው ጌቶቻቸው ጋር የሚሸርቡትን እንደሆነ ምንጮቹ አመልክተዋል።

Related stories   ‹‹የህዳሴው ግድብ ለሱዳን ከፍተኛ ጥቅም አለው፤ የቀጠናውን የኢኮኖሚ ትስስር ያጠነክራል››

 

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0