በመጪው የኢህአዴግ ጠቅላላ ጉባኤ፣ የማንነትና የወሰን ጥያቄዎች በድርጅት ደረጃ አጀንዳ እንዲሆኑ እህት ድርጅቶቹ በተናጠል እየወሰኑ መሆኑ ተሰማ። የሚያዘው አቋም ህወሃትን ከድርጅቱ ሊያሰናብተው እንደሚችል ከወዲሁ ስጋት አለ።

የዛጎል ታማኝ የመረጃ አቀባዮች እንዳሉት ሲጓተት የቆየው የኢህአዴግ ጉባኤ ከመካሄዱ በፊት፣ በድቡብ ክልል በተደጋጋሚ ሲቀርብቡ የነበሩ የዞንና የክልል ጥያቄዎች ምላሽ ያገኛሉ። ይህንኑ አስመልክቶ የክልሉ አዲሱ ሊቀመንበር ጥናቱ መጠናቀቁን መናገራቸውን ምንጮቹ በማስረጃነት ያስደጋሉ።

የአማራ ክልል በወልቃይት፣በራያ በመሳሰሉት አካባቢዎች ያለው ጥያቄ የማንነት መሆኑን ባለፈው ጉባኤው አበአቋም ደረጃ ምሳወቁንና መንግስት ጉዳዩን እንዲመለከተው መተየቁ ይታወሳል። እንደ መረጃው ምንጮች ኦዴፓ በአማራ ክልል ጥያቄ እምነት አለው። ኦዴፓ ብቻ ሳይሆን የኦሮሚያ ተቀናቃኝ ድርጅቶችም በተደጋጋሚ ድጋፍ እንደሚሰጡ ሲገልጹ ነው የቆዩት።

የተለያዩ ይወሰንና የማንነት ጥያቄ በአሉታዊ መልኩ የሚቀርብበት የትግራይ ክልል በመሆኑ፣ ህወሃት ደግሞ የማንነት ጥያቄ ላይመለስ በህገመንግስቱ ታትሟል የሚል አቋም እንዳለውና ” ካሁን በሁዋላ የወልቃይት ጉዳይን ማንሳት በትግራይ ክልል ላይ ወረራ እንደማካሄድ ይቆተራል” የሚል አቋም ስላለው የሚያዘው አቋም ቅሬታ ሊያስነሳ እንደሚችል የዜናው ሰዎች ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

ለውጡን ባለመቀበልና ፣ ተቀብሎም በሙሉ ሃይል ወደተግባር ለመግባት ፈቃደኛ እንዳልሆነ ተደርጎ ጣት የሚቀሰርበት ህወሃት ” ጭራሽ አጀንዳ አይሆንም” በሚልበት ጉዳይ ላይ በድምጽ ብልጫ የሚወሰነውን ውሳኔ ምን እንደሚያስከትል ከወዲሁ በርግጠኛነት መናገር ግን አይቻልም።በሌላም በኩል የአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ መስመር መሰባበሩ ሰለማይቀር ጉባኤው መጨረሻው ምን እንደሚሆን ጉጉትን ፈጥሯል። 

የአፋር ክልል ላይ መሰረት አድርገው የሚሰሩ የተቀናቃኝ ፓርቲዎችም ከትግራይ ክልል ጋር የድንበርና የሃብት ጥያቄ አላቸው። ማእድናቸውንም ያለ አግባበ የመጠቀም ጉዳይ መኖሩንም እንደሚያነሱ ይታወሳል።

ይህ በንዲህ እንዳለ ሰሞኑንን በትግራይ ቲቪ ቃለ ምልልስ ያድረጉት የቀድሞው የኢንሳ ድይሬክተር የነበሩት ጀነራል፣ አሁን ባለው ሁኔታ ከሌሎች ጋር መቀጥል የማይቻልበት ደረጃ ተደርሷል። የትግራይ ህዝብና ህወሃት በኬሚስትሪ የተቀላልቀሉ ናቸው” ሲሉ አጠቃላይ ግንዛቤታቸውን ሲሰጡ ተሰምተዋል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   የአሜሪካ ሴናተሮች የኢትዮጵያ ምርጫ እንዲራዘም ያቀረቡት ጥሪ ብልህነት የጎደለው እጅግ አደገኛ ነው - ሎረንስ ፍሪማን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *