“በከሸፈ ስልት – ጘንዘባችሁን አትከሰክሱ ” አሉ። እጅግ ቁጭትና እልህ በተሞላበት አንደበት ድርጅታቸውና ጉባኤው መቁረጡን ሲገለጹ ” ድላችንን በደማችን እንዳገኘነው ሁሉ፣ ሰላማችንን በደማችን እንተብቀዋለን” በማለት የጉባኤውን ውሳኔ አተሙበት። ማተቡንም ለኢትዮጵያ ህዝብ ሲያበስሩ  ይህ ሁሉ የማተራመስ ሩጫ እንደማያብረከርክ፣ ድርጅታቸው በማይናወጥ የ፪፩ ኛው ክፍለ ዘምን ስሪት ሆኑ አገርን አስቦና አስተውሎ ወደመራት ደረጃ መሸጋገሩን በማረጋገጥ ነበር።

ቀደም ሲል ልጅ እያሱ ሞክረው እንደከሸፈባቸው፣ ከዛም መንግስቱ ሞክረው እነድከሸፈባቸው፣ እንደገናም በ፰፫/፰፬ ኢህአዴግ ሞክሮ እንደከሸፈበት ያስታወሱት ጀዝመኛው አብይ ” እኛ አንከሽፍም፤ ወደ ዴሞክራሲ የምናደረገው ጉዞ እንዳይከሽፍ ተደርጎ ተሰርቷል” ሲሉ እሳቸውን የማውረድ፣ ኦህዴድም አገር የምምራት ብቃት እንደሌለው ለማሳየት የሚደረገውን ርብርብና ስለመኖሩ የሚነገረውን አፍርጠውታል። ሁሉም የኦሮሞ ህዝብ ከወንድም የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በአንድነት ከማናቸውም አይነት የጥፋት ተግባር አግራቸውን እንዲታደጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ኦሮሞና ሶማሌን፣ ሲዳማና ወላይታን፣ አማራና ኦሮሞን ለመከፋፈል የተደረገው የከሰረ ሙከራ አለመሳካቱ ” ከሽፋችኋል” ሲሉ የገለጹት ዶክተር አብይ፣ “ሌላ አዲስ ስልት ይዛችሁ እስክትመጡ ድረስ ገንዘባችሁን አትከስክሱ ሲል ጉቤው ለጥፋት ሃይሎች መክሯችኋል” ሲሉ ነው አናንቀው መልዕክት ያስተላለፉት። በተደራጁ የሚዲያ ሰዎች የሚደረገውን የመከፋፈል ሃሳብና ሙከራ የሚነጥፍ እንደሆነም ተናግሯል። 

አዲሱ ፓርቲ ኦዴፓ ስያሜውን፣ አርማውን፣ ህገ ደንቡንና አደረጃጀቱን ፪፩ ኛው ክፍለ ዘመን የሚጠይቀውን አመራር መስጠት በሚያስችል መልኩ ያደራጀ መሆኑን  በመግለጽ፣ ሌሎች እህት ድርጅቶችም ከኦዴፓ ትምህርት እንደሚገባቸው አስታውቀዋል። አዲሱ ሀይል በግጭት ጊዜ ድንጋይ የሚወረውርና ደሙን የሚያፈስ ብቻ ሳይሆን አመራር መስጠት የሚችል መሆኑን በማመን ይህንንም በተግባር እንደሚያረጋግጡ እምነቴ ነው ብለዋል።

ፓርቲው 9ኛ ድርጅታዊ ጉባዔውን ማጠናቀቁን ተከትሎ የመዝጊያ ንግግራቸውን ቆፈጠን ብለው ያስተላለፉት አብይ አህመድ ንግግራቸው መጪው የኢህአዴግ ጉባኤ ከመቼውም ጊዜ በላይ የሚጠበቅ እንደሚሆን ፍንጭ የሚሰጥ ሆኗል። በደቡብ ክልል ያለው የሃዋሳ የክልልነት ጥያቄ ምላሽ በክልሉ ጉባኤ ይፋ እንደሚሆን ፣ ሌሎችም የዞንና የማንነት ጥያቄ ያነሱ በአግባቡ መልስ እንዲያገኙ በአብይ መሪነት መጠናቀቁ ተዳምሮ በደቡብ ክልል ካሁን በሁዋላ ሁከት እንደማይኖር ውስጥ አዋቂዎች የሊቀመንበሩን ንግግር ያጎላሉ። የሰሞኑ ትርምስም ይህንኑ ተከትሎ የተደረገ እንደሆነ ያምናሉ።

በዚህ ወቅት እንደገለፁት፥ ባለፉት ሶስት አመታት የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከነበሩ 81 አመራሮች በአሁኑ ጉባዔ በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት እንዲቀጥሉ የተወሰነው 16ቱ ብቻ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

በጉባዔው የኦሮሞ ህዝብ እንደ ባህሉ ለኢትዮጵያ ሰላም፣ ልማትና ግንባታ ሀላፊነት ያለበት መሆኑንና በተግባር ሰርቶ የሚያረጋግጥ መሆኑን ውይይት እንደተደረገበት አንስተዋል።

ፓርቲው በሀገሪቱና በክልሉ የሚፈጠሩ ችግሮችን ህግን በተከተለና በብልሃት እየፈታ እንደሚሄድ በመግለፅ ለውጡ በማንኛውም ሁኔታ ተቀልብሶ የሚቆም አለመሆኑን ጉባዔው ማረጋገጡን ተናግረዋል።

በተደራጀ መንገድ የተጀመረው የለውጥ ጉዞ በትናንሽ ሙከራዎች እንደማይደናቀፍና ለዚህ ተግባር ጊዜያቸውንና ገንዘባቸውን የሚያባክኑ አካላት ከተግባራቸው መቆጠብ እንዳለባቸው ሊቀመንበሩና አሳስበዋል።

እንዲሁም ኦሮሞና አማራን፣ ሲዳማና ወላይታን፣ ኦሮሞና ሶማሌና በሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች መከካከል መከፋፈልን ለመፍጠር መሞኮር የኢትዮጵያን ህዝቦች ታሪክ አለማወቅና የማይሳካ ድካም እንደሆነ ጠቁመዋል።

ጉባዔተኛው የኦሮሞ ህዝብ ከወንድምና እህት ህዝቦች ጋር በፍፁም ፍቅርና መከባበር ተካብሮ የተጀመረውን ሰላምና ልማት የሚያስቀጥል መሆኑን ያረጋገጠ ነው ብለዋል።

በተጨማሪም የዴሞክራሲው ጉዞው ከዚህ በፊት እንዳጋጠመው ተጀምሮ የሚከሽፍ አለመሆኑን ጉባዔው እንዳረጋገጠና ለዚህም የመፍትሄ አቅጣጫ መቀመጡን ሊቀመንበሩና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ገልፀዋል።

ከዚህ ባለፈ የኦዴፓ 9ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የጋሞ አባቶች የሰሩትን ገድል በታላቅ አድናቆት እንደሚመለከተው አስታውቀዋል። የጋሞ ሽማግሌዎች ተግባር ኢትዮጵያ አሁንም ሽማግሌ እንዳላትና ወጣቶችም ሽማግሌዎችን በማክበር ለባህላቸው አክብሮት እንዳላቸው ያሳዩበት መሆኑን ተናግረዋል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *