ገና ወደ ሃላፊነት ሲመጡ በተቃውሞ አስተያየቶች የታጀቡት ምክትል ከንቲባ በየደረጃው እየወሰዱ ያሉት እርምጃዎች ቀደም ሲል ተግባር ለናፈቃቸው ሁሉ አስገራሚ እየሆነ ነው። በተለይም አሁን በካቢኒያቸው ያሰውሰኑት የመሬት ጉዳይ ትልቁና ዋናው ሆኖ ተመዝግቦላቸዋል።

የኦዴፓ የለውጥ ሃይል የሆኑትና በተለያዩ መንገዶች የአዲስ አበባን ነዋሪ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የጠየቁት ከንቲባ ታከለ ከመሬት ጋር በተያያዘ የተለዩ ሆነዋል። አዲስ አበባን የመሩ ከንቲባዎች በሙሉ እያስጠኑና ውሳኔ ሳይሰጡ ለዓመታት የተኙበትን የታጠሩ መሬቶች ጉዳይ በአጭር ጊዜ እልባት መስጠታቸው አሁን በታየው ፍጥነት ይከናወናል ብሎ ያሰበ አልነበረም።

” እናልማለን” በሚል ከሊዝ ነጻ የከተማዋ እንብርት ላይ ሰፊ መሬት አጥረው የከተማውን ነዋሪ መተላለፊያ ከልክለው የኖሩ “ባለሃብቶች” ላይ እርምጃ መውሰድ አለመቻሉ እጅግ አነጋጋሪ ጉዳይ ነበር። አንዳንዶቹ ቲፎዞ ያላቸው ” ሃብታሞች” የመነጠቅ ጉዳይ ሲነሳ አፈር በማስቆፈርና በማጋጋዝ ቁማር ሲጫወቱ እንደኖሩ፣ ይህም የሚደረገው ከንቲባው አፍንጫ ስር እንደነበር ለሚያስታወሱ፣ የቀድሞዎቹ የከተማዋ አስተዳዳሪዎች ውሳኔ ለመስጠት አለመቻላቸው በተለያዩ ጊዜያት በቀዳሚነት በሪፖርተር ሲዘገብ መቆየቱ አይዘነጋም።

ይህንን ዝምታና ዳተኛነት የሰበሩት ታከለ ኡማ ካቢኒያቸው እጅግ የሚመሰገን ውሳኔ እንዲውስን አስችለዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በመዲናዋ ለዓመታት ታጥረው የተቀመጡ 4 ነጥብ 1 ሚሊየን ካሬ ሜትር መሬት ውል እንዲቋረጥ ወሰነ በዚህም

በግል ባለሀብቶች  የተያዙ 95 ቦታዎች፦  456,428 ካሬ  ሜትር

በመንግስት መስሪያ ቤቶች የተያዙ 19 ቦታዎች፦ 127,140.93 ካሬ ሜትር

የሸራተን ማስፋፊያን ጨምሮ በሚድሮክ ግሩፕ የተያዙ 11 ቦታዎች፦ 549,241.ካሬ ሜትር

በዲፕሎማቲክ ተቋዋማት የተያዙ 18 ቦታዎች፦  250,413.89  ካሬ ሜትር

በፌደራል ተቁዋማት መከላከያና ኢትዮ ቴሌኮምን ጨምሮ 11 ቦታዎች፦ 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ካሬ ሜትር

በአጠቃላይ 154 ቦታዎች በካሬ 4,126,423.83/ አራት ሚሊየን አንድ መቶ ሀያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሀያ አራት ካሬ የሊዝ ውላቸው ተቋርጦ ተመላሽ እንዲሆኑ ተወስኗል።

ቦታዎቹ ከ 1997 እስከ 2004 በተለዬዩ ጊዜያት የተላለፉና እስካሁን ምንም አይነት ልማት ሳይከናወንባቸው ታጥረው የተቀመጡ መሆናቸውን አስተዳደሩ አስታውቋል።

የካቢኔ ስብሰባውን የመሩት የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ እነዚህና መሰል ቦታዎች የከተማዋን ልማት እንዲጓተት ምክንያት እንደሆኑ ጠቅሰዋል። ይህ ስራ የአንድ ጊዜ ዘመቻ ሳይሆን ከዚህ በኋላ መስተዳድሩ ቦታ ወስደው ወደ ልማት የማይገቡ ማንኛውም የመንግስትም ሆነ የግል ባለሀብት ላይ ጥብቅ ክትትል አድርጎ እርምጃ እንደሚወስድ ነው ያስታወቁት።

በውሳኔው የሼክ አላሙዲ 13 ቦታዎች ተካተው እንዲነጠቁ መደረጉ ታውቋል። እሳቸው እስካሁን በእስር ላይ መሆናቸው ታውቋል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   የኮሚሽነር አበረ ህልፈት "በነጋዴዎች" እይታና ፤ የሃኪም ትክክለኛው መረጃ " ቸልተኛነት አይተናል"

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *