“Our true nationality is mankind.”H.G.

‹የጫት ፣ ሽሻ እና ሌሎች አደንዛዥ ዕፅ የሚያስጠቅሙ ቤቶች ይዘጉልን› የጎንደር ከተማ ወጣቶች

ባሕር ዳር፡መስከረም 14/2011 ዓ.ም(አብመድ) በጎንደር ከተማ ቀበሌ 13 ነዋሪ የሆኑ ታዳጊ ወጣቶች በአካባቢው የአደንዛዥ እፅ የሚያስጠቅሙ ግለሰቦች በመበራከታቸው ስጋት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል፡፡
በአካባቢው እንደ ሽሻ ፣ጫት እና ሌሎች አደንዛዥ እፅ ማስጠቀሚያ ቤቶች በመበራከታቸው ተደጋጋሚ የሆነ ወንጀል እየተፈፀመብን ነው ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

ከ50 በላይ የሚሆኑ ወጣቶች በጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ.ቤት ተገኝተው ህገ-ወጥ አስጠቃሚዎች እና የቤት አከራዮች በህግ እንዲጠየቁላቸው አሳስበዋል፡፡
ከየት አካባቢ እንደመጡ የማይታወቁ አደንዛዥ እፅ ተጠቃሚዎች በአካባቢው ሰዎች የእለት ከእለት ስራ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያስከተሉ መሆናቸው ተጠቆሟል፡፡
ከአሁን በፊት የሰው ህይወት እንዲያልፍ ያደረጉ እና በቅረቡም በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ የአካል ጉዳት ማድረሳቸውም ተገልጧል፡፡

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የወንጅል መከላከል የስራ ሂደት ኮማንደር አያና ሹምየ በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ የቀረበው ቅሬታ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ወንጀሉ ሊቆም ያልቻለው አደንዛዥ እፆቹን የሚያስጠቅሙ የቤት አከራይ ግለሰቦች ቁጥር በመበራከቱ ነው ተብሏል፡፡

ምንም እንኳን ድርጊቱን ማስቆም ባይቻልም በዚህ ተግባር ተሳትፈው በማስረጃ ክስ ቀርቦባቸው ቅጣት የተላለፈባቸው ሰዎች እንደነበሩ ተናግረዋል፡፡

በገንዘብ ከተቀጡ ወንጀለኞች 129 ሺህ ብር ቅጣት ተጥሎ እንደነበር ኮማንደሩ አስታውሰዋል፡፡ ወጣቶቹ ግን ዛሬም ትኩረት ያልተሰጠው ይህ ህገ- ወጥ ድርጊት መፍትሄ እንዲያገኝ አበክረው ይሻሉ፡፡

ዘጋቢ፡-ሀይሉ ማሞ

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   የትግራይ ክልል ባቀረበው ፍላጎት መሠረት የአፈር ማዳበሪያ መቶ በመቶ እንዲቀርብ መደረጉ ተገለጸ
0Shares
0