የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በመንግሥታቱ ድርጅት ሰባ ሦስተኛ ጉባዔ መክፈቻ ወቅት አይገኙም። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ ኒውዮርክ ገብተዋል። 

በዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የተመራ ልዑካን ኒው ዮርክ ቢገኝም የጠ/ሚኒስትሩ ጉባዔው ላይ ጭራሹኑ ስላለመገኘታቸው በይፋ ከመንግስት የተሰጠ መግለጫም ሆነ ማብራሪያ የለም። ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለጉባኤው ንግግር የሚያደርጉበት መርሃ ግብር ይፋ ሆኖ ነበር። 

ዶ/ር ወርቅነህ ከጠቅላላ ጉባኤው ጎን ለጎን ከመንግስታቱ ድርጅት ከፍተኛ ባለስልጣናት የተናጠል ውይይት እንደሚያደርጉ የመንግስት ሚዲያዎች አስታውቀዋል።

73ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከመስከረም 8 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በኒውዮርክ እየተካሄደ ነው። ስብሰባው “የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ለሁሉም ህዝቦች ጠቃሚ ማድረግ ፣ ለዓለም ሠላም፣ እኩልነት እና ዘላቂ ተጠቃሚኒት የመሪነት ሚና ይጫወት” በሚል መሪ ቃል ነው የሚካሄደው። 

ይህ ጉባኤ አገራችን የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል በሆነችበት ወቅት ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄድ የመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Related stories   A call from Dr Dawit Wondimagegn "to strike for a health professional is to aim.. to shoot, And kill."

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *