በ Seyoum Teshome 
አሁን ባለው የኢትዮጲያ ፖለቲካዊ ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ግራ-መጋባት ይታየኛል። ግራ መጋባቱ በዋናነት “ሀገሪቱ ወደየት እያመራች ነው?” በሚለው ጥያቄ ላይ የተመሰረተ ነው። ይህ ግራ መጋባት ታዲያ በአንዱ ወይም በሌላኛው ወገን ላይ ሳይሆን በሁሉም ወገኖች ላይ የሚስተዋል ነው። የገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች እና ደጋፊዎች፣ በብሔርተኝነት እና በአንድነት ጎራ በተሰለፉት ተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎችና ደጋፊዎች ላይ በግልፅ ይስተዋላል። በዚህ ፅሁፍ ከሦስቱም ጎራዎች አንዳንድ ምሳሌዎች በመጥቀስ ግራ መጋባቱን ለማሳየት እንሞክራለን። ከዚያ በቀጠል ደግሞ “ሀገራችን ወደየት እያመራች ነው?” የሚለውን ጥያቄ ከሌሎች ሀገራት ታሪክና ፖለቲካዊ ክስተት ጋር በማያያዝ ምላሽ ለመስጠት እንሞክራለን። 
የመጀመሪያው ግራ መጋባት የህወሓት/ኢህአዴግ መስራች እና ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ አባይ ፀሐዬ በኢትዮጲያ ፌደራሊዝም ስርዓትን አስመልክቶ የሰጡት አስተያየት ነው። እንደ እሳቸው አገላለፅ፣ በዩጎዝላቪያ (Yugoslavia) የነበረው የፌደራሊዝም ስርዓት የወደቀው በአንድ ብሔር (the Serbs) የበላይነት ላይ የተመሰረተና ሌሎችን ብሔሮች ያገለለ በመሆኑ ነው። ከዚህ በተጨማሪ፣ የሶቭዬት ፌዴሬሽን (Soviet federation) የተበታተነው ደግሞ በስርዓቱ ጨቋኝነት እና በዴሞክራሲ እጦት እንደሆነ ገልፀዋል። 
“አዎ…የህወሓት/ትግራይ የበላይነት አለ’ በሚል ርዕስ ባወጣሁት ፅሁፍ በዝርዝር ለማብራራት እንደሞከርኩት አሁን ባለው ፖለቲካዊ ስርዓት ላይ የህወሓት/ትግራይ የበላይነት በግልፅ የሚታይ ሃቅ ነው። በሌላ በኩል፣ የኢህአዴግ መንግስት በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች ከሕዝብ ለሚነሱ የነፃነት፥ እኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በኃይል ለማፈን ጥረት እያደረገ ነው። በዚህ ምክንያት፣ የኢህአዴግ መንግስት ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ ጨቋኝና አምባገነን እየሆነ መጥቷል። ነገር ግን፣ የመንግስታዊ ስርዓቱ መስራችና ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ አባይ ፀሐዬ “ዩጎዝላቪያና ሶቬት ሕብረት የፈረሱት አሁን የኢህአዴግ መንግስት እየፈፀመ ያለውን ስህተት በመፈፀማቸው ነው” ማለታቸው በኢህአዴግ ውስጥ ያለውን ግራ መጋባት ያሳያል። 
ከላይ በተጠቀሰው የአቶ አባይ ፀሐዬ አስተያየት ግራ የተጋባው አንድ የኦሮሞ ብሔርተኛ ወዳጄ “ይሄ ነገር ‘ኣላዋቂነት’ ወይስ ‘ንቀት’ ነው?” በማለት ጠየቀኝ። በእርግጥ እንደ አባይ ፀሐዬ ያሉ አንጋፋ ፖለቲከኞች “አላዋቂ ናቸው” እንዳይባል ሀገሪቱ የምትመራበትን ፖለቲካዊ ስርዓት መዘርጋት የቻሉ ናቸው። አይ…ነገረ ስራቸው ሁሉ “ንቀት ነው” እንዳይባል ደግሞ በንቀት ራሳቸውን ለውድቀት አይዳርጉም። ምክንያቱም፣ የዩጎዝላቪያና ሶቬት ህብረት የወደቁበትን መሰረታዊ ምክንያት እያወሱ ተመሳሳይ ስህተት ይፈፅማሉ ብሎ ማሰብ ይከብዳል። 
ሦስተኛውን ግራ መጋባት የታዘብኩት ደግሞ የአንድነት አቀንቃኝ በሆነው ወዳጄ ላይ ነው። ከዚህ ጓደኛዬ ጋር ከረጅም አመታት በኋላ ታክሲ ውስጥ ተገናኘንና እንዲህ ሲል ጠየቀኝ፡- “የኢህአዴግ መንግስት አሁን ካለንበት የፖለቲካ ቀውስ ላይ ያደረሰን አውቆና አቅዶ ነው ወይስ ሳያውቅ በስህተት ነው?” በእርግጥ አውቆና አቅዶ ሀገሪቱን አሁን ካለችበት ደረጃ ላይ ማድረስ በጣም ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ዕዉቀት ይጠይቃል። ነገር ግን፣ ሀገርና ሕዝብን ለፖለቲካ ቀውስና ውድቀት የሚዳርግ አሻጥር ክፋት እንጂ ዕውቀት ሊባል አይችልም። በሌላ በኩል ደግሞ “ሳያውቁ በስህተት የፈፀሙት ነው” እንዳይባል ደግሞ ስህተታቸውን የነገሯቸውን የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ጦማሪያን፣ የመብት ተሟጋቾች፣ …ወዘተ ለእስርና ስደት ዳርገዋቸዋል። 
ሙሉ ጽሁፉን ለማንበብ ተከታዩን ሊንክ ይጫኑ
https://ethiothinkthank.com/…/ethiopia-heading-into-confli…/

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   የአውሮፓ ህብረት የይስሙላ ምርጫዎች ሲታዘብ ቆይቶ አሁን አልታዘብም ያለበትን ምክንያት ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያሳውቅ ተጠየቀ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *