የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ 10ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ በሀዋሳ ከተማ መካሄድ ጀምሯል። በዛሬው እለት የተጀምረው 10ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ እስከ መስከረም 21 2011 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድም ድርጅቱ አስታውቋል።

በድርጅታዊ ጉባዔው ላይ በሀገሪቱ ያለውን የለውጥ ጉዞ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያስችል ውሳኔዎች እንደሚተላለፉበትም ደኢህዴን ገልጿል።

እንዲሁም ሀገራዊ ለውጡን በብቃት እንዲሳካ ማድረግ፣ የንቅናቄው የቀደሙ ጉባኤዎች ውሳኔዎች አፈፃፀምም በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥም የጉባዔው አጀንዳዎች ናቸው።

ደኢህዴን ያስጠናቸው የለውጥ መሠረታዊ እቅዶች ላይ ምክክር የሚደረግ ሲሆን፥ በፖርቲ ግንባታ ጥናት ስር የአርማ የስያሜና የህገ ደንብ ጉዳዮች ላይ ጉባሄው ይወያያል ነው ያሉት።

በተጨማሪም በድርጅታዊ ጉባዔው የንቅናቄውን ሊቀ መንበርና ምክትል ሊቀመንበር እንዲሁም የማእከላዊ ኮሚቴ እና የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫም ይካሄዳል።

በ10ኛ ድርጅታዊ ጉባሄ ላይ ከ1 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የሚታደሙ ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 800 በድምፅ እንደሚሳተፉም ተገልጿል

 (ኤፍ.ቢ.ሲ)

Related stories   የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዑስማን ሳልህ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *