በተደጋጋሚ የፈለገውን ማድረግ እንደሚችልና እሱ በሚመራው ሃይል ኦሮሚያን ማስገንጠል ቀላል እንደሆነ የሚናገረው ጃዋር መሐመድ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ላይ የተፈጸመውን የግድያ ሙከራ አስመልክቶ አቃቤ ህግ ይፋ ያደረገውን ክስ ተከትሎ ጥያቄ አነሳ። በግል የፌስ ቡክ ገጹ ጥያቄ ከማቅረቡ ጥያቄው ካልተመለሰ ስለሚወስደው ቀጣይ ርምጃ ያለው ነገር የለም።

በጽንፈኛነቱ የሚታወቀው ጃዋር መሐመድ በግል የፌስ ቡክ ገጹ እንዳለው በመንግስት በኩል የግድያ ሙከራው በቀድሞ የድህንነት ሰዎች መቀነባበሩ በተደጋጋሚ መነገሩን አመልክቷል። ዛሬ ይፋ በሆነው ክስና የክስ ጭብጥ ላይ ዋና አቀናባሪ ተብሎ ሲጠቀስ የነበረው ተስፋዬ ኡርጌ አለመካተቱን ነው የነቀፈው።

Related stories   ምርጫውን ለማደናቀፍ ያሴሩ አካላት ህልማቸው አይሳካም – አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

ጃዋር ይህንን ጥያቄ ያነሳው አቃቤ ህግ የግደያ ሙከራውን ያቀነባበሩትና ለመተግበር ሙከራ ያደረጉት ተጠርጣሪዎች ኦነግ እንዲነግስና አገር እንዲመራ ከተያዘ ዓላማ በመነሳት ስለመሆኑ አላብራራም። በኦሮሚያም ሆነ በመላው አገሪቱ በሚባል ደረጃ ተቀባይነት ያላቸው ዶክተር አብይ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንደሌላቸው ጠቅሶ አቃቤ ህግ የመሰረተው ክስ አሁን እየተካሄደ ካለው የከረረ ፖለቲካ ጋር ለበርካቶች ትርጉም ሰጥቷል። ይሁን እንጂ በግልጽ ባልተቀመጠ ምክንያት ነው ጃዋር ጥያቄውን ያነሳው።

2018-09-28-2.png

ከጃዋር መሐመድ ፌስ ቡክ ቃል በቃል የተወሰደ

የሰኔ 16ቱ የቦምብ ፍንዳታ የመራው ተስፋዬ ኡርጌ ለምን አልተከሰሰም? ፖሊስ ከዚህ በፊት ጥቃቱን በዋናነት ያቀነባበረው በድሀነንት መስሪያ ቤት የጸረሽብር ግብረሀይል ሃላፊ የነበረው ተስፋዬ ኡርጌ ነው ብሎ ከሶ ነበር። አቶ ተስፋዬ ከዚህኛው ፍንዳታ ውጪ ላለፉት 27 አመታት ብዙ የሽብር ጥቃቶችን አስፈጽሞ ተቃዋማውን ለመወንጀል ይጠቀም እንደነበር፤ ይህንንም ኦፕሬሽን ብጌታቸው አሰፋ ትዛዝ ሲያስፈጽም እንደነበር ነው የተነገረው። ባጠቃላይ የሰኔ 16ቱ የቦምብ ፍንዳታ በቀድሞ የድህንነት ሰዎች የተቀነባበረ እንደነበር ነው በመንግስት በኩል ሲቀርብ የነበረው። ታዲያ ዛሬስ ከክሱ ውስጥ ይህ ዋና አቀነባባሪው ተስፋዬ ኡርጌ ለምን ቀረ?

ለወትሮው ጥያቄ ሲያቀርብ ቀነ ገድብ የሚያስቀምጠው፣ ሲያሻውም የተቃውሞ ጥሪ የሚያቀርበው ጃዋር አሁን ላነሳው ጥያቄ ወደፊት ስለሚወስደው ርምጃ ወይም አቋም ምንም አላለም። አቃቤ ህግ በራሱ አካሄድ ምርመራውን እንዳጠናቀቀ በተስፋዬ ላይ ክስ እንደሚመሰርት አስቀድሞ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ በጠየቀበት ወቅት ይፋ አድርጎ ሳለ፣ ጃዋር ይህንን ጥያቄ ማንሳቱ ከዜናው ጋር ተጨማሪ መነጋገሪያ ይሆናል ተብሎ ይገመታል። ኦነግ ይህንን አስመልክቶ እሳካሁን ያለው ነገር የለም። ሆኖም የጃዋር አካሄድ ዶክተር አብይ ላይ ጣት የማስቀሰር እንደሆነ ግምታቸውን የሰጡ አሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *