“Our true nationality is mankind.”H.G.

በአዲስ አበባ ከተማ ታግዶ የቆየው የመሬት መስተንግዶ ተጀመረ

ሪፖርተር ፡  ውድነህ ዘነበ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ሥልጣን በተረከቡ ማግሥት፣ የመሬት ኦዲት እስኪካሄድ የመሬትና መሬት ነክ መስተንግዶ እንዳይሰጥ አግደው ነበር፡፡

በዚህ መሠረት የኢንዱስትሪ አልሚዎች የመሬት ጥያቄ፣ የሰነድ አልባና አግባብ ባለው አካል ሳይፈቀድ በወረራ የተያዙ ቦታዎች መስተንግዶ፣

መሬት ያልተረከቡ የመኖሪያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበራት መስተንግዶ፣ እንዲሁም ምክትል ከንቲባው ሥልጣን ከመረከባቸው በፊት ወጥቶ የነበረው 30ኛው የሊዝ ጨረታ ታግደው ቆይተዋል፡፡

ምክትል ከንቲባው የመሬት ኦዲት በማዕከልም ሆነ በክፍለ ከተማ ከተጠናቀቀ በኋላ፣ ሰኞ መስከረም 14 ቀን 2011 ዓ.ም. አሥሩም ክፍላተ ከተሞች መስተንግዶ እንዲጀምሩ መመርያ ሰጥተዋል፡፡

የቦሌ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም ኢቲቻ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ በመመርያው መሠረት ከሰኞ ጀምሮ የመሬትና መሬት ነክ መስተንግዶ አገልግሎት ጀምሯል፡፡

‹‹ነገር ግን ኅብረተሰቡ ባለመስማቱ ሊሆን ይችላል፣ በሳምንቱ መጀመርያ አገልግሎት ለማግኘት እምብዛም አልመጣም፡፡ ክፍለ ከተማው አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ ኅብረተሰብ መስተናገድ ይችላል፤›› ሲሉ አቶ ፍፁም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አቶ ፍፁም ጨምረው እንደገለጹት፣ በማዕከል ከተካሄደው የመሬት ኦዲት በተጨማሪ በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚካሄደው ኦዲትም ተጠናቋል፡፡ ‹‹የኦዲት ግኝቱን በቅርቡ ለኅብረተሰብ ይፋ እናደርጋለን፤›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤
0Shares
0