“Our true nationality is mankind.”H.G.

በረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ /ጥንቅሹ ይከሰሳሉ፤ በክብር አልተሸኙም

የአማራ ክልል ገዢ ፓርቲ አዴፓ፣ የቀድሞዎቹን ባለስልጣናት አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ጥንቅሹ ላይ ክስ ለመመስረት የሚያስችል መረጃ አሰባስቦ መጨረሱ ተሰማ። ፓርቲው በርካቶችን በክብር መሸኘቱን ይፋ ሲያደርግ ሁለቱን ያላካተተው በዚሁ ምክንያት እንደሆነ ስለጉዳይ እናውቃለን የሚሉ ለዛጎል ተናግረዋል። 

ሁለቱ ጉምቱ ባለስልጣኖች ከድርጅት ሃላፊነታቸው መታገዳቸውን ተከትሎ በተለያዩ ሚዲያዎች ቅሬታቸውንና የህግ ተጣሰ ተቃውሟቸውን ማቅረባቸው አይዘነጋም። ይህንኑ ተቃውሟቸውን ተከትሎ አቶ ንጉሱ ጥላሁን መልስ በሰጡበት ወቅት እገዳው ፖለቲካዊ ውሳኔ መሆኑንን ተናግረው ነበር። 

እገዳው የድርጅታቸውን ህግና ደንብ የተከተለ መሆኑንን በማስረዳት ያጣጣሉት አቶ ንጉሱ ከጥረት ኢንተርፕራይዝ ጋር በተያያዘ ክስ የሚያስመረቱ ጉዳዮች እንዳሉ ጠቁመው፣ ይህንን ተግባራዊ የሚያደርገው የአስተዳደር አካሉ የሚሄድበት ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበው ነበር።

በአዴፓ ጉባኤ ይህ ጉዳይ ተነስቶ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው ጥረት ኮርፖሬሽን 11 ቢሊዮን አለው የተባለው ውሸት መሆኑንን አመልክተዋል። “ያገኘሁት ካፒታል 5.1 ቢሊዮን ብር ብቻ ነው። ጥቁር አባይ ትራንስፖርት 500 ተሽከርካሪ አለው እየተባለ የነበረው የለም ያለው 340 መኪና ብቻ ነው።ከዚህ ውስጥ የሚሰሩት 48 መኪኖች ብቻ ናቸው ” ሲሉ ተናግረዋል።

በጥረት ካምፓኒ የሰባት ኘሮጀክቶች ሀብት ባክኗል። ከ2008 – 2010 ግማሽ ዓመት ብቻ 347 ሚሊዮን ብር ኪሳራ መድረሱን  ከጉዳዩ ጋር  ቀጥያ ግንኙነት ያላቸው ጉባኤተኛ  ማስረዳታቸው ታውቋል። በዚህም በቀጥታ አቶ ታደሰ ጥንቅሹ የጥረት ስራ አስኪያጅ በመሆናቸውና አቶ በረከት በበላይ አመራርነታቸው ተጥያቂ እንደሚሆኑ ነው ለማወቅ የተቻለው።

ይህ የመጠየቅ ጉዳይ ከኢህአዴግ ጉባኤ በሁዋላ በይፋ በተለያዩ ከፍጠኛ ፕሮጀክት ሃላፊዎች ተግባራዊ እንደሚሆን ይጠበቃል። አሁን ያለው ለውጡን ተከትሎ የተነሱ ግርግርሮችና ሰው ሰራሽ መፈናቀሎች ሲሰክኑ ቀጣዩ ተግባር ይህ እንደሚሆን ግምታቸውን የሚሰጡ ጥቂት አይደሉም።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ኤፒ ለቅጥፈቱ ይቅርታ አልጠየቀም – ምርጫ ተራዘመ፤ለምን?
0Shares
0