“Our true nationality is mankind.”H.G.

እነ ዶክተር ኮንቴ ከአፋር ክልል በሃይ ተባረሩ፣ ” ከቆያችሁ ለህይወታችሁ አደገኛ ነው ተብለን ህዝብ ሳናገኘ ለቀን ወጣን”

ሙሉ በሙሉ ያልተደመች ክልል እንደሆነች በሚነገርላት የአፋር ክልል በፌደራል መንግስትና በኢህአዴግ ደረጃ በተደረገ ጥሪ ወደ አገር ቤት የተመለሱትን የአፋር ሕዝብ ፓርቲ አመራሮች ከሕዝብ ጋር ሳይገናኙ እንዲባረሩ መደረጉ ታወቀ። የክልሉ አመራሮች ከህወሃት ጋር ከፍተኛ ቁርኝት እንዳለውም ዜናውን የላኩት አመልክተዋል።

የፓርቲው መሪ ዶክተር ኮንቴ ሙሳ የሚመሩት የልዑክ ቡድን ወደ አፋር ከተማ ያመራው ከክልሉ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ተነጋግሮ፣ ቀጠሮ ይዞና ቀን ቆርጦ ነበር። በስምምነታቸው መሰረት ወደ ክልሉ እንዳመሩ ግን የገጠማቸው ያልተጠበቀ ሆነ። ምክንያቱ በግልጽ በማይታወቅ ሁኔታ አስቀድመው ፈቃድ የሰጡትና የተስማሙት ባለስልጣናት እሳት ጎርሰው በመጡበት እንዲመለሱ አደረጓቸው።

በክልሉ የለውጥ ያለህ የሚሉትን ወጣቶች እንደሚያስተባበሩ የተናገሩ እንዳሉት የእነ ዶክተር ኮንቴ አፋር ክልል መገኘት በጥብቅ የሚፈለግና የሚጠበቅ ጉዳይ ነበር። 

በመልካም አስተዳደር፣ በሙስናና በአቅም ማነስ የክልሉን ህዝብ በወጉ እንደማይመሩ በተደጋጋሚ ተቃውሞ የሚሰነዘርባቸው የክልሉ አመራሮች ሃሳባቸውን ለምን እንደቀየሩ በዝርዝር አላስታወቁም። የልዑክ ቡድኑ አፋር ከገባ በሁዋላ ” በአስቸኳይ ክልሉን ለቃቹህ ካልወጣቹህ ለህይወታችሁ ተጠያቂ አይደለንም” በማለት ነው ያበረሩዋቸው።

ዝርዝር ጉዳዩን ባያብራሩም ከውስጥ ከፍተኛ ግፌት ያለበት የክልሉ መንግስት ሃሳቡን ቀይሮ እንግዶቹን ለማባረር የወሰነው በሌሎች ጫና ነው። እንደ ዜናው ምንጮች ከሆነ አሁን በስልጣን ላይ ያለው የአፋር ክልል ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ከህወሃት ጋር የጠበቀ ግንኙነት አለው። 

በአገሪቱ የተጀመረውን ለውጥ ተከትሎ ኢህአዴግ የሚፈርስ ከሆነ ህወሃት አፋር፣ቤኒሻንጉል፣ ጋምቤላና የሶማሌ ክልልን በአንድ ላይ የማደራጀት ዓላማ እንዳለው በተደጋጋሚ በህወሃት ደጋፊዎች ዘንድ የሚገለጽ ጉዳይ ነው። በሶማሌ ክልል ሙሉ በሙሉ ነገሮች ተቀይረው ክልሉ በለውጥ ሂደት ውስጥ እንደሆነ፣ ለውጡም በክልሉ አዲስ አመራር እንዲሰየም ማድረጉ፣ አዲሱ አመራርም ከዶከተር አብይ የተሃድሶ ለውጥ ጋር እንደሚሰራ ማረጋገጡ አይዘነጋም። 

የጋምቤላ ክልል ህዝብ ለውጥ ፈላጊ መሆኑንን በተደጋጋሚ በሰላማዊ ሰልፍና በሚችለው ሁሉ እየጠየቀና መስዋዕትም እየሆነ ይገኛል። ለክልሉ ፖለቲካ ቅርብ የሆኑ እነደሚሉት የጋምቤላ የመደመር ጉዳይ የቀናት ወይም የሳምንታት ጉዳይ ነው። የቤኒሻንጉል ጉዳይ በውል ያልለየለት ቢሆንም ከኢህአዴግ ጉባኤ በሁዋላ የማያዳግም መፍትሄ እንደሚፈለግለት ምንጮች ያስረዳሉ። አሁን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ለውጡ ጎራ ያላለበት የአፋር ክልል በሕዝብ ተቀባይ የሆኑትን የአፋር ንጉስ ልጅና የዶክተር ኮንቴን ፓርቲ እስከመቼ እንደሚይገል ባይታወቅም ልክ እንደ ሶማሌ ክልል ሁሉ በጥንቃቄ መፍትሄ እነድሚበጅለት እነዚሁ ክፍሎች አመልክተዋል።

በከፍተኛ ማስፈራራት ከአፋር ክልል ስለተባረሩት ወገኖች የፌደራል መንግስት ያለው ነገር የለም።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤
0Shares
0