የአዲስ አበባ አስተዳደር ለረዥም ዓመታት መሬት አጥረው በያዙ የመንግስት ተቋማትና የግል ” ባለሃብቶች” ላይ ጥናት አካሂዶ ባሳለፈው  ውሳኔ መሰረት መሬት ነጠቀ። ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ጉዳዩ የሞራል ጉዳይ አንደሆነ ተናገረዋል።

” ስም አልጠራም” ካሉ በሁዋላ መሬት አጥረው ለረዥም ዓመታት የያዙትን ሁሉ ” ሞራል የላቸውም” ሲሉ የወቀሱት ከንቲባው እርምጃውን ለመውሰድ ሲታሰብ በርካታ ችግር እንደነበር፣ በቡድን ለመስራት የመፍራት አዝማሚያዎች መታየታቸውን፣ በተለይም ውለታ አለብን የሚሉ ምክንያቶች ከቅርብ ሰዎች ይቀርቡ እንደነበር አመልክተዋል።

ይህንን ካስታወሱ በሁዋላ ” ማንም ሆነ ማን” በማለት ለረዥም ዓመታት መሬት አጥረው ባላለሙት ላይ የተወሰደው እርምጃ የማይታጠፍ መሆኑንን ነው ያመለከቱት። መከላከያ የሚወደድ የአገራችን ተቋም መሆኑንን ጠቁመው፣ ግን የወሰደውን መሬት ካላለማ መንግስት ነኝ ማለቱን ሊያቆም ይገባል ሲሉ ወቅሰዋል። ቴሌንም በተመሳሳይ አንስተዋል።

Related stories   ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ200 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ

ከመስክ ጉብኝቱ በሁዋላ ባደረጉት አጭር ንግግር ከንቲባው እንዳሉት ” ውለታ” በሚል ለተነሳው  ውለታ መልካም መሆኑን ተናግረው። ግን ይህንን እርምጃ ከመውሰደና ህግና ስርዓትን ከማስጠበቅ ወደሁዋላ እንደማያደርግ ነው ያመለከቱት። ለሚያደምጡዋቸው ” ጉዳዩ የሞራል ነው” ሲሉ ክፉኛ የተቹት አቶ ታከለ ኡማ፣ ሞራል የሌላቸው ሲሉ በተደጋጋሚ ባለሃብቶቹን አርግፈዋቸዋል።

ከሳቸው ቀጥለው የተናገሩ አንዳሉት በጉብኝቱ ላይ ባዩት ማዘናቸውን አመላክተዋል። እኚህ ሰው ፒያሳ ከንቲባው ቢሮ አፍንጫ ስር ከአስራ ሰባት ዓመት በላይ የታጠረውን መሬት በሰጡት አስተያየት ” ትልልቅ የሚባሉ” ሲሉ የጠቀሷቸውን ሰዎች አቅለዋቸዋል። እሳቸው እንዳሉት ” ትልልቅ” ያሉዋቸው ሰዎች ” እየሰራን ነው ውጡልን” በሚል አልሚ መስለው ለመታየት መሞከራቸውን ቀደም ሲል ከንቲባው ካነሱት የሞራል ጉዳይ ጋር አያይዘዋል። አስተዳደሩ እንዲህ ያሉትን ከቶውንም መስማት እንዲያቆም ተማጽነዋል።

Related stories   አቡነ ማቲያስ መነጋገሪያ ሆነዋል - ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻው እንዲከር ጥሪ አቅርበዋል

አንድ አፍታ የተሰኘው ሚዲያ በዩቲዩብ እንዳሰራጨው አቶ ታከለ እነዚህ ሰዎች ዳግም ለማልማት ቢፈልጉ እንኳን መልሶ መሬቱን መስጠት የማይታሰብና የሞራል ጉዳይ መሆኑን አመልክተዋል።

የተለያዩ የውጭ ሚዲያዎች በገጻቸው በእስር ላይ ያሉት ሼኽ መሀመድ ሁሴን አላሙዲ በኢትዮጵያ የነበሯቸውን መሬቶች ማጣታቸውን ሰፊ ሽፋን ሰጥተው ዘግበዋል።

አቶ አርከበ እቁባይ ፒያሳ ለዓመታት ታጥሮ የተያዘው ቦታ ከሊዝ ነጻ በሳቸው ትዕዛዝ ለሼኽ መሐመድ መሰጠቱን ለሪፖርተር መናገራቸው የሚታወስ ነው። በወቅቱ እሳቸው ይህንን ያሉት ቦታውን አስመልክቶ ሚድሮክ ግንባታ ለመጓተቱ የሰጠውን የተጭበረበረ ምክንያትና ችግሩን በከተማዋ አስተዳደር ላይ ባላከከበት ወቅት ነበር። አቶ አርከበ ለሪፖርተር ደውለው በሰጡት መረጃ መሰረት የፒያሳው መሬት ከሊዝ ክፍያ ነጻ የተሰጠና ያለክፍያ ተወስዶ የታጠረ መሬት መሆኑ በውቅቱ ይፋ ሲሆን በነጻ ባለቤት የሆኑት ሰውም ሆኑ ሰራተኞቻቸው አላስተባበሉም። አቶ አርከበ በወቅውቱ ከዚህ በላይ የሚሄዱ ከሆነ ዶክመንቱን አቀርባለሁ። ይፋ አደርጋለሁ ብለውም ነበር።

Related stories   የኮሚሽነር አበረ ህልፈት "በነጋዴዎች" እይታና ፤ የሃኪም ትክክለኛው መረጃ " ቸልተኛነት አይተናል"

ከአቶ አርከበ በሁዋላ አዲስ አበባን የመሯት ከንቲባዎች የተኙበትን ጉዳይ አቶ ታከለ ኡማ በአጭር ጊዜ ውስጥ እርምጃ መውሰዳቸው አድናቆትን አስችሯቸዋል። አቶ ታከለ ውሳኔው ተመርምሮና ተጠንቶ የተሰራ በመሆኑ ምንም ችግር እንደማያስከትል፣ በቀጣይ በሁለተኛን በሶስተኛ ደረጃ የተከፈለ ስራ እንደሚሰራ ይፋ አድርገዋል።

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *