ኤርትራ መሽገው የነበሩትና በቅርቡ ወደ አገር ቤት የገቡት የኦነግ አንድ ክንፍ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከድርጅት መሪነታቸው እንዲለቁ ቄሮ ንቅናቄ መጀመሩ ተሰማ። የዛጎል መረጃ አቀባዮች እንዳሉት ዳውድ ኢብሳ ዙሪያቸው ባልጠሩ የተለያዩ ጉዳዮች የተተበተበ መሆኑም እንዳሰቡት ድርጅቱን እየመሩ ለመቆየት ይቸገራሉ።

በባህላዊው የኦሮሞ ገዳ ደንብ መሰረት አቶ ዳውድ ስምንቱን ዓመት ካጠናቀቁ ቆይቷል። በእድሜያቸውም ቢሆን ሰፊ ህዝብ የሚወክል አንድ ተፎካካሪ ድርጅትን በብቃት ለመምራት በሚያስችለው ደረጃ ላይ አይደሉም። በሚደግፏቸው የወለጋና አካባቢው ቄሮዎች ዘንድ በርካታ ጥያቄ የሚነሳባቸው አቶ ዳውድ ኢብሳ ከሁለቱ ማለትም አባ ነገኣ /ጀነራል ሃይሉ ጎንፋና በዙም ድምጻቸው ከማይሰማው ገላሳ ዲልቦ ኦነግ ጋር ስምምነት ላይ ባለመድረሳቸው ትክክለኛው የኦነግ ባለቤት ለመሆንም እንደሚቸገሩ ነው።

እሳቸው የሚመሩት ኦነግ የስራ አስፈጻሚ አመራሮች ከአንድ የትውልድ ቀዬና አካባቢ መሆኑም ሌላ ችግር መሆኑንን የሚያነሱት የዜናው ምንጮች፣ አቶ ዳውድ በሀረርጌ፣ በአርሲ፣ በባሌ፣ በምስራቅ ሸዋ፣ በምዕራብ ሸዋ ተቀባይነታቸው መመናመኑን ይናጋራሉ። “ተቀባይነት ከሌላቸው በአቀባበል ስነ ስርዓት ላይ እንዴት ቁጥሩ ከፈተኛ የሆነ ህዝብ ተገኘ ” በሚል ለቀረበላቸው  ጥያቄ ሲመልሱ ” እሱ አዲስ አበባ ላይ ካለው ፖለቲካ የሚነሳ እንጂ ሌላ ትርጉም የለውም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ጉዳዩን ትልቅ ያደረገው አቶ ለማ መገርሳና ወርቅነህ ገበየሁ አስመራ ሄደው መደርደራቸው ነው።

ዛጎል በዚሁ ጉዳይ ያዘጋጀውን ሙሉ ሃተታ በሳምንቱ መጨረሻ ያትማል

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *