“Our true nationality is mankind.”H.G.

“ብሮድካስት ባለስልጣን ለኤል ቲቪ ማስጠንቀቂያ ሰጠ” ቤተልሄም፤ ” ማስጠንቀቂያ እልተሰጠንም ” ድርጅቱ

“ደግነቱ  ሲጀመር በቀይ ነዶ እየተምዘገዘገ ወደ ጆሮና አይን የሚመጣው ትንታጉ የሃርድ  ቶክ ፕሮግራም ይህንን ውዝግብ የሚሰማው አለመሆኑ ያስደስታል። ከዚያ በላይ ደግሞ ሃርድ ቶክ ሲያከትምለት እዚያው ባልነበረበት አገር መሆኑ ያረካል። ከዚህ ቅራ ቅንቦ ክርክር ይልቅ ያልሆኑትን መሆንና ያንኑ ለማጽናት የሰው ቀልብ ለመሳብ የሚደረገው የጅልነት ግልቢያ ያሳዝናል። ልክ ካንቶና፣ ቴሌ፣ ዩዜብዮ፣ ሮሲ፣ ካካ፣ ሜሲ፣ ማራዶና … ወዘተ እያሉ ለራሳቸው ስም የሚያወጡ፣ ነገር ግን በግብር ዜሮ የሆኑ የግር ኳስ ተጨዋቾች አይነት… “


ዶክተር ገመቺስ በባለቤትነት የሚያስተዳድሩት ኤል ቲቪ የተሰኘው የቴሌቪዥን ፕሮግራም ያሰራጨው ቃለ ምልልስ ወደ አንድ ብሄረሰብ ያመዘነ ሆኖ በመገኘቱ ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ኤጀንሲ ማስጠንቀቂያ እንደደረሰው የድርጅቱ ሰራተኛ የሆነችው ቤተልሄም ታፈሰ አረጋገጠች። ይህንኑ ዜና በግል የፌስ ቡክ ገጿ አትማለች። አብዛኛው አስተያየት የከረረ ተቃውሞና የሙያ ስነምግባር አለመከተሏን የሚያመላክት ነው። በሌላ በኩል ደርጅቱ ማስጠንቀቂያ እንዳልተሰጠው ይፋ አድርጓል። በዚህ መነሻ የቤቲ የተደበቀ ሃሳብ አሁንም ሊጣራ እንደሚገባ አስተያየት እየተሰጠ ነው።

የኤልቲቪ የሰው ኃይል አስተዳደር አዲስ ብርሃኑ ብሮድካስት ኤጀንሲ ማስጠንቀቂያ እንዳልተሰጣቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል፤ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ከሚዲያዎች ጋር ተደርጎ በነበረው የመገማገሚያ ውይይት ቃለ መጠይቁ ተነስቶ “ካለው የፖለቲካ ሁኔታ ጋር የማይጣጣምና ሁኔታውንም የሚያጋግል ስለሆነ ትክክል አይደለም” የሚል አስተያየት እንደተሰጣቸው ብቻ ነው ለቢቢሲ የተናገሩት። በዚሁ መነሻ ቤቲ ለምን የመንግስትን ስም ለማጠልሸት እንደፈለገች፣ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ እንደተሰጠ አድርጋ መዘግቧና ለሌሎች ሚዲያዎችም ምላሽ መስጠቷ ምን አልባትም በህግ ሊያስጠይቅ እንደሚችል ግምት አለ። ከዛ በላይ ግን ዝና ፍለጋ እንደሆነ የሚናገሩ ጥቂት አይደሉም።

ኢጀንሲው ከላይ የተባለውን ጠቅሶ የቃል ማስጠንቀቂያ መስጠቱን የገለጸችው ቤተልሄም በዝርዝር ምን እንደተነገራቸው አላብራራችም። በደፈናው ግን ” ባለፈው ሳምንት ከአብን ሊቀመንበር ዶክተር ደሳለኝ ባደረኩት ቃለ መጠይቅ ወደ አንድ ብሄር ያዳላ ነው በማለት እኔና የቴሌቭዥን ጣብያውን የወቀሰ ሲሆን፣ LTV በራሱ ዪቱይብ ቻናል ላይ ጭኖት ከሁለት መቶ ሺ በላይ ሰው አይቶት የነበረው የዚሁ ቃለመጠይቅ ቪድዮ እንዲያወርድ በተሰጠው ትእዛዝ መሰረት ጣብያው የጫነውን ኢንተርቪው ለማውረድ ተገዷል” ብላለች።

ከጉዳዩ ጋር ምን ግንኙነት እንዳለው ባይታወቅም ከሁለት መቶ ሺህ ሰዎች በላይ ቪዲዮውን እንደተመከቱት ያስታወቅችው ቤተልሄም “የሚድያ ነፃነትና በጋዜጠኞች ላይ የሚደረግ ወከባ ይቆማል ተብሎ በሚታሰብበት በዚሁ ወቅት፣ ብሮድካስት ባለስልጣን እንዲህ አይነት ድርጊት መፈፀሙን አሳዛኝ ድርጊት ነው ” ስትል ወቅሳለች። በወቀሳዋ ኤጀንሲው ማስጠንቀቂያ የሰጠበትን ምክንያት ዘርዝራ መከራከሪያ አላቀረበችም። 

አክላም ” እውነት ለመናገር ኦሮሞ ነኝ። በኦሮሞነቴም እኮራለሁ። አንድም ቀን ግን ካሜራ ፊት ኦሮሞነቴን ዘሬን ይዤው ገብቼ አላውቅም።  ስራዎቼም ለዚህ ምስክር ናቸው። ለአንድ ብሄር አደላች የሚለው ቀሽም መከራከሪያ ነው ” ካለች በሁዋላ  በማጠቃለያዋ  ” ደህና ሰንብች ሃርድቶክ ብያለሁ ” ስትል በመገረም ስቃለሽ።

ከአብን ሊቀመንበር ጋር ያደረገችውን ቃላ ምልልስ ተከትሎ ከፍተኛ ወቀሳ የገጠማት ቤተልሄም በሚዲያ ነጻነት ስም ሆን ተብሎና ታስቦበት የተዘጋጀ ቃለ ምልልስ ስታደርግ ተጠያቂውን በማሳጣትና ምላሽ እንዳይሰጥ በመገደብ፣ እወክለዋለሁ የሚለውን ህዝብ ስሜት በመንካት ፣ በአማራ ህዝብ ላይ ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት የተፈጸሙትን ዝግናኝ ወንጀሎች በማናናቅ፣ የአማራ ሴቶች እንዳይወልዱ መደረጋቸውን በይፋ አደባባይ ወጥተው መናገራቸው የአደባባይ እውነት ሆኖ ሳለ በማጣጣል፣ የተጠያቂውን ምላሽ ለታቀደው ዝግጅት እንዲመች በማድረግ ወዘተ ለተነሳባት ተቃውሞ ” እኔ ምን አጠፋሁ” በማለት ከመናገር ውጪ ቀጥተኛ ምላሽ እስካሁን አልሰጠችም።

“አሽሙርና የአየር በአየር ወሬ በመልቀም ራስን ከሃርድ ቶክ ተርታ ማሰለፍ እጅግ ውድቀት ነው” ሲሉ አስተያየት የሰጡ  ልጅቷ ጭብጨባ ጭንቅላቷን አሳብጦታል። የአማራን በብሄር መደራጀት የማይወዱ ሲያፏጩ ትክክለኛ ድጋፍ መስሏታል። ነገሩ ሁሉ ” አወቅሽ ሲሏት የቄስ ሚስት መጸሃፍ አጠበች” እንደሚባለው ዓይነት መሆኑንን ያመላክታሉ።

እጅግ ገለልተኛ የሆኑ ክፍሎች የጣቢያው ባለቤት ፓስተር ዶከተር ገመቺስ ክርስቲያን እንደመሆናቸው፣ ለእውነት ያደሩ መሆናቸውን ደጋገመው እንደሚናገሩት፣ የአምላክን መጽሃፍ ህዝበ እግዚአብሄር ፊት ይዞ እንደሚወጣ ሰባኪና መምህር፣ እንደ አንድ ልምድ ያለውና ሃላፊነት እንደሚሰማው ሰው ይህ ሁሉ ተቃውሞ ሲነሳ ቃለ ምልልሱን አይተው ዝም ማለታቸውን ቅር እንዳሰኛቸው ይንገራሉ።

ዛሬ ጊዜው ይባላሉ፣ ይጨራረሳሉ በሚል እሳታን ቤንዚን ተደረገው የተቀመጡ የኦሮሞና የአማራ ህዝብ በመረዳት ላይ የተመሰረተ ግንኙነትና አንድነት በሚፈጥሩበት ወቅት እንዲህ ያለውን ቃላ ምልልስ ማካሄድ መላ ካልተባለ አደጋው የከፋ ሊሆን ስለሚችል የብሮድ ካስት ኤጀንሲ ይህንን ማደረጉ አግባብ እንደሆነ የሚናገሩ አሉ። ያንኑ ያህል ደግሞ ያወገዙትም አሉ።

ባይበዙም በቃለ ምልልሱ ወቅት በሰጠው ምላሽ ብዙም ባይረኩም የተጠያቂው ትህትናና ትዕግስት ተደንቋል። በሌላ በኩል በጠያቂዋ ገጽታ ላይ ይታዩ የነበሩትን መቀያየሮችና የሻካራ ስሜት መገለጫዎች በማንሳት አካሄዱ ሁሉ ትክክል እንዳልነበር በጨዋ ቋንቋ ሲገልጹ መሰንበታቸው የሚታወሰ ነው።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ኤፒ ለቅጥፈቱ ይቅርታ አልጠየቀም – ምርጫ ተራዘመ፤ለምን?
0Shares
0