የሚመሩትን ሰራዊት በመያዝ ወደ አስመራ አቅንተው የነበሩትና አሁን በተጀመረው የለውጥ ሂደት ወደ አገራቸው የተመለሱት ብርጋዴር ጀነራል ከማል ገልቹ የኦሮሚያ አስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ ሆኑ። ጀነራሉ በአቶ ጁነዲን ዘመን በኦሮሚያ ጠንካራ የሚባል ሰፊ መጠን ያለው የልዩ ሃይል ሲገነባ ሚናቸው ከፍተኛ እንደነበር የሚያውቋቸው ይናገራሉ።

የኦሮሚያ ልዩ ሃይል በፌደራል ፖሊስ ቅርጽ የተደራጀና ክልሉን ሙሉ በሙሉ የመከላከል አቅም ነበረው። በኦሮሚያ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ከመቀጣጠሉ በፊት ይህ ሃይል ማንኛውንም ችግርና የድንበር ውዝግብ ያለ አንዳች የፌደራሉ ሃይል እገዛ ማስታገስና ማስቆምና አይከብደውም ነበር። በተለይም ከሶማሌ ክልል ጋር ያለውን የተለመደ የድንበርና የግጦሽ መሬት ውዝግብ መቆጣጠር ለኦሮሚያ ልዩ ሃይል ትልቅ የቤት ስራ ሆኖ እንደማያውቅ ለስራው ቅርብ የሆኑ ይናገራሉ።  ይህን ሃይል የገነቡት ከስደት ተመላሹ ከማል ገልቹ ናቸው።

የትላንቱ “አሸባሪ” የዛሬው አዲስ ተሿሚ ከአስመራ ወጥተው ኡጋንዳ ይኖሩ እንደነበር የሚያውቋቸው በትችት ሲገልጹ ነበር። እኚህ በኦሮሚያ ምስራቅ ክፍል ተሰሚነት እንዳላቸው የሚነገርላቸው ጀነራል፣ የኦሮሚያ የአስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ ሆነው መመደባቸው  አስገራሚ ሆኗል። ምን አልባትም የቀድሞው ኦህዴድ፣ የአሁኑ ኦዴፓ በምስራቅና በምዕራብ በኩል በቀላሉ ድጋፍ ለማግኘት እንደሚያስችለው ይገመታል።

የኦዴፓ መሪዎች ጀነራሉን ቀደም ብለውም ቢሆን ስለሚያውቋቸው ሃላፊነቱን ሲሰጡዋቸው ከጸጥታ ማስከበር ጋር ያለውን ችግር ሙሉ በሙሉ ለመቅረፍ ከክማል ገልቾ የተሻለ አማራጭ እንደማይኖር በማመን እንደሆነም አስተያየት እየተሰጠ ነው።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *