ሐይማኖት አበራ ተገኝ የረዳት አብራሪ ሃይለመድህን እህት ናት። ወንድሟ ወደ አገሩ እንዲገባ ፍላጎት እንዳላት ጠቅሳ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ደብዳቤ ጽፋ ነበር። ቅዳሜ ” በቅርብ ቀን” በሚል ርዕስ ወንድሟን አስመልክታ ሙሉ መረጃ ለሕዝብ ይፋ እንደምታደረግ አስታወቃለች።

” ውንድሜ ወንጀለኛ አይደለም” በሚል መደምደሚያ እንዳመለከተችው፣ ከዛሬ አራት አመት በፊት ወንድሟ ስዊዘር ላንድ አውሮፕላን አሳርፎ እጁን የሰጠበትን ምክንያት የሚያስረዳ መረጃ ነው ይፋ የምታደረገው።

Related stories   "የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎችን ላለመላክ የወሰነው የማይታዘዝና የማያጎበድድ መንግሥት ይመጣል የሚል ስጋት ነው"አንዳርጋቸው ፅጌ

ለጄኒቭ ፖሊስና አቃቤ ህግ የተናገረውን ሙሉ ሰነድ ኦሪጂናሉን በፈረንሳይኛ፣ እንዲሁም ትርጉሙን ይፋ እንደምታደርግ ነው የተናገረችው። በዚሁ ለአቃቤ ህግ በተሰጠ ቃል ውስጥ ለወንድሟ መሰደደ ምክንያት የሆኑ አራት ሰዎች በስም የተዘረዘሩ መሆንን ሐይማኖት አስታውቃለች።

“ለወንድሜ ስደት ምክንያት የሆኑትን የአራት ሰዎች ስም ዝርዝርም ይፋ አደርጋለሁ። ያኔ የሚመለከተው ክፍል የሚሰጠውን መልስ አብረን እናያለን ” በሚል ፍትህ ፈላጊነቷን አሳይታለች።

Related stories   በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 110 ሺህ ዶላር ተያዘ

የአማራ መገናና ብዙሃን አየር መንገዱን አስመልክቶ መረጃ ይፋ ካደረገ በሁዋላ ከየአቅታጫው ተበዳይ ነነ የሚሉ ወገኖች እየተነሱ ነው። የዋና ስራ አስፈጻሚዉን የስልክ ድምጽ ባማስማት ሁሉ ቅሬታዎች ይፋ እየሆኑ ነው።

2018-10-14-9.png

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *