በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከአንድ የ33 ዓመት ወጣት ሆድ በቀዶ ህክምና 120 ሚስማሮች፣ አንድ መርፌ ቁልፍ፣ ሁለት መርፌ፣ ሁለት ስትኪኒና ሁለት ስባሪ ብርጭቆዎች መውጣታቸው ተገለፀ።  ለ10 ዓመታት የአዕምሮ ህመምተኛ የነበረው ወጣት ለስምንት ዓመታት መድሃኒት እየወሰደ መቆየቱ ተነግሯል። በኋላም መድሃኒቱን በማቋረጥ ለሁለት ዓመት ፀበል ሲከታተል መቆየቱን ቤተሰቦቹ አስታውቀዋል።

በቅርቡ ግን የወጣቱ ሆድ በማበጡና ባጋጠመው ህመም ምክንያት ወደ ሆስፒታሉ አቅንቷል። በዚህ ወቅት በዶክተሮች በተደረገ ምርመራ ባልተለመደ ሁኔታ በሆዱ ውስጥ ሚስማሮችን ተገኝተዋል። 2 ሰዓት ከ30 ደቂቃ በፈጀው የቆዶ ህክምናም 120 ሚስማሮች፣ አንድ መርፌ ቁልፍ፣ ሁለት መርፌ፣ ሁለት ስትኪኒና ሁለት ስባሪ ብርጭቆዎችን አውጥተዋል።

ቆዶ ህክምናውን የመሩት  የሆስፒታሉ የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ዶክተር ዳዊት ተአረ እንደገለፁት፥ ቀዶ ህክምናው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቆ ወጣቱ በአሁኑ ወቅት በጥሩ ሁኔታ በማገገሚያ ክፍል ውስጥ ይገኛል።

በዘመን በየነ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *