“Our true nationality is mankind.”H.G.

” ኢትዮጵያዊነትን ከሰላም ጋር አንድ ለማድረግ እንስራ” ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

 4ኛው የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር  አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ በወርሃ የካቲት 1942 የተወለዱ ሲሆን ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዘኛና አማርኛ አቀላጥፈው የይናገራሉ።

አምባሳደር ሳህለወርቅ የፈረንሳዩ ሞንተፔለ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ምሩቅ ሲሆኑ እኤአ ከ1989-1993 ተቀማጭነታቸውን ሴነጋል በማድረግ የማሊ፣ የኬፕ ቨርድ፣ የጊኒ ቢሳዎ፣ የጋምቢያና የጊኒ አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል።

እኤአ ከ1993-2002 ደግሞ በጅቡቲ አምባሳደር ሆነው የሰሩ ሲሆን በወቅቱ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ቋሚ ተወካይም ነበሩ።

ከዚያም በመቀጠል ከ2002-2006 በፈረንሳይ አምባሳደር እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ተቋም ተወካይ ሆነው ሰርተዋል።

በኋላም በተባበሩት መንግሥታት ልዩ መልዕክተኛ ውስጥ የተቀናጀው የሰላም አስከባሪ ሃይል ተወካይ በመሆን በሴንትራል አፍሪካ(BINUCA) ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል።

በአፍሪካ ሕብረት ውስጥና በተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚ ኮሚሽን ውስጥም የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ ሆነው ያገለገሉት አምባሳደር ሳህለወርቅ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥም የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል ሆነው ሰርተዋል።

እኤአ በ2011 የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሃፊ የነበሩት ባን ኪሙንም በኬኒያ የተባበሩት መንግሥታት ዳይሬክተር ጄነራል አድርገው ሾመዋቸው አገልግለዋል።

በተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ በአፍሪካ ሕብረት ልዩ ተወካይ እንዲሁም በአፍሪካ ሕብረት የተባበሩት መንግሥታት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾመዋል።

BBC

ታላቅ ሀገር የመገንባት ህልምን እውን ለማድረግ ከሰላም ውጪ አቋራጭም ሆነ አማራጭ መንገድ እንደሌለ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ላይ ፕሬዚዳንት በመሆን በተሾሙበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ነው ይህን ያሉት።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በንግግራቸው፥ የኢትዮጵያ እና የህዝቦቿ ርእሰ ብሄር በመሆን ለማገልገል በመመረጣቸው ደስታና ክብር እንደተሰማቸው ገልፀዋል።

ፕሬዚዳንቷ አክለውም አቅማቸው በፈቀደው ሁሉ የበኩላቸውን ሲወጡ ለነበሩትና በዛሬው እለት በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣናቸውን ለለቀቁት ለኢፌዴሪ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የሚወዷትን ሀገራቸውን ለበርካታ ዓመታት ሲያገለግሉ የነበሩ ትልቅ የሀገር ባለውለታ ናቸው፤ በዛሬው እለትም ባደረጉት ተግባር በብዙ የአፍሪካ ሀገሮች ከተለመደው ውጪ በገዛ ፍቃድ ስልጣን በመልቀቅ ለለውጥ እድል መስጠት መጀመሩን ልንማር ይገባል።

ይህ ተግባር በክልሎች፣ በየደረጃው በሚገኙ የአስተዳደር አካላት፣ በመንግስትና በግል ተቋማትም ሆነ በሌሎች ማህበራዊ ተቋማት ጭምር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተስፋ አደርጋለው ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፥ አሁን በሀገሪቱ የተጀመረው የለውጥ ጉዞ በሴቶችም ሆነ በወንዶች እኩል ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ከተመራ ኢትዮጵያ ከድህነት እና ኋላቀርነት ተላቃ ወደ ብልጽግና ጎዳና የምታመራበትና ዜጎቿን ከመድሎዎ በፀዳ መልኩ በእኩልነት የሚኖሩባት ሀገር እውን እንደሚያደርግ እተማመናለሁ ብለዋል።

የለውጥ ጉዞው ውስብሰብ እና በርካታ ፈተናዎች ያለቡት እንደሚሆን ይጠበቃል ያሉት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፥ እነዚህን ፈተናዎች መንግስትም ሆነ ሌሎች የፖለቲካ ሀይሎች የጋራ ቤት እንደሚገነባ ቤተሰብ እርስ በአርስ በመደማመጥ፣ በመፈቃቀድና በመተሳሰብ አንድነትን በማጠናከር መሻገር እንደሚጠይቅ ገልጸዋል።

 

Related stories   የሲኤንኤን ዘጋቢ ኒማ- በተወነችው ተውኔት ውስጥ ዳግም ሞት የተፈረደባቸው ዜጎች

Bilderesultat for ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

….ታላቅ ሀገር የመገንባት ህልምን እውን ለማድረግ ከሰላም ውጪ ምንም አቋራጭም ሆነ አማራጭ መንገድ የለም ….

 

ታላቅ ሀገር የመገንባት ህልምን እውን ለማድረግ ከሰላም ውጪ ምንም አቋራጭም ሆነ አማራጭ መንገድ የለም ያሉት ፕሬዚዳንቷ፥ ስለዚህ ሁላችንም ሰላማችንን አጥብቀን እንድንጠብቅ ከሁሉ በላይ ሰላም ሲታወክ በምትጎዳዋ እናት ሰም እጠይቃለሁ ብለዋል።

ኢትዮጵያዊነትን ከሰላም ጋር አንድ ለማድረግ እንስራ ሲሉም ፕሬዚዳንቷ ጥሪ አቅበዋል።

የሰላም እጦት ዋነኛ ተጠቂዎች ሴቶች በመሆናቸው፥ በስልጣን ቆይታቸው ዋነኛው ትኩረታቸው መላው ኢትዮጵያን ሴቶችና ሰላም ወዳድ ወንዶችን እንዲሁም በመላው ዓለም የሚገኙ ሰላም ወዳዶችን ሁሉ ከጎናችው በማሰለፍ ሰላም በማስፈን ላይ ርብርብ ማድረግ እንደሚሆንም አስታውቀዋል።

በዚህም የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ጨምሮ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎናቸው እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል።

የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌትና የስልጣኔ ምልክት የሆነቸው ኢትዮጵያ ድህነትና ኋላ ቀርነት ውስጥ እንደትቆይ ያደረጋት የሰላም እጦት ነው ያሉት ፕሬዚዳንቷ፥ የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ የሰላም ጠንቅ የሆኑትን በማስወገድ የሀገሪቱ እድገትና ብልጽግናን አይቀሬነት ማረጋገጥ እንደሚገባም አንስተዋል።

ስለ እድገትና ብልጽግና ሲወራም የሴቶችና ወጣቶች እኩል ተጠቃሚነት ወሳኝ መሆኑን በመረዳት መላው የሀገሪቱ ሴቶች እና ወጣቶች በርትተው በሀገሪቱ ልማት ተሳታፊ በመሆን ድህነትን በጋራ እንዲያስወግዱም አደራ ብለዋል።

ሰላም የልማትና ብልጽግና ምልክት በመሆኑ፤ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ሴቶችም ሆነ ወጣቶች እንዲሁም ሁሉም የሀገረቱ ህዝቦች ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ እንዱረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል።

ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ዋስትና ያለው ዴሞክራሲ ወሳኝ ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፥ መንግስትም ሆነ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዴሞክራሲ ስር እንዲሰድ በማድረግ በሀላፊነት መንገድ እንዲሰሩም ነው ያሳሰቡት።

ህዝቡም የተጀመረው ለውጥ ተጠናክሮ እንዲቀጠል ለውጡን ለሚመራው የፖለቲካ ሀይል የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

ሴቶች ከወንዶች በተሰማሩበት ማለትም በቤት ውስጥ ልጆቻቸውን የሚያሳድጉ፣ በገጠርም ሆነ በከተማ በተለያየ ዘርፍ ተሰማርተው ኑሮን ለማሸነፍ ሌት ተቀን የሚተጉ ለእኔ ባያልፍልኝ ለልጆቼ ለሀገሬ ያልፋል በሚል ትግል የሚያደርጉ ሴቶች ከጥረታቸው ወደ ኋላ እንዳይሉ አደራ ብለዋል።

በወንዶች ጥረት ብቻ የተገነባ ሀገርም ሆነ ቤተሰብ የለም ያሉት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፥ ሴቶች የቤትም የሀገርም ምሰሶ ናቸው፤ ሴቶች ከተጎዱ ቤተስብ ይጎዳል ሀገር ይጎዳል፤ ስለዚህ ሴት ሀገር ነች፤ ሀገርን ደግሞ ወንዱ ሊንከባከብ ይገባል ብለዋል።

የሴቶችን ማንኛውንም አይነት ጥቃት የሚጸየፍ ትውልድ ለመፍጠር መስራት እንደሚገባም ነው ያስታወቁት። ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፥ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ20 የካቢኔ አባላት 10 ሴቶች እንዲሆኑ መደረጉ እና እሳቸውም ለዚህ እንዲበቁ መሆኑ በአሁኑ ወቅት እየመጣ ካለው ለውጥ ተጠቃሽ ነው ብለዋል።

የእስካሁኑ የሴቶች የትግል ጉዞ እውን እንዲሆን ሀላፊነት ከተረከቡ እንስቶ እስከ ዛሬዋ ድረስ ከፍተኛ ስራ በመስራት ላይ ለሚገኙት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሁን የጀመሩት አካታች ፖሊሲ ለሴቶች ብቻ ሳይሆን ለወንዶች ብሎም ለቤተሰብ እና ለሀገር መልካም በመሆኑ አጠናክረው እንዲቀጥሉበት አደራ ብለዋል።

በሙለታ መንገሻ – (ኤፍ.ቢ.ሲ)

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0