ወያኔ የራያን ሕዝብ መሬት ለመዝረፍና ማንነቱን በሃይል ለመጨፍለቅ የምታደረገው አፈና ትግሉን በይበልጥ ያጠናክረዋል እንጅ አያስቆመውም።

የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር (ትሕነግ) ዘርንና ቋንቋን መሰረት ባደርገ መንግስታዊ አወቃቀር የኢትዮጵያን ህዝብ የጫነችበት ቀንበር ከጀርባው ለማላቀቅ፣ ለሃያ ሰባት አመት ያደረገው እልክ አስጨራሽ ትግል ብዙ የደም ዋጋ ቢከፈልበትም፣ አሁን ለደረስንበት የሰላም ጮራ በመጠኑ ለማየት አብቅቶናል፣ ይህን የተጀምረው የእርቀ ሰላም ጉዞ ያልተዋጠላችው ትሕነግ (ወያኔ) በየማዕዘናቱ ትንኮሳ በማድረግ፣ ይሄውና ዘር ተኮር መተላለቅ እንዲነሳና አገሪቱ ወደ ማያባራ እልቂት እንድትገባ የተካኑበት መሰሪ ተንኮል በመጠቀም፣ ሕዝቡ እርስ በራሱ በማጋጨት ላይ ይገኛሉ።

ምንም እንኳ ለብዙ ዓመታት የራያ ህዝብ በወያኔ አፈና ምክንያት የደረሰበት ችግር አደባባይ ወጥቶ ማስረዳት ባይችልም፣ በተለያዩ ዘዴውች ስለ ማንነቱ ሲታገል ኑሯል። የዶክተር አብይ የለውጥ መንግስት ባደረገው የሰላም ጥሪ፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ መብቱን ለማስከበር ሰላማዊና ህጋዊ በሆነ መንገድ መታገል ህገ መንግስታዊ መብቱ እንደሆነ ባረጋገጠበት ጊዜ፣ መሬታቸው በጉልበት ተወሮ ወደ ትግራይ በተካለሉት የወልቃይት፣ ጠገዴ፣ የጠለምት እና የራያ ነዋሪ ወገኖቻችን ጥያቄያቸው በአደባባይ ባቀረቡ ቁጥር፣ በትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር (ትሕነግ) አልሞ ተኳሾች ሌት ተቀን ሲገደሉ፣ ሲደበደቡ፣ ሲታፈኑና መፈናፈኛ አጥተው የመንግስት ያልህ እያሉ የሲቃ እረሮ እያሰሙ ይገኛሉ።

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ፣ የራያ ህዝብ መብቱን ተጠቅሞ በማንነቱ የደረሰበት ግፍና ስቃይ እንዲሁም ማንነቱን ለማስመለስ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ጥያቄውን ለሚመለከተው ለወራሪው የትግራይ ክልል አስተዳደር ለማቅረብ አደባባይ እንደወጣ፣ አጋዚ በተባለው አልሞ ተኳሽ ቡድን በተተኮሰው ጥይት ብዙ ህፃናት፤ ሴቶች፤ ሽማግሌዎችና ጎርምሶች በግፍ ተጨፍጭፈው ተገድለዋል። ብዙዎችም የከባድና ቀላል ቁስለኛ ሆነዋል፣ እንዲሁም ብዛት ያላቸው የአካባቢው ወጣቶች በሌሊት የቤታቸው በር እየተሰበረ ተለቅመው ታፍነው ወደ ማይታወቅ ቦታ በመኪና ተጭነው ተወስደዋል። በወገናችን በራያ ህዝብ ላይ ይህንኑ መሰል አረመኒያዊ ድርጊት በመፈፀሙ በጣም አዝነናል፣

ድርጅታችን ልሳነ ግፉዓን፣ ከራያ ህዝብ ወገናችን ጎን እስከ ነፃነት ድረስ፣ ለማነነቱ በሚያደርገው ትግል አብረነው የምንቆምና የምንሰለፍ መሆናቸንን ስንገልጽ ከዚህ በታች የጠቀስናቸው ጥያቄውች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መልስ እንዲሰጣቸው በጥብቅ እናሳስባለን።

1ኛ/ ሽብር ፈጣሪው የትሕነግ ልዩ ሃይል ከጀመረው እኩይ ተግባር ተቆጥቦ በአስቸኳይ ከራያና ወልቃይት መሬት ወጥቶ በምትኩ የፌደራል ሃይል ገብቶ የአካባቢውን ሰላም እንዲያስከብር እናሳስባለን፤

2ኛ/ በትሕነግ ልዩ ሃይል በሺዎች የሚገመቱ የራያ ወጣቶች ምንም ጥፋት ሳያጠፉ መብታችን ይከበርልን ብለው ስለጠየቁ ብቻ ታፍሰውና ታፍነው የተወሰዱት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ እናሳስባለን፤

3ኛ/ በትግራይ ልዩ ሃይል አልሞ ተኳሾች ሕይወታቸው ላጡት ወገኖቻችን ተጠያቂው ትሕነግ (ወያኔ) ብቻ መሆኑን እናምናለን።

4ኛ/ በመላው ኢትዮጵያ በተለይም፣ በአካባቢው አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን፣ የራያና የወልቃይት ህዝብ የጠየቀውን የማንነት ጥያቄ ታሪካዊና ባሕላዊ ጥናት መሰረት ባደረገ፣ እልባት እንዲሰጠው፣ የማንነት ጥያቄው፣ በማድበስበስ ለማዘናጋት የሚደረገው ጉዞ በዙ ዋጋ እንደሚያስከፈል፤ በአገራችን የተጀመረው የለውጥ፣ የእርቀ የሰላም ጥረትና የመደመሩ ጉዳይ አቅጣጫው ስቶ ከማንወጣው አዘቅት ስለሚጨምረን ከአሁኑ መፍትሄ በአስቸኳይ እንዲሰጠው እናሳስባለን፤

የራያ፣ የወልቃይት፣ ጠገዴና የጠለምት ሕዝብ ማንነቱን በትግሉ ያረጋገጣል!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

ልሳነ ግፉዓን ድርጅት፣

ጥቅምት 16/2011

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   የአሜሪካ ሴናተሮች የኢትዮጵያ ምርጫ እንዲራዘም ያቀረቡት ጥሪ ብልህነት የጎደለው እጅግ አደገኛ ነው - ሎረንስ ፍሪማን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *