“Our true nationality is mankind.”H.G.

የመጨረሻው መጀመሪያ – የአፋር ክልል በለውጥ ፈላጊዎችና ተጻራሪዎች መካከል ልዩነት ተፈጥሯል፤ ፕሬዚዳንቱ ታገዱ

የአፋር ክልል ጉዳይ ወደ መጨረሻው እየተቃረበ መሆኑንን ጉዳዩን የሚከታተሉ እየተናገሩ ነው። አፈናና እስር እንዲሁም ድብደባ ቢደርስበትም ሕዝብ ለውጥ መፈለጉን አደባባይ በመውጣት በተደጋጋሚ እየገለጸ ነው። በክልሉ የሃብት ተጠቃሚነት ጉዳይ ከመቼውም በላይ ገኖ ወጥቷል። ክልሉን የሚመራው ፓርቲም ከሕዝብ ጎን በመቆምና ባለመቆም ጉዳይ ተቧድኗል። 

የአፋር ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አብዴፓ ም/ፕሬዚዳንት ሊቀምንበር ሃሰን አብዱልቃድር ሶስት አመራሮች በዲሲፒሊን ጉድለት መታገዳቸውን ለኢዜአ ተናግረዋል። እነሱም የቀድሞውን ፕሬዚዳንት አቶ ኢስማኤል አሊ ሲሮ፣ ምክትል ፕሬዚዳንቱን አቶ አወል አርባና የአርብቶ አደር ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ አሊ ሁሴን ናቸው።

በቅርቡ ለሚካሄደው ሰባተኛው ድርጅታዊ ጉባኤ አዘጋጅነት በአብላጫ ድምጽ የተመረጡትን አዘግጅ ኮሚቴዎች ባለመቀበላቸውና፣ ሂስና ግለሂስ ለማድረግ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሶስቱ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች እንዲታገዱ መደረጉን ነው ዜናው ያስታወቀው። 

በሌላ በኩል ግን የአፋር ክልል ለውጡን በአዲሱ መደመር ስሌት ሊቀላቀል ይገባል የሚል አቋም ያላቸው፣ አፈናና እስር ይቁም፣ የልማታቸንና የተፈጠሮ ሃብታችን ተጠቃሚ እንጂ ተመልካች መሆን የለብንም የሚሉትን የሚደግፉት ሃይሎች አሁን አይናቸውን መጻፍና ማንበብ በቅጡ በማይችሉት አሁን ክልሉን በሚመሩት አቶ ስዩም አወልና የእሳቸው ደጋፊዎች ላይ ተክሏል።

እንደ ሶማሊ ክልል ለውጥ የናፈቃቸው እነዚህ ሃይሎች በፊደራል መንግስት በኩል ሙሉ ድጋፍ እንዳላቸውም ይታመናል። በሌላ በኩል የአቶ ስዩም ቡድን በህወሃት ድጋፍና እገዛ እንደሚደረግለት ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ይናገራሉ። ህወሃት ከሶማሌ ክልል ጋር ያለው ግንኙነት እንዲበጠስ ከሆነ በሁዋላ ትኩረቱን ያደረገው አፋር ላይ ነው።

የጋምቤላ ጉዳይ በበቃኝ ከተጠናቀቀ በሁዋላ ቀጣዩ ትኩረት የአፋር ክልል ላይ እንደሚሆን እየተገለጸ ባለበት በአሁኑ ሰዓት፣ ፓርቲው ውስጥ ፍትጊያ መጀመሩ የእነ አቶ ስዩም ጉዳይ እያከተመ መሄዱን የሚያሳይ ስለመሆኑ ምልክት ነው። የአፋር ህዝብ ልክ እንደ ሶማሊ ክልል አይነት በሳልና ሰው ሰው የሚሸት አስተዋይ መሪ ከመናፈቁ ጋር ተዳምሮ ለውጡ ብዙም እንደማይቆይ ከወዲሁ እየተነገረ ነው። የአቶ ስዩም ቡድን በክብር ሃላፊነቱን ህዝብ ለሚፈልገው አመራር የማይሰጥ ከሆነ የአብዲ ኢሌ አይነት እድል ሊገጥማቸው እንደሚችል ግምት አለ።

ነገሮች በዚህ መልኩ በሚሄድሁበት በአሁኑ ወቅት ታገውደዋል የተባሉት ክፍሎች ሙሉ በሙሉ ስራቸውን በመስራት እነሱም ፖለቲካዊ እርምጃ መውሰዳቸውን እያስታወቁ ነው። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ እንደሚሉት በዚሁ ግብ ግብ መነሻ የፌደራል ከፈተኛ ባለስልጣናት ወደ አፋር አምርተዋል። 

የክልሉ አክቲቪስቶች እንደሚሉት አቶ ስዩም የሚባሉት የአፋር ፕሬዚዳንትና ቡድናቸው ከፓርቲው ታግደዋል። ይህንኑ ለማስተባበል ሲባል የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አምባሳደር ሃሰን አብዱልቃድር ለኢዜአ ከዲሲፒሊን ጋር በተያያዘ ሶስት አባላትን መታገዳቸውን ተሽቀዳድመው ይፋ አድርገዋል። ከዚህም በተጨማሪ አቶ ስዩም የአፋርን ጉዳይ ወደ ጎሳ ሊወስዱት እየሞከሩ ያለበት መንገድ ጥንቃቄ እንደሚያሻው ተጠቁሟል።

የአፋር ክልል ጉዳይ ከተጠናቀቀ ቀጣዩ ክልል ቢኒሻንጉል እንደሚሆን ይገመታል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ቻይና በአፍሪካ ኅብረት አሸማጋይነት የሚካሄደውን የህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር እንደምትደግፍ ገለጸች
0Shares
0