“Our true nationality is mankind.”H.G.

ይድረስ ለ ክቡር ከንቲባ ታከለ ኡማ – ሸገር መሃል – አባዊርቱ

በመጀመሪያ ከፍ ያለ የአድናቆትና የክብር ደብዳቤዬ ይድረስህ። በቀጥታ ወደመጣሁበት ጉዳይ እገባለሁ – በስልጣን ከተሾምክበት ቀንና ወር ጀምሮ ስራዎችህን በደንብ እከታተል ነበር። ሁሌ የሚገርመኝና የሚደንቀኝ የምትሰራው መልካምና ምስጉን ስራ እንደተጠበቀ ሆኖ ከዳር እስከዳር የተነሱብህን ተቃዋሚ አትላቸው ተቺዎች በጭራሽ ከምረዳው በላይ ሆኖብኝ ቆይቶ ነበር። የቅርቡን ሃርድቶክ ኢንተርቪውን በደንብ ካየሁ በሁዋላ ለምን እንደዚህ አጥብቀው እንደሚተቹህ ግልጽ ሆነልኝ። ይህውም እንዲህ ነው። በዚህ አጋጣሚ ያንን ኢንተርቪው እስቲ እንደገና በዪቱብ በደንብ ተመልከተው ወንድሜ። ምክንያቱን በደንብ ትረዳዋለህ። ይህንን ስል ጠያቂው በደንብ መጠየⷅ የሚገባውን ሁሉ በማድረጉ አደንቀዋለሁ። ምንም እንከንም አላወጣለትም። እስቲ ወደ አንተው ስብና ሳልገመግም ስራዎችህን እንመልከት ከተሰየምክበት ጥቂት ወራት ወዲህ ያረካቸውን ነገሮች በመዳሰስ። ህዝቡ ይህን ሳያውቀው ቀርቶ ሳይሆን እንደው በጥቅሉ ለማስታወሻና ለህሊናም ብዬ እንጂ።

የሸገርን ወጣቶች በከፊልም ቢሆን ስራ እንድይዙ በማድረግ። ለደሃ የሸገር ነዋሪዎች የተዘጉ ቤቶችን እየከፈትክ በማሳደርና በማኖር፡ የከተማዋን ጽዳት በልዩ ትኩረት አይቶ ህዝቡን ማስተባበር፡ እንደመልካሙ መሪያችን ተምሳሌት ሆነህ ታች ወርደህ ዝቅ ብለህ ህዝቡን በማስተናገድ፡ ከስራባልደረባዎችህ ጋር አንድ ላይ በመሆን የአጭርና ረጂም ጊዜ የከተማ እቅድ አውጥቶ ያንን ለመተገበር ሌት ተቀን መስራት፡ የተራቡና የተጠሙትን ተፈናቃዮች በጊዜው ደርሶ አለሁላችሁ ማለት፡ ስንቱን ቆጥሬው ስንቱን እዘልቀዋለሁ። የኢትዮጵያ አምላክ ብቻ ብርታትና ጥንካሬውን ይስጥህ እንጂ አንተስ መልካሙን ለከተማው ህዝብ እያረክ ነው። እናም በዚሁ ቀጥልበት። ከሁሉ በላይ ሰው እያወቀም ይሁን ሳያውቀው ወይም እንዲረዳው ያልፈለገው ነገር ቢኖር የሸገር የየክፍለከተማው የመሬት ይዞታን የመሰለ የተጨማለቀ መስሪያቤቶችን እያጸዳህና ወደፊት እያስገሰገስክ ባለበት ጊዜ አፋቸውን ሞልተው አንተን የሚተቹ ግለሰቦችም ይሁኑ ድርጅቶች ምክንያታቸው ግልጽ ባይሆንም የኔ ጥርጣሬ አዲሳበቤ አይደለህም ከሚል ይመስለኛል። ጠያቂውም ነካክቶ አልፎታል። ያንተ መልስ ግን ትህትና ያዘለ ቢሆንም አስረግጠህ አንተ አዲሳበቤ መሆንህን ፪፭ አመታትም ኑር ፭ አመታት ቁጥሩ ሳይሆን የነዋሪነት ግዴታህንና ብቃትህን እንዲህ በግልጽ እያስመሰከርክ ማለትህአኩርቶኛል:: ተቺዎችህ ግን ምን ሆነህ እንድትቀርብላቸው ግልጽ ባለመሆኑ መላ ለመምታት ያስቸግራል። ግልጹ ነገር ግን የሰራሃቸው ስራዎች ለብዙ አመታት የከንቲባነትን ስልጣን ይዘው ይንደፋደፉ ከነበሩት በሙሉ የመጀመሪያውን ይይዛል በኔ ግምት። እመነኝ ወንድሜ። ወደፊት እንደዚህ አይነት ጥያቄ ሲቀርብልህ ቀጥ ብለህ ደረትህን ነፍተህ በመለማመጥ ሳይሆን በግልጽ በጥቂት ወራት ውስጥ ስራህ የሚመሰክረውን እያሰመርክበት አስረዳ። ለትህትና ገና አልታደልንም። የአቢይን ትህትናና ቅንነት ያየ ባሁን ጊዜ አቢይይን ያንጉዋጥጣል ሰው ብሎ መገመት በከበደ ነበር። እናም ይቺን አጭር ማስታወሻ እንድጽፍልህ ያበቃኝ ምንም ተስፋ ሳትቆርጥና የያዝከውን መስመር ሳትስት ስራህ ላይ ብቻ አተኩር። ዶር አቢይ ከሰሩት ነገር በሙሉ ያንተን ለዛ ቦታ መሾም ከዋነኞቹ አንዱ ነው። በስራ እያስመሰከርክ ነውና። አዲሳበቤ አይደለህም ለሚሉ በሙሉ መልስህ እንዲህ መሆን ነበረበት “ እኔ አዲሳበቤ ካልሆንኩ ማንስ ሊሆን ይችላል በፈለጋችሁት መስፈርት? “ ብለህ ካበቃህ በሁዋላ እንዲህ ብለህ በልብህ ደግሞ ተርትባቸው፡ ” ሰንጋ ፈረሰኞቹ እየጋለቡ ነው ውሾቹ ግን ከሁዋላ ጩሀታቸውን አላቁዋረጡም” :: በዚህ አጋጣሚ የቅርብ ዘመድህ ሊቁ ጸጋዬ ገ/መድህን በህየወት ቢኖር ምነኛ በኮራብህ ነበር። ካለበትም ያይሃልና አደራ በርታ። ተስፋም አትቁረጥ። ሌላው በግድ ሊግቱን የሚሞክሩት ነገር ግልጹ ነገር ባደባባይ እየታየና እየተዳሰሰ “ ለቄሮዎች ቦታ አድለሃል” ነው።  ገና ብዙም ትባላለህ። ስብናህን ስገመግመው ግን ለንዲህ አይነት ከንቱ ትችት የማትበገር መሆንህን ነውና አደራ ተስፋ አትቁረጥ። ስራህ እየመሰከረ ነው። የሸገርን የመሬት አስተዳደር ጉዳጉድ በየክፍለከተማው መደርመስ ስትጀምር ገና ብዙ ቅጥረኛ ተቺዎች ያላኩብሃልና በተጠንቀቅ ጠብቃቸውና ስራህ ላይ ብቻ በርታ። የመሬት አስተዳደር ጉድ በቀላሉ የሚፈታ ስላልሆነ በቀላሉ እንዳትሸነፍ። እስካሁን የሰራሃቸውን ያየ ሲሆን ኒሻን የሚያሰጥህ ነበር። ገና ብዙ አውሬዎች ከየምሽጉ ይላኩብሃልና በስራት መክታቸው። ፈጣሪ አብሮህ ይሁን። ለከተማው ያለህ ምኞትና ትልም እጅግ የሚደነቅ ነው። ከዚህ በላይ አዲሳቤነትና ኢትዮጵያዊነት ምን ሊሆን ይችላል? የሚገርመኝ ባለፈው ስራት የተለየ ካድሬ የሆንክ ይመስል ጥላሸት የሚቀቡህ ነፈዞች ለዛማ ከአቢይና ለማስ በላይ የቅርብ ወዳጆች ነበሩ እንዴ ብለን እንድናስታውሳቸው ግድ ይለናል። ያውም የመረጃ አካል አልነበሩም እንዴ? ፈጣሪ የኢትዮጵያን መከራ በቃ ብሎ ወደህሊናቸው መልሶ እንዲህ የሚያስደምም ለውጥ በማምጣት ተባበሩን እንጂ ወዴት እንደምንሄድ ማን ያውቅ ነበር? ሁሉ ለራሱ ቀረብኝ የሚል እንደ አሸን በፈላበት አገር አንተና የነቲም ለማ የሰላምና ያገር እድገት ጉዞን ለመገንዘብና አፕሪሼት ለማድረግ ሁሉም በእኩል ላይታደል ይችላልና በርታ። ህዝባችን ዛሬ ያወድስና ነገ የሚከዳ ነው ባብዛኛው። ለአጋጉል ተቺዎች ቦታ አትስጥ!! ይህው ነው መልክቴ። በዚች ኦሮሚፋ ግጥም ልለይህ።

ለሚሌ ፋካቴ ጀሪቲ ፋርሲናን

ጋማና ዳባቴ ኦልኬሳ ቡራቅናን

ማቃ ኦሮሞቲን ሁንዳ ጢሬፋዋን

ጀሪቲን ዋልኬሳ  ኢልማን ቢኔንሳዋን!!!!

ሸገር ከንኬ ሚቲ ዮጋ ሲንጄዳኒ

ገዴን ገዴዱማ ዲሲ ሃጢባራኒ።

ጃባዱ ኮርሜቶ ጂሩኬቲ ጪሚ

ሴራን ቡሉ ታና ሲሪቲ ናሂሚ!!

ኦሌ ቡላ ማሌ ዱጋን ሂንዶካቱ

ጋቲራን ጉባናን ቢዪስ ቢያ ሂንታቱ።

ቃማጤን  ባዳቴ ኢጃን ዮጋአርጋኒ

ዋን ጄዳን ዳብናን ኮርማን ሃሞርካኒ??

አቺዱፋን ታኬ ዋራ ሴራን ቡሉ

ማታ ጋዲቃብናን አራብሶን ሲን ዖሉ

ቱፋዱ ናዲሲ ዋራ ጋራፍ ቡሉ።

ጋሩ ናማዲንቃ ሸገር ካንኬሚቲን

ዋራቤሳ ገዲ ኬሱማ ጀሪቲን

ደንደኢ አካ ታዬ ሜ ሃቡልቱ ዱቢን

ጄዴን ሲቲዳማ ኤታማዦር ዊርቱን

አባዊርቱ

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ሕዝብን ማን ይሰራዋል?
0Shares
0