ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ከዚህ ቀደም በቀን 4/10/2010 ዓ/ም “የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቂ ተቀባይነት የለውም” ብለው ከግል የህወሃትና የትግራይ ፍላጎት ብቻ ተመሰርተው የማንነት ጥያቄው ውድቅ ነው እንዳሉ እናስታውሣለን።

አሁንም ሰልጣናቸውን መሰረት አድርገው የዓለም ማህበረሰብና መንግሰታት ለማደናገር ለማጭበርበር ድጋሜ በ14/02/2011 ዓ/ም የወልቃይት ጠገዴ የአማራ የማንነት ጥያቄ ተቀባይነት የለውም ብለው ስለ ሰጡት መልሰ የወልቃይት ጠገዴ ኮሚቴን እና መላ የአማራ ህዝብ የሚሳዝን ነዉ፡፡ ብሎም ሃሳባቸው ህግ እንደሌለ ወደ ግጭት የሚያመራ ሰለሆነ ኮሚቴው በከፍተኛ ደረጃ ተቃውሞውን ይገልፃል፡፡ ምክንያቱም:_

የወልቃይት ጠገዴ የአማራ የማንነት ጥያቄ መጀመሪያ ታህሳሥ 27/04/2007 ዓ/ም በፖስታ (EMS) ልከን ሁለተኛ በ21/03/2008 ዓ/ም ለፌዴሬሽ ም/ቤት ጥያቄ በአካል 23,000(ሃያ ሦሰት ሺ)የህዝብ ፌርማ የያዘ 9 (ዘጠኝ) ገጽ ደብዳቤ አቅርበናል። በተመሳሳይ በታህሣሰ 7/04/2008 ዓ/ም ለትግራይ ም/ቤት ለወ/ሮ ቅዱሣን ነጋ፣ለትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ለአቶ አባይ ወልዱ፣ለህውሃት ጽ/ቤት፣ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ትግራይ ም/ዞን ሑመራ በ10/04/2008 ዓ/ም መቀሌ የገባ የማነንት ጥያቄ ማመልከቻ ለማቅረብ የሄዱትን የማነንት ጥያቄ ኮሚቴ ልዑክ ባረፉበት ሁመራ አዱ ገነት የተባለ የአቶ አበበ ለውጤ ሆቴል ከምሽቱ 5፡20 በ32 ልዩ ሃይልና ፖሊስ ታፍነው በስንት አቤቱታ ኮሚቴው ከታፈነበት እንዲፈታ ሆኗል። በ11/04/2008 ዓ/ም ለሑመራ ዞን አሰተዳደር አቶ ኢሣያስ ታደስ እና አቶ ተኪኡ መተኩ ባሉበት ጥያቄአችን አቅርበናል። በተሠጠን መልስ “የወልቃይት ህዝብ የታገለው ትግራይ ለመሆን ነው ብለውናል። በሦስተኛ የወልቃይት ጠገዴ እስራትና ደብደባ ሲበዛ በቅሬታ ጥር 02/05/2008 ዓ/ም ለትግራይ ምዕራባዊ ዞን አስተዳደር ቅሬታ ጥር 08/05/2008 ዓ/ም መቀሌ ለትግራይ ምክር ቤት ለወ/ሮ ቅዱሣን ነጋ፣ ለትግራይ ኘሬዝዳንት ጽ/ቤት ለህወሃት ጽ/ቤት፣ ለትግራይ ስብዓዊ መብት ኮሚሽን አቅርበን ወ/ሮ ቅዱሣን ነጋ ለተላከው ልዑክ ቃል በቃል “የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ የትግራይ ማንነት ተስጥቶት ያደረ ስለሆነ የአማራ ማንነት አያስፈለገውም” ብለው መልስ ሲሰጡ አቶ አባይ ወልዱ ካቢኔአችው ሰብስበው “በወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት የሚጠይቁ ጠላቶች ተነስተውብናል። ሰለሆነም የትግራይ ህዝብ ተነሰ” ብለው የቅስቀሳ መግለጫ ሰጥተዋል።

ይህን መነሻ በማድረግ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ 82 ሰው ያለበት በቅሬታ ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት ጥር 19/05/2008 ዓ/ም አዲስ አበባ የሄድን መሆናቸንን ይታወቃል። በዚህ ቀን የህወሃት አፋኝ ቡድን እንጦጦ ላይ በማገት በምክትል ኮማንደር ፅጋቡ ረዳ ህድሩ መሪነት ወደ ስሉልታ በመመለሰ ለ3 ቀን ጫንጮ ከተማ እንድንቆም እንደተደረገ ይታወሳል፡፡ ዋና ምክንያቱ ጥያቄአችሁን አቁሙ እና ተመለሱ ነበር፡፡ ነገር ግን ከእገታ በኋላ ጥር 25/05/2008 ዓ/ም ፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥያቄያችንና ያለን ቅሬታ አቅርበን ሰንወጣ 20 የኮሚቴ አባላት ታፍነን ማእከላዊ ገብተን በዚሁ ኮማንደርና ሌሎች የህወሐት ባለስልጣናት በድጋሚ ማስጠንቀቂያ ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት ተለቀናል።

በ26/05/2008 ዓ/ም ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ ያለው አባተ ፊት ቀርበን ቅሬታችን አቅርበን ወጥተናል። “ከዛም በኋላ መመዘኛው ተሟልቷል” ብሎ ፌዴ/ም/ቤት ተቀብሎናል። ይህን ተከትሎ መጋቢት 26/07/2008 ዓ/ም ለትግራይ ክልል መንግስት መልስ እንዲሰጡበት የተፃፈ ደብዳቤ ግልባጭ ደርሶን በእጃችን ይገኛል፡፡ ጭብጥ ሀሳቡም የማነንት ጥያቄው ህጋዊና ህገ- መንግሰታዊ ጥያቄ መሆኑ ፌዴሬሽን ም/ቤት አምኖበታል። ይሁን እንጂ የትግራይ ክልል መንግሰት የማንነት ጥያቄው መልስ እንዲሰጥበት በአቶ ያለዉ አባተ የተጠየቀበትን አፈ-ጉባዔ ኬሪያ ኢብራሂም ያውቃሉ። ከዚህ በመነሳት ህወሃት የማንነት ጥያቄዉን እንደ ልማዱ ላለመመለሰ ኮሚቴውን አፍኖ ለማጥፋት በ05/11/2008 ዓ/ም ጎንደር ከተማ ጦርነት እንደከፈተ ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም ከማወቅ በላይ ለአፋኝ ቡድኑ ውሣኔ ሰጥተው እንደላኩ ይታወቃል፡፡

አሁንም “የወልቃይት ጠገዴ የአማራ የማንነት ጥያቄ በትግራይ አድርጎ አልመጣም” የሚሉትን ፍፁሞ ሃሰት ነው፡፡ ከማመልከትም በላይ ታፍነናል፣ ታስረናል፣ ተገድለናል። ይህን ሁሉ እያወቁ የሰጡት መልስ ለወልቃይት ጠገዴ አጠቃላይ ለአማራ ህዝበ ካላቸው ንቀት የመነጨ አንደሆነ ያመለክታል። ይህ ብቻ ሳይሆን አሁንም ከህውሃት ወገንተኝነት ወጥተው ለኢትዮጵያ ህዝብ በሚዛናዊ የቆሙ አይመስሉም።

አሁንም ጥቅምት 06/02/2011 ዓ/ም የወልቃይት ጠገዴ ቅሬታ ይዞ በማመልከቻ ወደ መስሪያቤታቸው ሂዶ በቢሮአቸው እያሉ “የሉም ወደ ውጭ ለትምሕርት ሄደዋል” በማለት የተላከው ልኡክ ሳያነጋግሩ መልሰዋል፡፡ ወይዘሮዋ በህወሃታዊ አመለካከት ተጠፍረው የህዝብ ጥያቄ በትክክል እያዩት አደለም። ስለሆነ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝቦች ህወሃት በህግ ሳይሆን በጉልበት የያዝኩት አከባቢ ስለሆነ አሁንም በጉልበት ካልሆነ በህግ አልመልስም እያለ እንደሆነ ህዝባችን ሊረዳ ይገባል፡፡

ከዚህ በኋላ መላ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝባችን ሳንፈልግ በግድ መገዛት ይብቃ! ለህወሃት የሚሆን ህግ በኢትዮጵያ ከሌለ በምንችለው ራሳችንን ማዘጋጀት እንደሚጠበቅብን ማሰብ ተገቢ ነው። ኮሚቴው ለአራት ዓምታት ያህል የህግ ያለህ ብሎ ደክሟል የህውሃት አመራሮች በመቀሌና በፌዴሬሽን ም/ቤት ሆነው ጥያቄውን ኢ-ፍትሃዌ የሆነ መልስ ሲሰጡበት ማነህ የሚል የማዕከላዊ መንግስት አጥተናል።

የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ!

ጥቅምት 17/2011

ጎንደር/አማራ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *