የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አወጣ የተባለው መግለጫ መንግስት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት በማዝመት ሰላማዊ ሰዎችን እየገደለና ንብረታቸውን እየዘረፈ መሆኑንን አትቷል። የሰላም ስምምነቱን ለመተግበር ያጋራ ኮሚቴ ተቋቁሞ ለውጡን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመተግበር እየሰሩ መምሆኑንን ያወሳው መግለጫ መንግስት ለምን ሃይል እንደተጠቀመ አላብራርም።

በትዕግስት በመመካከር ከመስራት ይልቅ ሸርና ደባ እየተሰራበት እንደሆነ ያስታወቀው ኦነግ፣ ተሰራብኝ ያለውን ሸፍጥ አላብራራም። ምክንያቱ በግልጽ ባልታወቀ ሁኔታ ጦርነት እንደተከፈተበት ያወሳው ኦነግ ” ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ በቄሌም ወለጋና በጉጂ ዞን ኣከባቢዎች እየተፈጸሙ ያሉት ሁኔታዎች ለዚህ ጉልህ ማስረጃ ናቸዉ። ይህ ሁኔታ ደግሞ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር፣ ክቡር የሰዉ ህይወት ያለ ኣግባብ እንድጠፋ፣ እንድሁም የሕዝብና የሃገር ንብረት እንድወድም፣ አልፎ ተርፎም ሕዝቡ በስጋት፣ በጥርጣሬና በፍርሃት ድባብ ስር እንዲኖር እያደረገ ይገኛል” ይላል።

መንግስትም ሆነ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ኦነግ ትጥቅ እንዲፈታና ወደ አገር ቤት ሲገባ በገባው ቃል መሰረት በሰላማዊ መንገድ ትግሉን እንዲያካሂድ ደጋግሞ ማስጠንቀቁ ይታወሳል። ሶስት ባለቤት ካሉት ኦነግ የአንዱ መሪ የሆኑት አቶ ዳውድ ኢብሳ ” ማነው ትጥቅ አስፈቺ፣ ማን ነው ትጥቅ ፈቺ” በማለት የምንግስትንና የክልሉን ጥሪ እንደማይቀበሉ በመንግስት ሚዲያ ቀርበው መናገራቸው ይታወሳል። ይህንኑ ተከትሎም አቶ ጸጋዬ አራርሳ፣ አቶ ጃዋር መሐመድ የመሳሰሉት የኦሮሞ አክቲቪስቶች መንግስት ህግ ማስከበር እንደሚገባው ማሳሰባቸው አይዘነጋም።

በተደጋጋሚ አቶ ዳውድ በሳቸው የሚመራው ኦነግ ትጥቅ እንዲፈታ ንግግር ቢደረግም አሻፈረኝ በማለታቸውና በሰፊው ኦሮሚያ ተቀባይነትም ስለሌላቸው መንግስት ሃይል ለመጠቀም መወሰኑ ተሰምቷል። በምዕራብ ወለጋ አካባቢ ተሰሚነት ያላቸው አቶ ዳውድ የሚመሩት ኦነግ ያወጣው መግለጫ የንደራደር ጥሪ ይሁን የሌላ በውል አልታወቀም። ነገር ግን የነፍጥ ትግል ጥሪያቸው መሐል ኦሮሚያና ምስራቅና ደቡብ ክፍል የሚዘልቅ ባለመሆኑ በቅርቡ ፈተና ውስጥ ይወድቃሉ ተብሎ እንደሚገመት ስለጉዳዩ የሚያውቁ ይናገራሉ። 

መንግስት ወጥቶች በስህተት ትምህርትና በማይጠቅም ዓላማ ተታለው ዘመናዊ መሳሪያ ከታጠቀ ሃይል ጋር ጦርነት ለመግጠም ጫካ የገቡትን እንዲመለሱ ሲመክር ሰብቷል። የአካባቢው ሽማግሌዎችም ይህንኑ ስራ ሲሰሩ እንደቆዩ ተመልክቷል። በአሶሳ አካባቢ የ፲ ዓመት ህጻናትን ሳይቀር በመልመል ወታደራዊ ስልጠና ይሰጥበት የነበረ ማዕከል መደምሰሱና ከሃምሳ በላይ ታዳጊዎች መያዛቸውን የመንግስት ሚዲያ መዘገቡ ይታወቃል። በቅርቡም አስር የሚሆኑ አሰልታኞች መያዛቸው ይታወሳል።

መግለጫው እነድሚከተለው ነው። የቃላት ግድፈቱን ለማረም ያልሞከርነው የሃሳብ ለውጥ አስከተለ የሚል ቅሬታ እንዳይነሳ ነው።

ከኦነግ ዛሬ የተሰጠ መግለጫ

ያለ አግባብ ለሚጠፋው የሰዉ ሕይወትና ንብረት ተጠያቂነት ልኖር ይገባል

ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ የጦር ሠራዊቱን በሕዝባችን ላይ በማዝመት ሰላማዊ ሰዎችን መግደልና የሰዎችን ንብረት መዝረፍ ዛሬም ድረስ ቀጥሎበታል። ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ በቄሌም ወለጋና በጉጂ ዞን ኣከባቢዎች እየተፈጸሙ ያሉት ሁኔታዎች ለዚህ ጉልህ ማስረጃ ናቸዉ። ይህ ሁኔታ ደግሞ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር፣ ክቡር የሰዉ ህይወት ያለ ኣግባብ እንድጠፋ፣ እንድሁም የሕዝብና የሃገር ንብረት እንድወድም፣ ኣልፎ ተርፎም ሕዝቡ በስጋት፣ በጥርጣሬና በፍርሃት ድባብ ስር እንድኖር እያደረገ ይገኛል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባርና የኢትዮጵያ መንግስት ስምምነታችንንና በሕዝቡ ዉድ መስዋዕትነት የተግኘዉ የለዉጥ ሂደት በኣስተማማኝ መልኩ ስር በመስደድ ስኬታማ እንድሆን በማድረጉ ሂደት ላይ የሚሰራ ኣንድ የጋራ ኮሚቴ መስርተን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን። በዚህ የጋራ ኮሚቴ አመካይነትም በቋሚነትና በቀጣይነት ተገናኝተን እየተመካከርን በመስራት ላይም እንገኛለን።

ይህንን ሂደት የሰዉ ሕይወት መስዋዕትነትን በማይጥይቅ መልኩ፣ በሀገርና በሕዝብ ንብረት ላይም ጉዳትን በማያስከትል ሁኔታ፣ እንድሁም፣ ያለምንም ጥድፍያና ወከባ ጊዜ ወስደን በመመካከርና በቀና መንፈስ አብረን በመስራት ማሳካት እንደሚቻል የድርጅታችን የኦነግ ጽኑዕ እምነታችንና ኣቋማችንም ነዉ።

ይሁን እንጂ በመንግስት ኣንዳንድ ኣካላትና ግለ-ሰቦች እንድሁም በኢሕአዴግ በቀጣይነት የሚካሄዱብን ኣፍራሽ ፕሮፓጋንዳዎችና ገደብ ያጡ ሸርና ደባዎች የሕዝቡንና የሀገርን ሰላም የሚጎዱ ስለመሆናቸዉ በግልጽ የሚታይ ሓቅ ነው። ስለሆነም እንደነዚህ ኣይነቶቹን ሸርና ደባዎች፣ እንድሁም ኣፍራሽ ፕሮፓጋንዳዎች በሚመለከታቸዉ ኣካላት ኣስፈላጊ ክትትልና ቁጥጥር ተደርጎባቸዉ ማስቆም እንደሚገባ እስከዛሬ ስናስገነዝብ ቆይተናል። ይህንን ያደረግነው ተስማምተን የገባንበትን የሰላምና የእርቅ ሂደት በስኬት ለማጠናቀቅ ይረዳ ዘንድ መሆኑን ማስገንዝብ እንወዳለን። ይህ ደግሞ ለሕዝብና ለሃገር ሰላምና ደህንነት በቅንነት ከማሰብም እንደሆነ ልታወቅ ይገባል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ምክንያቱን በትክክል ለመረዳት አዳጋችና ኣስቸጋሪ በሆነብን ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግስት ሃገር በጠላት የተወረረች ይመስል ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ የጦር ሠራዊቱን በሕዝባችን ላይ በማዝመት ሰላማዊ ሰዎችን መግደልና የሰዎችን ንብረት መዝረፍ ዛሬም ድረስ ቀጥሎበታል። ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ በቄሌም ወለጋና በጉጂ ዞን ኣከባቢዎች እየተፈጸሙ ያሉት ሁኔታዎች ለዚህ ጉልህ ማስረጃ ናቸዉ። ይህ ሁኔታ ደግሞ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር፣ ክቡር የሰዉ ህይወት ያለ ኣግባብ እንድጠፋ፣ እንድሁም የሕዝብና የሃገር ንብረት እንድወድም፣ ኣልፎ ተርፎም ሕዝቡ በስጋት፣ በጥርጣሬና በፍርሃት ድባብ ስር እንድኖር እያደረገ ይገኛል።

ኣሁን ባለዉ ሁኔታ በጦርነትና በሓይል መፍትሔ ልገኝለት የሚችል ችግር እንደሌሌና ለሕዝብም ሆነ ለሃገር ከጦርነት የሚገኝ ትርፍ ወይም ጥቅም እንደሌሌ ኦነግ በጽኑዕ ያምናል። በሕዝቡ ትግልና መስዋዕትነት በተግኘዉ የለዉጥ ሁኔታ ላይ እንቅፋት ልሆንና የሕዝቡን ተስፋ ልያጨልም የሚችል ይህ ኣሳዛኝ ኣካሄድ በኣስቸኳይ እንድቆምም እንጠይቃለን። ይህ ኣካሄድ በሚያስከትለዉ ኣደጋ ለሚደርስ የሰዉ ህይወት መጥፋት፣ እንድሁም በሕዝብና በሃገር ንብረት ላይ ለምደርስ ዉድመት ሃላፊነት/ተጠያቂነት ልኖር እንደሚገባም ኦነግ ኣጥብቆ ያሳስባል።

Via Dawit Endeshaw of The Reporter Newspaper

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   እንግሊዝ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እቅዷን ይፋ አደረገች፤ ዶክተር ዳንኤል የማይካድራን ጂኖሳይድ ዝም ማለቱ ክህደት ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *