ትህነግ/ህወሓት የወልቃይት ጉዳይ ሲያስጨንቀው አዲስ ማደናገሪያ ጀምሯል። የራሱን የወልቃይት ኮሚቴ በማዋቀር የወልቃይትን ጥያቄ ወደምታፍነው ኬርያ ኢብራሂም ልኳል።

1ኛ) ቄስ ተሻለ (ትውልዱ ሽራሮ የሆነ)

2ኛ) ስዩም ኪዳኔ (ትውልዱ አድዋ የሆነ)

3ኛ) ዳኘው ወልዴ (ወልቃይት ለለቅሶ በገንዘብ “ወዬታ” የሚያቀርብ)

4ኛ) ሲሳይ ገዛኸኝ (የወልቃይት ተወላጅና ሁመራ ውስጥ የቀበሌ 2 አስተዳደር) የሚመሩት 20 ግለሰቦችን በኮሚቴነት በማዋቀር “ወልቃይት የአማራም አይደለም፣ የትግራይም አይደለም፣ ራስ ገዝ መሆን አለበት” የሚል ኮሚቴ አዋቅረዋል።

ከኮሚቴዎቹ መካከል እነ ፀጋዬ በርሄን ሲያማክሩ የነበሩና የትህነግ/ህወሓት ባለስልጣናት የነበሩም ይገኙበታል። አብዛኛዎቹ በመንግስት ስልጣን ላይ የሚገኙ ሲሆኑ ወጫቸውንም የትግራይ ክልል መንግስት ሸፍኖ እየተንቀሳቀሱ ነው።

ትህነግ/ ህወሓት የወልቃይት ጥያቄ ላይ ማደናገሪያ ለመፍጠር ያቋቋማቸው ኮሚቴዎች ከትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች መጥተው በትግራይ ክልል መንግስት ወልቃይት ውስጥ ሰፈራ የተሰጣቸውን የትግራይ ተወላጆች እና ትግራይ ውስጥም እስከ ሽራሮ ድረስ ፊርማ ማሰባሰባቸው ታውቋል።

“ወልቃይት ራስ ገዝ ይሁን” ብለው ማደናገሪያ አጀንዳ ይዘው ብቅ ያሉት የትህነግ/ህወሓት ኮሚቴዎች በዛሬው ዕለት በትግራይ ክልል መንግስት ወጭ ከሁመራ ወደ አዲስ አበባ በአውሮፕላን መጓዛቸው ታውቋል። የወልቃይትን ጥያቄ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤነትን ተጠቅማ ስትመልስ የከረመችው የትህነግ/ህወሓት ስራ አስፈፃሚዋ ኬሪያ ኢብራሂም ለእነዚህ የማደናጋሪ የትህነግ/ህወሓት ኮሚቴ አባላት የምትለውን በቅርቡ የምንሰማው ይሆናል! ትክክለኛውን የወልቃይት ጠገዴ ኮሚቴ ትህነግ/ህወሓት ያሳድደዋል፣ ኬርያም በትህነግ/ህወሓት አቋም ስትመልሰው ቆይታለች። ይህኛውን ኮሚቴ ትህነግ/ህወሓት አቋቁሞ ወደ ራሱ አመራር ቢሮ ልኮታል። ኬርያ የምታደርገው ግልፅ ነው! ይህ የእነማን ሴራ እንዳለበት ግልፅ ነው!

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   በሳሊቫኪርና በሪክ ማቻር መካከል እያገረሸ ያለውን ቅራኔ እየተባባሰ በመምጣቱ በደቡብ ሱዳን አዲስ ግጭት እንዳያገረሽ ተሰግቷል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *