‹‹ኢትዮጵያ ማንም ተነስቶ በወደደው ልክና መልክ እንደ ቂጣ ጠፍጥፎ የሚጋራት የግል ርስት ሳትሆን ዘመናትን ያስቆጠረች ታላቅ ሕዝብ የፈጠራት ታላቅ ሀገር ነች፡፡እሳት ቢያንቀላፋ ገለባ ጎበኘው እንዲሉ ኢትዮጵያ ደክማ ይሆናል እንጅ አልተሸነፈችም፤ እምዬ ቀጥና ይሆናል እንጅ አልተበጠሰችም፡፡ ኢትዮጵያዊ ሆኖ የኢትዮጵያን ክፉ የሚመኝ ጤነኛ ሰው አለ ብዬ አላምንም፡፡››

• ስላከበራችሁኝ እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ! አንድ ሆናችሁ ስላኮራችሁኝ አንድነታችሁ እንዳይወሰድባችሁ እጸልይላችኋለሁ!
በፍራንክፈርት በዓይነስጋ መተያየታችንን እንደ ታላቅ ዕድል እቆጥረዋለሁ፡፡
ከአገር የወጣችሁበት ምክንያት እንደ ቁጥራችሁ ብዙ ነው፡፡ 
ሀገራችን ኢትዮጵያ በችግሯ ከመታወቋ በፊት ከአውሮፓውያን ጋር ታሪካዊ ግንኙነት ነበራት፤ ከእንግሊዝ በትምህርት፣ ከፈረንሳይ በባቡር፣ ከቱርክና ግሪክ በንግድ፣ ከሩሲያ ጋር በጦር አጋርነት፣ ነበረን፡፡
ፍራንክፈርት የወልፍ ጋንግ ከተማ ነች፡፡ የጀርመን የባሕል ማዕከል መቋቋሙ የጠንካራ ትስስራችን ማሳያ ነው፡፡
እንደ ሀገር ከጀርመን እንደ አጠቃላይም ከጀርመን ጋር የሚያመሳስለን ብዙ ነገር አለ፡፡
በ2ኛው የዓለም ጦርነት ከተጎዱ፣ መኖሪ ቤቶ ፍርስራሽ የሆኑባት የጦር አውድማ ሆና፣ ዋነኛ የንግድ ማዕከላቸው ፍራንክፈርት ወድመዋል፡፡ ጀግኖቹ ጀርመኖች ግን መልሰው ለመገንባት 40 ዓመት አልፈጀባቸውም፡፡ ይህ ለኛ ትልቅ ትምህርት ነው፡፡
20ዓመት ባልሞላ ጦርነት አውሮፓውያን ሚሊዮኖችን አጥተዋል፤ ተሰደዋል፣ ቆስለዋል፤ ሞተዋል፡፡ ያ ሁሉ የመጣው በጥቂት ጥቅማቸው የኛ ዘር ይበልጣል ባሉ መሪዎች የጦርነት ጠባሳ ነው፡፡ አሰቃቂው ጦርነት ትርፉም ጦርነት፣ ድኅነት፣ ስደት፣ ሞት፣ … ነበር፡፡ ግን በፍጥነት አገግመው ሚሊዮኖችን እስከማስጠለል ደረስዋል፡፡ 
እርስ በእርስ ከመጠላለፍ ወጥተው ለነገ ሲሉ የደረሰባቸውን መከራ ረስተው በትጋት ለነገ ሠርተው ነው ከዚህ የደረሱት፡፡
ከዚህ ከፊት ከፊታችሁ ስቆም ሀገራችን ሰላም ሆና፣ ግጭት ቀርቶ፣ በፍቅር እየሠራን ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ግን አሁን በእጃችን ያለው ነፃነትና ተስፋ ብቻ ነው፡፡ 
ዘረኝነትና የበላይት አባዜን አውሮፓ አምርሮ የተዋጋው ካደረሰበት ጥፋት ስለተረዳ ነው፤ ይህ ለኛ ከፍተኛ ትምህርት ይሰጠናል፡፡ የኛ የፖለቲካ ጉዞ በማሳደድና በመሰደድ የተመሠረተ እንደነበር ግልጽ ነው፡፡ 
አሁን ለሀገራችን በተባበረ ክንድ የምንተጋበት ወቅት ነው፡፡ በየጎራው ያሉ ኃይሎች አሸናፊ የሚሆኑበትን እና ሀገራችን አብረን የምንገነባበትን መንገድ መከተል አለብን፡፡
ኢትዮጵያ ማንምተነስቶ በወደደው ልክና መልክ እንደ ቂጣ ጠፍጥፎ የሚጋራት የግል ርስት ሳትሆን ዘመናትን ያስቆጠረች ታላቅ ሕዝብ የፈጠራት ታላቅ ሀገር ነች፡፡
እሳት ቢያንቀላፋ ገለባ ጎበኘው እንዲሉ ኢትዮጵያ ደክማ ይሆናል እንጅ አልተሸነፈችም፤ እምዬ ቀጥና ይሆናል እንጅ አልተበጠሰችም፡፡
ኢትዮጵያዊ ሆኖ የኢትዮጵያን ክፉ የሚመኝ ጤነኛ ሰው አለ ብዬ አላምንም፡፡
ከትናንት መልካም ነገሮችን ብቻ ሳይሆን መስተካከል ያለባቸው ነገሮችንም ወርሰናል፡፡ በትናንት ላይ እየተጨቃጨቅን ሳይሆን በጎ ሐሳብን ወደ ተግር በመቀየር ብቻ ማተኮር ይኖርብናል፡፡
በማኅበራዊ ሚዲያ ተጥደን ሳይሆን ትርጉም ያለው ሥራ እንሥራ፡፡
በጨለማው ውስጥ ሆነን ሻማ ማብራት እንጅ ስለጨለማው መስበክ አይበጀንም፡፡
ፍትሕና ዴሞክራሲ በማኅበራዊ ሜዲያ ጧት ተዘርተው ማታ የሚደርሱ አይደሉም፡፡ እነሱን የሚያበቅሉ የዳበሩ ተቋማት ያስፈልጋሉ፡፡ ቡቃያ ሆኖ የሚያጓጓን የለውጥ ሰብል የስልጣና የለውጥ ነዶ የሚያሳቅፈን ተደምረን ዛሬ ስንሠራ መሆኑን ለአፍታ መዘንጋት የለብንም፡፡
ፍትሕና ዴሞክረሲ ሊሸከሙ የሚችሉ ተቋማት በመገንባትና ለእነዚሁ ተቋማት የሚመጥኑ ባለሙያዎችን በመምረጥ በማሰልጠንና በመመደብ ላይ እገኛለን፡፡
ምርጫ ቦርድ ነፃ ተአማኑና ገለልተኛ እንዲሀጎን ለማድረግ የሕግና ማሻሻያ ስራ ላይ እንገኛለን፡፡
የሕና ፍትሕ ተቋማት የዜጎች መብት ጠብቀው እንዲሰሩ መሻሻያ ላይ እንገኛለን፡፡

መከላከያ ሠራዊታችን የዘመነና ሀገራችን ታፍራ እንድትኖር የሚያደርግ እንዲሆን ከሌሎች ሀገራት ጋር ጭምር በመሥራት ላይ እንገኛለን፡፡

በቅርቡ ተከታታይ እርምጃዎችን በፍትሕ ዘርፉ ላይ እንወስዳለን፡፡
በካቢኔዎቻችን ላይ የታየውን የፆታ ስብጥር በፍትሕ ዘርፉ እንደግመዋለን፡፡
የትምህርት ፍኖተ ካርታችን ዓለማቀፍ ተወዳዳሪነትን የሚያመጣ ሆኖ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡
የትናንቱን ዝንፈት ከማረም ጎን ለጎን አሁን ላለው ትውልድ ሥራ መፍጠር፣ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶች እንዳይፈጠሩ ለማድረግ፣ ሰባቱንም ቀናት ሌት ተቀን እንደምንሠራ አረጋግጥላችኋለሁ፡፡
በሦስት ግንባር የከፈትነው ጦርነት በድል እንደሚጠናቀቅ አልጠራጠርም፤ አትጠራጠሩ፡፡
የደቡብ ኮሪያው ጀኔራል ፓርክ በጀርመን በነበሩት ዲያስፖራዎች መዋጮ ሀገራቸውን ገንብተዋል፤ እናንተም ከማኪያቶ ወጫችሁ አንድ ዶላር ለኢትዮጵያ እንድትለግሱ በድጋሜ እጠይቃችኋለሁ፡፡ 
ከተባበርንና አንድ ከሆንን፣ በትንንሽ የተጣዱ ጉዳዮች መጠመዱን ትተን ለትልቁ ስዕል ከተጨነቅን፣ ቆፍጠን ብለን ከሠራን ይቻላል፤ የድል ነጋሪትም በዓለም ላይ ይጎሰማል፡፡

እኔ ዛሬ ከዚህ የቆምኩት እናንተ አምባሳደሮች ናችሁ፤ ከእናንተ ፊት የቆምኩት ከኮሪያውያን ስለተማርኩ እንደማታሳፍሩኝ ስለማምን ነው፡፡ እዚህ የምታገኙትን አገር ቤት ያለው ዘመዳችሁ ተጠቃሚ መሆኑ ድንቅ ነው፡፡ ለራሳችሁ በኪራይ እየኖራችሁ የወላጆቻችሁን ቤት ትሠራላችሁ፤ እናንተ ቀን ከሌት እየሠራችሁ ታናናሾቻችሁን ታስተምራላችሁ፡፡ ይህንን የምታደርጉት ሀገራችሁን ስለምትወዱ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ከአውሮፓ የአምስት መቶ አመት ትውውቅ አላት፡፡ እንደቀደሙት ወገኖቻችንም ዕውቀትን አሻግሩ፤ ወደ ሀገራችሁ ፣ሞጥታችሁም ተግባራዊ አድርጉ፡፡
ከማንም አትጠብቁ፤ ኢትዮጵያ የእናንተ ናትና፡፡ ሰው የእናትና አባቱን ቤት በማገዝ እንጅ በማማረር ለውጥ አምጥቶ አያውቅም፡፡ ማን ለማን ያማርራል? 
ኦሮሞው፣ አማራው፣ ሶማሌው፣ ጉራጌው ፣… በሚል ሳንለያይ የአንድነት መዝሙር እየዘመርን ወደፊት ብቻ እንጓዝ!
ከብዙ ዓመታት በፊት በአውሮፓ በዚህ ወቅት በበረዶ ብዙዎች ይሞቱ ነበር፡፡ ከችግሩ ግን የቅዝቃዜውን ማሞቂያና የሙቀቱን ማቀዝቀዣ ፈለሰፉ፤ ከችግራቸውም ተማሩ፡፡ እኛም ይህንን እንከተል፡፡
በአንድነት እንነሳ፡፡ ትናንት ከኛ ውጭ ነው፤ ከተጠቀምንበት ያለንም ያለነውም ዛሬ ነው፡፡ ማግለልን ሳይሆን ማቀፍን ከተከተልን ነገ ወርቃማ ዕድል ሆኖ ይጠብቀናል፡፡
በስደት የሚኖሩ ሕዝቦቿ እንደሚሰበሰቡ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
በሳሀራ በረሃ በቀቢጸ ተስፋ የሚሰደዱበት ጊዜ እንደሚቆም ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
ልጆቻችን ወደ አውሮፓ ለጉብኝት እንጅ ለስደት የማይመጡበት መንገድ እንደሚመጣ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
ልጆቻችን ስማችንን በክብር በበጎ እንደሚያነሱ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
በአዲስ አበባ የዛሬዋን ቀን እያስታወስን በእግራችን የምንዝናናበት ቀን እንደሚመጣ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
የትናንትን መጥፎ ታሪክ ዘግተን ነገን በተሻለ ሕይወት እንደምንኖር ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
ኢትዮጵያ በልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር! 
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቿን ይባርክ! 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ጀርመን ፍራንክፈርት
በአብርሃም በእውቀት – (አብመድ)

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *