አሜሪካ ከገቡ በሁዋላ ራሳቸውን ከሚታይ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ቆጥበው የቆዩት ወይዘሮ ብርቱካን ሚደቅሳ በምንግስት ግብዣ ለሹመት አዲስ አበባ እንደሚገቡ የሚቀርቧቸው እየገለጹ ነው። ወደ አገራቸው መመለሳቸውን አስመልክቶ እሳቸውም ሆኑ መንግስት በይፋ ያሉት ነገር የለም።

የአንድ ልጅ እናት የሆኑትና በ፩፱፱፯ ድህረ ምርጫ ጀምሮ  እውቅና ያገኙት የቀድሞው የቀስተደመና ፓርቲ መስራች፣ ቅንጅት መንፍስ ነው የሚል እምነት ነበራቸው። ቅንጅት የሚለው ህብረት ከተፈጠረ በሁዋላ የገነኑት ወ/ሮ ብርቱካን በፖለቲካ እምነታቸው በእስር የከፋ ጊዜ አሳልፈዋል።

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

ከእስር በሁዋላ አየለ ጫሚሶ የቅንጅት ወራሽ እንዲሆኑ ሲደረግ አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ የተሰኘ ፓርቲ መስራችና ከአገር እስኪወጡ  ፓርቲውን በመምራት ወ/ሮ ብርቱካን ይታወቃሉ።

የፌደራል ፍርድ ቤት ዳኛ፣ ጠበቃ የነበሩት ወ/ሮ ብርቱካን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ ፣ ከዩናይትድ ስቴትስ ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ በሕዝብ አስተዳደር  ሁለተኛ ዲግሪ አላቸው።

መንግሥት ባደረገላቸው ጥሪ  የፊታችን ሐሙስ አዲስ አበባ እንደሚገቡ የተነገረላቸው ወ/ሮ ብርቱካን፣ መንግስት ሴቶችን ወደ ሃላፊነት ማምጣት በሚለው አዲስ እሳቤ ከሙያቸው ጋር በተያያዘ  ሹመት እንደሚሰጣቸው ከወዲሁ እየተነገረ ነው። ወ/ሮ ብርቱካንም ሆኑ መንግስት በጉዳዩ በግልጽ ያሉት ነገር ባይኖርም አዲስ አበባ የመግባታቸው ነገር የተረጋገጠ ነው።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

ከወ/ሮ መዓዛ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሹመት ማግስት ይህ ዜና መሰማቱ ምን አልባትም የወ/ሮ ብርቱካን ወደ አገር ቤት መመለስ ሹመታቸው ከሙያቸው ጋር በተያያዘ የመሆኑንን ጉዳይ ያጎላዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በጀርመን ለሕዝብ ባደረጉት ንግግር ሴቶችን ወደ አመራር ማምጣቱ የሚቀጥል ተግባር መሆኑንን ማረጋገጣቸው ይታወሳል።

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *