“Our true nationality is mankind.”H.G.

“የትግራይና አማራ ክልል ጦርነት ጀምሩ? ኢሳያስ አማራ ክልልን ይጎበኛሉ!!

Amhara is one of the nine ethnic divisions (kililoch) of Ethiopia, containing the homeland of the Amhara people. Previously known as Region 3, its capital is Bahir Dar.

የአማራና የትግራይ ክልል በመግለጫ በሚታኮሱበት በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን ሲዞርና ያሻውን ሲያደርግ ከርሞ ወደ አሜሪካ የተመለሰው አቶ ጃዋር መሐመድ የትግራይና የአማራ ክልል ጉዳይ ከቁጥጥር ውጪ ሳይሆን የፌደራል መንግስት ጣልቃ ገብነት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን በፌስ ቡክ ገጹ አመልክቷል። ይህንኑ የጃዋር መልዕክት ተንተርሶ ዳንኤል በርሃኔ የሚባለው የሆርን አፌርስ አዘጋጅ ጉዳዩን ለውይይት ጋብዞታል። አምላክ ሁላችንንም ይጠብቀን ብሏል።

መለስ በዘረጉት የፌደራል ስርዓት ኢትዮጵያ በቋንቋ በሚል ስትሸነሸን የትግራይ ክልል ቀድሞ ያሌለውን አግበስብሶ ወስዷል በሚል ጩኸት ቢሰማም የወቅቱ ኢህዴን የአማራ ክልል ወኪል ባለመሆኑና በክልሉ ተወላጆች ይመራ ስላልነበር ተከራካሪ አልነበረም። በዚሁ የተነሳ ችግሩ ሲብላላ ቆይቶ አሁን መፈንዳቱ አገሪቱን በየአቅጣጫው እሳት እንዳለበሳት የተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች በተደጋጋሚ እየገለጹ ነው።

፩.jpg

የትግራይ ክልል የቅማንት ተቆርቋሪ ሆኗል። አሁንም ይህንን ከታች ያለውን ዳንኤል ብርሃኔ ከሙሉቀን ያገኘውን ወስዶ የራሱን አስተያየት በማከል ለጥፏል።

፪.jpg

ዛሬ የአማራ ክልል ባወጣው መግለጫ ችግሩ እንዳለ ጠቁሞ የቅማንትን ህዝብ ከወንድሞቹ ለማጣላትና የተፈጠረውን ችግር የፖለቲካ ገባያ ለማድረግ የሚጠቀሙ ሃይሎች እንዳሉ አስታውቋል። ከመከላከያ ሃይል ጋር በመሆን የማረጋጋት ስራ እየተሰራና አንሳራዊ ሰላም እንዳለም አስታውቋል። አይይዞም ከዚህ ተግባር የፖለቲካ ትርፍ እናገኛለን ብሎ ማሰብ አግብባ እንዳልሆነ አመልክቷል።

መግለጫው በምዕራብ ጐንደር ዞን አዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ምስረታ በዓልን አክብረው እየተመለሱ ባሉ ወገኖች ላይ ማንነታቸው ለጊዜው ያልታወቁ ግለሰቦች ባደረሱት ጥቃት የ4 ሠዎች ህይወት ሊያልፍ ችሏል፡፡ በዚህ መነሻ በተፈጠረ ግጭት በዞኑ መተማ እና ሽንፋ አካባቢዎች በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን አመልክቷል። እነዚህ ማንነታቸው ያልታወቀና አድፍጠው ጉዳት ያደረሱት ክፍሎች እነማን ናቸው የሚለውን መግለጫው አፍርጦ አልተናገረም። ይሁንና እድኖ ለመያዝ ጥረት እየተደረገ መሆኑንን አመልክቷል።

ጉዳዩ በንዲህ እንዳለ ሰባት የሚሆኑ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ሃይሎች በከበባ መያዛቸው ተሰምቷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ መሸገው የሚዋጉና መከላከያን ጦርነት የገጠሙ ሃይሎች እንዳሉ ሙሉቀን ተስፋው አመልክቷል።

እነዚህን መሽገው የሚታኮሱትን ሃይሎች ሙሉቀን የመከላከያ ሃይሎችን ጠቅሶ ” ትግርኛ ተናጋሪ አዋጊዎች አሏቸው ” ብሏል። ዳንኤል በበኩሉ ለውትሮው ህወሃቶች የሚተሉዋቸውን አጼ ቴዎድሮስን ባምቆላመጥ በሙሉቀን መረጃ ግርጌ እንዲህ ብሏል። ” አጼ ቴዎድሮስን ያፈራውን ታልቁን የቅማንት ህዝብ የገዱ አንዳርጋቸውንና የአሳምነው ጽጌን ጀሌዎች እየገረፈ ይመስላል፤ የመይሳው ካሳና የግብርዬ ህዝብ ላይ ጥይት የተኮሰ እድሜውን አሳጠረ ” ሲል አወድሷል።

Related stories   ወደ ድርደር ? ከታንክ ወደ አህያ የወረደው ትህንግ በማን ሊወከል?

በራያ፣ በወልቃይት ጉዳይ የተወጠረው የትግራይ ክልል አስተዳደር አማራ ክልል ላይ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎችና አካባቢዎች እጅ አዙር ስራ እየሰራ መሆኑን በርካቶች እየገለጹ ነው። በቤኒሻንጉል በኩል የሚከወነውን ድራማ የሚጫወቱት እነሱ ስለመሆናቸው መንግስት መረጃ እንዳለውም ይነገራል። በዚህ ሁሉ ውስጥ ዜጎች እርስ በእርስ አሁንም ለመባላት ዝግጁነታቸው በከፍተኛ ደረጃ መነሳሳቱን የሚገልጹ ህወሃትን መውቀሱ አግባብ እንዳልሆነ ያስረዳሉ። ዞሮ የሚያፍሩት የራሳቸውን ወንድም የሚገድሉ ውሾች መሆናቸውንም ያክልሉ።

ይህ በንዲህ እንዳለ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፉወርቂ አርብ ባህር ዳር ይገባሉ። የኢሳያስ ጉብኝት በውል ባይገለጽም ከአማራ ክልል ጋር በገበያና በጸጥታ ጉዳዮች ላይ ስምምነት እንደሚደርሱ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ወገኖች ይናገራሉ።

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተሠጠ መግለጫ

Related stories   የሲኤንኤን ዘጋቢ ኒማ- በተወነችው ተውኔት ውስጥ ዳግም ሞት የተፈረደባቸው ዜጎች

በህዝቦች ትግል የመጣው ለውጥ እንዳይቀለበስ የተገኘውን ተስፋ ነፃነት እና ሠላም መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡

የሚታዩ ችግሮችንም በሰከነ መንገድ የህግ የበላይነትን አስጠብቆ መፍትሄ ለመስጠት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና ህዝብ እየሠሩ ይገኛሉ፡፡ ሰሞኑንም በምዕራብ ጐንደር ዞን አዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ምስረታ በዓልን አክብረው እየተመለሱ ባሉ ወገኖች ላይ ማንነታቸው ለጊዜው ያልታወቁ ግለሰቦች ባደረሱት ጥቃት የ4 ሠዎች ህይወት ሊያልፍ ችሏል፡፡ በዚህ መነሻ በተፈጠረ ግጭት በዞኑ መተማ እና ሽንፋ አካባቢዎች በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በግጭቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ይገልፃል፡፡ በሌላ በኩል አጋጣሚውን በመጠቀም ሁኔታውን በማባባስ ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ህዝባችን ችግሮችን በውል የመረዳት አስተውሎት ያለው በመሆኑ ችግሩ ወደ ከፋ ግጭት እና ጥፋት ሳይሄድ አካባቢው እንዲረጋጋ ማድረግ ተችሏል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፀጥታ ሀይሎች ከኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት አባላት ጋር በመሆን በአካባቢው ችግሩን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሠሩ ይገኛሉ፡፡ ከአካባቢው ህዝብ ጋር በመሆን መስዋዕትነት በመክፈል ጭምር ጥፋተኞች በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ እየተደረገ ያለውን ጥረት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በእጅጉ ያደንቃል፡፡
በጉዳዩ ላይ ቀጥተኛ ተሣትፎ በማድረግ ችግሩ እንዲፈጠር ያደረጉ ተጠርጣሪ ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር እየዋሉ ይገኛሉ፡፡

ግጭቱን የህዝብ ለህዝብ በማስመሰል ከዚህ ትርፍ ለማግኘት የሚደረግ ሙከራ ፍሬ አልባ እና ምንም መሠረታዊ መነሻ የሌለው ከንቱ ድካም መሆኑን የክልሉ መንግስት ያስታውቃል፡፡ ይህንን ዓላማ አድርገው የሚንቀሳቀሱ አካላት እና የዚህ አስፈፃሚ ግለሰቦችም ትርፋቸው ኪሣራ እንደሆነ ሊገነዘቡት ይገባል፡፡

በክልሉ በየትኛውም አካባቢ ህግን የሚፃረሩ ተግባራትን ለማስወገድ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና ህዝብ የሚሠሩ ሲሆን ህዝቡ ያገኘውን ሠላም ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ አካላትን በማጋለጥ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ለመወጣት ጥረት ማድረግ ይኖርበታል፡፡

በቀጣይ የክልሉ ህዝብን ሠላም ለማስጠበቅ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ ርብርብ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን እየገለፅን መላ የክልላችን ህዝቦችም የተገኘውን ሠላም እና ነፃነት በመጠበቅ ከመንግስት ጐን እንዲሰለፍ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0