“Our true nationality is mankind.”H.G.

አብዲ ኢሌ ምግብ አልተመቸኝም ይላል – 200 ሰዎች የተቀበሩበት የጅምላ መቃብር ተገኘ! አጫጭር ዜናዎች

ሁለት መቶ ሰዎች በጅምላ የተቀበሩበት መቃብር ተገኘ። የጅምላ መቃብሩ በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል  አዋሳኝ አካባቢ ነው። ፖሊስ በቁጥጥር ስር ባሉት የቀድሞ የሶማሌ ክልል መሪ አቶ አብዲ ኢሌ ላይ የሚያደርገውን ምርመራ ተከትሎ በጥቆማ የተገኘው የጅምላ መቃብር ነጹሃን ተጨፍጭፈው የተቀበሩበት ነው።
አዲሱ የሶማሌ ክልል መሪ የሰው ልጅ ሊሰራው ይችላል ተብሎ የማይገመት ድርጊት በክልሉ ሲፈጸም እንደነበር በጠቀሱበት ቃለምልልስ የጅማላ መቃብር መገኘቱን አስታውቀው ነበር። ቀደም ሲል ጀምሮ የክልሉ ነዋሪዎችና ቀና ሃላፊዎች ለሂውማን ራይትስ ዎች ጥቆማ ሰጥተው በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የጅምላ ግድያና አጸያፊ ተግባራት ሲፈጸም መቆየቱ ሲዘገብ ነበር። 
መለስ ዜናዊ የሚባሉት የቀድሞ ባለስልጣን ይህንን ተግባር የሚፈጽሙትን በዝምታ ማለፋቸው ሌላው የአሳዛኙ ተግባር አካል ነበር። ለዚህም ይመስላል ” ኦጋዴን የኢትዮጵያ ሃፍረት” በማለት ሂውማን ራይትስ ዎች ጠንካራ የተባለ ሪፖረት ያቀረበው። ይህንን ሪፖርትም ሆነ ሌሎች የሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ ሪፖርቶች ሲወጡ ” የሊብራሊዝም አቀንቃኞች” በሚል ጉዳዩን የርዕዮተ ዓለም ያስመስሉት ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ መሪነት ከመጡ ወዲህ በተወሰደ የሰለጠነና ጥንቃቄ የተሞላበት እርምጃ አብዲ ኢሌ እና አበሮቹ እስር ቤት ሲገቡ ክልሉ መልካም የተባሉ መሪ ለማግነት ችሏል። የመለስ ደጋፊዎችና በክልሉ ሲነገዱ የነበሩ ” ፍትህ ለአብዲ”  በማለት ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል። የስማሌ ክልል ልዩ ሃይል መከላከያን ደምስሶ ቤተመንግስቱን ተቆጣጠረ እያሉ ይዘግቡ ነበር።
አሁንያላለቀውን ምርመራ ይፋ ያደረገው ፖሊስ እንዳለው አሁን የተገኘው የጅምላ መቃብር ፪፻ የሚሆኑ ንጹሃን ዜጎች የተቀበሩበት ነው። ማንነታቸውንም ለመለየት ስራ እየተሰራ ነው። አሁንስ ፍትህ ለአብዲ ኢሌ የሚሉ ተዝካር ናፋቂዎች ምን ይሉ ይሆን!! 
ዛጎል ዜና

የሳዑዲ አረቢያ መራሹ ጥምረት በየመን ላይ በሚያደርገው የቦምብ ድብደባ ከዩናይትድ ስቴትስ ለጀቶቹ ያገኘው የነበረው የነዳጅ የመሙላት ውል ዛሬ መቋረጡን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገበ። ይህ ርምጃም ዋሽንግተን በአወዛጋቢው የየመን ግጭት ጦርነት የነበራትን ቁልፍ ተሳትፎ እንዲያከትም እንደሚያረገውም ዘገባው ገልጿል። ሳውዲ መራሹ የአውሮፕላን ጥቃት ለበርካታ ሲቪሎች እና ሕጻናት ሕይወት መቀጠፍ መንስኤነቱ ዓለም አቀፍ ትችት እያስከተለ ነው። እንደሳውዲ የዜና ወኪል ጥምረቱ ከአሜሪካ የሚያገኘውን ድጋፍ እንዲያቆም መጠየቁን ይፋ ካደረገ በኋላ፣ የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ጂም ማቲስ የሳውዲ አረቢያን ውሳኔ እንደሚደግፉ መግለፃቸውን ዘገባው አመልክቷል። ይህ ርምጃ የተሰማው የጥምረቱ አውሮፕላኖች ስልታዊ የሚባለውን የሆዴይዳን ወደብ በሚደበድቡበት ጊዜ፤ ዋሽንግተን ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾጊን በገደለው የሳውዲ የስለላ ቡድን ምክንያት ከሪያድ ጋር ያላት ትብብር ምርመራ እና ጫና በበዛባት ወቅት መሆኑንም ዘገባው አክሎ ገልጿል። ፔንታገን የመን ላይ ለሚያንዣብቡብት የጥምረቱ አውሮፕላኖች 20 በመቶ የሚሆነውን የነዳጅ ሙሌት ያቀርባል። DW Radio

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፤ የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሶማሊያው አቻቸው መሐመድ አብዱላሂ ማህሙድ ባሕር ዳር ላይ ትናንት እና ዛሬ ተከታታይ ዉይይት እና ምክክሮችን ማካሄዳቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባወጣው መግለጫ አመለከተ። መሪዎቹ ባለፈው አሥመራ ላይ በጋራ የተስማሙባቸውን የሦስቱን ሃገራት ወዳጅነት እና ሁሉን አቀፍ ትብብር በተመለከተ እድገት እና ስኬቱን መቃኘታቸውን መግለጫው ጠቅሷል። በዚህም አዎንታዊ ውጤቶች መመዝገባቸውን፤ በተጨማሪም በተናጠልም ሆነ በጋራ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በትብብር ለመቋቋም እና ለመረዳዳት መስማማታቸውም ተገልጿል። ሃገራቱ ለአካባቢው ሰላም እና ሁሉን አቀፍ ትብብርም ቁርጠኞች መሆናቸውንም አመልክተዋል። ሦስቱም መሪዎች የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ የጣለውን ማዕቀብ ማንሳቱን እንደሚደግፉም ተመልክቷል። መሪዎቹ በዛሬው ዕለትም በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተገነባውን ከፍተኛ ሆስፒታል በጋራ መርቀዋል። የኤርትራ እና የሶማሊያ ፕሬዝደንቶች በአማራ ክልል የሁለት ቀናት ጉብኝት እና ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ያደረጉትን ውይይት አጠናቅቀው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ቀጣይ ውይይታቸው መቼ እንደሚካሄድ ባይገለፅም መቅዲሹ ላይ እንደሚደረግ ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። DW Radio

በሩብ አመቱ የንግድ ገቢ ግብር ካሳወቁ ነጋዴዎች 77 በመቶዎቹ ኪሳራና ባዶ ያሳወቁ ናቸው ሲል የገቢዎች ሚኒስቴር ተናገረ

ከ2 ሺህ 915 ግብር ከፋዮች መካከል በትክክል ግብራቸውን ከክፍያ ጋር ያሳወቁት 961 ብቻ ናቸው ብሏል፡፡ቀሪዎቹ 1 ሺ 954 ያህሉ ወይም 77 በመቶዎቹ ኪሳራና ባዶ ያሳወቁት በሀሰተኛ ደረሰኝ ስለሚጠቀሙ ነው ተብሏል፡፡የገቢዎች ሚኒስቴር ለሸገር እንደተናገረው ሀሰተኛ የንግድ ፈቃድና አድራሻ ያላቸው ሀሰተኛ ድርጅቶች በሚሸጡት ህገ-ወጥ ደረሰኝ 4 ቢሊዮን ብር ግብይት ተፈፅሟል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ 124 ድርጅቶች በሀሰተኛ ደረሰኝ እንደሚሸጡ ደርሼባቸዋለሁ ያለ ሲሆን ባለፉት 3 ወራትም ኦዲት ከተደረጉ 563 ድርጅቶች 722 ሚሊዮን ብር በሀሰተኛ ደረሰኝ ግብይት ተፈፅሟል ብሏል፡፡ 

Related stories   ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ

በጥቅምት ወር ብቻ 385 ሚሊዮን ብር በሀሰተኛ ደረሰኝ ግብይት መፈፀሙን በ383 ድርጅቶች ላይ በተደረገ የኦዲት ምርመራ መረጋገጡን ሰምተናል፡፡ በመሆኑም ነጋዴዎች በአነስተኛ ደረሰኝ የፈፀማችሁት ግብይት በገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ተቀባይነት እንደሌለው እወቁት ተብላችዋል፡፡ የሻጭ ድርጅቶችን የንግድ ፈቃድ ትክክለኛነት የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥርና የማሽን ቁጥር በትክክል አመሳክሮ ደረሰኝ መቀበሉን አትዘንጉ ተብላችኋል፡፡ የሻጭ ድርጅቶች ትክክለኛ አድራሻ እንዳላቸው ካላረጋገጣችሁ የሂሳብ መዝገባችሁ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውም ተብላችዋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን – sheger Radio

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው አመት ይካሄዳል ተብሎ ለሚጠበቀው ምርጫ ዝግጅት አለመጀመሩን ተናገረ

ምርጫው ፍትሃዊ እንዲሆንና በህዝብ ድምፅና ይሁንታ ብቻ ስልጣን የሚያዝበት ይሆናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ቃል ለተገባለት ለዚህ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ ለመፎካከር ከአገር ውጪ የነበሩ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጭምር ወደ አገር መግባታቸው ይታወቃል፡፡ይሁንና ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እስካሁን ዝግጅት አለመጀመሩን የቢሮው ምክትል ሀላፊ አቶ ወንድሙ ጎላ ለሸገር ተናግረዋል፡፡ አቶ ወንድሙ እክል አለበት የተባለው የምርጫ ህግ ተሻሽሎ አለመፅደቁ፤ ምርጫ ቦርድም እንደ አዲስ ይደራጃል ቢባልም እስካሁን ተግባራዊ አለመሆኑ ዝግጅት ላለመጀመራችን ምክንያት ነው ብለዋል፡፡ምርጫው የቀረው ጊዜ አመት ከመንፈቅ ብቻ ነው፡፡

Related stories   ወደ ድርደር ? ከታንክ ወደ አህያ የወረደው ትህንግ በማን ሊወከል?

ትዕግስት ዘሪሁን – sheger Radio

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ በሆስፒታሉ ለሚገኙ ታካሚዎች የሚያቀርበውን ኦክስጅን ማምረቻ አስመረቀ

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ በሆስፒታሉ ለሚገኙ ታካሚዎች የሚያቀርበውን ኦክስጅን ማምረቻ አስመረቀ፡፡ በመቶ ሚሊዮን ብር የተገነባው የኦክስጅን ማምረቻ ፕላንት ለህክምና አገልግሎት የሚውል የተጣራ ጋዝ እዛው በማምረት በሆስፒታሉ ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን በየክፍሎቻቸው በተዘረጋ መስመር እንዲደርስ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡ከዚህ ቀደም ከሌሎች አቅራቢ ድርጅቶች የሚገዛው ለህክምና አገልግሎት የሚውል ኦክስጅን በሚፈለገው ጥራት እና ዓይነት ለማግኘት አስቸጋሪ እንደነበር የሆስፒታሉ የምህንድስና ዘርፍ ዳይሬክተሩ አቶ አስፋህ ሰለሞን ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ከሰባት መቶ እስከ 1 ሚሊዮን ብር ድረስ በየወሩ ለኦክስጅን ጋዝ ግዢ የሚወጣውን ወጪ እንደሚያስቀርም አቶ አስፋህ ነግረውናል፡፡የህክምና ኦክስጅን ጋዙ ከሆስፒታሉ ህሙማን በተጨማሪ ለሌሎችም ሆስፒታሎች ለማቅረብ እንደታሰበና እስካሁንም ለቅዱስ ጳውሎስና ለጥቁር አንበሳ ሆስፒታሎች ሲያቀርብ መቆየቱን ከሆስፒታሉ ሰምተናል፡፡

ምህረት ሥዩም – sheger Radio

ትምህርት ሚኒስቴር ያዘጋጀውና ተማሪዎች ከተለያዩ ግለሰቦች መልካም ተሞክሮ ይቀስሙበታል የተባለ መርሃ ግብር እስከ ህዳር 26 ድረስ ይካሄዳል ተባለ

ትምህርት ሚኒስቴር ያዘጋጀውና ተማሪዎች ከተለያዩ ግለሰቦች መልካም ተሞክሮ ይቀስሙበታል የተባለ መርሃ ግብር እስከ ህዳር 26 ድረስ ይካሄዳል ተባለ። “የዓለም ታላቁ የትምህርት ቀን” የሚል መጠሪያ በተሰጠው መርሃ ግብር በተለያዩ መስኮች ውጤታማ የሆኑ ግለሰቦች ወደተማሩባቸው ትምህርት ቤቶች በመሄድ የህይወት ተሞክሯቸውን ለተማሪዎች ያካፍላሉ ተብሏል።ግለሰቦቹ መልካም ተሞክሯቸውን ከ5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች እንደሚያጋሩ ነው በትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ወይዘሮ ሐረጓ ማሞ የተናገሩት።

በየዓመቱ የሚከበረው “የዓለም ታላቁ የትምህርት ቀን” በ2030 ድህነትን ከዓለም የማጥፋት እና ጸረ አብሮነትና ኢ-ፍትሃዊነትን የመዋጋት ዓላማ ያነገበ መሆኑን ከኃላፊዋ ሰምተናል። በተጨማሪም ተማሪዎች የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እንዲሁም የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት እገዛ እንዲያደርጉ የሚያዘጋጅ ስራ የሚሰራበት ነው ተብሏል።ለአንድ ወር ያህል በሚቆየውና የፊታችን ሰኞ በሚጀምረው የዓለም ታላቁ የትምህርት ቀን አማካኝነት ከአንድ ሺ በላይ ትምህርት ቤቶች በቀድሞ ተማሪዎቻቸው እንደሚጎበኙ ሰምተናል።በተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊነቶች ላይ ያሉ ግለሰቦችም ወደተማሩባቸው ትምህርት ቤቶች እንደሚሄዱ ሰምተናል። ለተማሪዎች ስለተሞክሮዎቻቸው በክፍል ውስጥ ለ45 ደቂቃና በመሰብሰቢያ ቦታዎች ተገኝተው ገለፃ ያደርጋሉ ተብሏል።

አቅሙ ያላቸው ግለሰቦች ወደየትምህርት ቤታቸው ሲሄዱ የመማር ማስተማር ሂደቱን የሚያግዙ የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲያበረክቱም ተመክረዋል።“የዓለም ታላቁ የትምህርት ቀን” ሲከበር የሚከናወነው ተግባር ወደፊት አገር ተረካቢ የሆኑ ወጣት ተማሪዎችና መምህራንን ለማፍራት ያግዛል ተብሏል።

በየነ ወልዴ – sheger Radio

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞ ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ ሙሀመድ ኡመር ላይ ለሚያደርገው ምርመራ ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ ቀን ተፈቀደለት

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞ ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ ሙሀመድ ኡመር ላይ ለሚያደርገው ምርመራ ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ ቀን ተፈቀደለት፡፡ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ለዛሬ ቀጠሮ የያዘለትን የአቶ አብዲ ጉዳይ ተመልክቶ እና ከወንጀሉ ክብደትና ውስብስብነት አንፃር ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ መፍቀድ ትክክለኛ መሆኑን አምኖበታል፡፡ ፖሊስ ካለፈው ቀጠሮ ወዲህ 16 ገፅ የኦዲት ማስረጃ ማቅረቡን በንግድ ተቋማት ላይ የደረሰን ጉዳት የሚገልፅ 35 ገፅ ማስረጃም አቅርቤያለሁ ብሏል፡፡

Related stories   “ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በአንድነት በመከባበር፤ በመተሳሰብ እና በመረዳዳት ሊያከብር ይገባል”

ፖሊስ ተጨማሪ ጊዜ የፈለገው በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች 200 ግለሰቦች መገደላቸውን በተጠርጣሪዎቹ ምርመራ ማግኘቱን ፖሊስ አመልክቶ በጅምላ የተቀበረውን አስክሬን የመለየት ስራና ምስክር ለመቀበል ለወንጀሉ ተግባር የዋለ ገንዘብ እና መሳሪያ ለመያዝ እንዲቻለው መሆኑን አመልክቷል፡፡የተጠርጣሪ ጠበቆች 200 ሰዎች ተገደሉ የተባለው አዲስ ምርመራ ስለሆነ ብቻውን ተነጥሎ ሊታይ ይገባል ሲሉ አመልክተዋል፡፡ ተጠርጣሪዎች አደረሱት የተባለው ጉዳትም በዝርዝር ሊቀርብ ይገባል ብለዋል፡፡ በመጨረሻ ፍርድ ቤቱ የ14 ቀናት ተጨማሪ ፈቅዶ ለህዳር 13, 2011 ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

sheger Radio

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት አቶ አርዲን በድሪን የክልሉ ርዕሠ መስተዳድር አድርጎ ሾመ

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት አቶ አርዲን በድሪን የክልሉ ርዕሠ መስተዳድር አድርጎ ሾመ፡፡ ሹመቱ የተሰጠው ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ነው፡፡ ለ13 አመታት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድርነት ያገለገሉት አቶ ሙራድ አብዱልሃዲ በራሳቸው ጥያቄ ከስልጣን መልቀቃቸው ተሰምቷል፡፡

ምክር ቤቱ የአቶ አርዲን በድሪን ሹመት በ29 ድጋፍና በአምስት ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ አፅድቆታል፡፡ አቶ አርዲን በድሪ ከክልሉ የቀድሞ መስተዳድር አቶ ሙራድ አብዱላሂ ጋር የሀላፊነት ርክክብ ለማድረግ በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሐላ እንደፈፀሙ ተነግሯል፡፡ አቶ አርዲን የክልሉ የትምህር ቢሮ ምክትል ሀላፊ፣ የሐረር መምህራን ኮሌጅ ዲን ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም የሐረሪ ብሔራዊ ሊግ ለቀመንበር እና የክልሉ ባህል፣ ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ሆነው በማገልገል ላይ እንደነበሩ ሰምተናል፡፡ 

አስፋው ስለሺ – sheger Radio

ኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ፣ የአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዝደንት ከስራ መታገዳቸው ለተጀመረው የእርቅና የሰላም ጉዞ የማይበጅ መሆኑን ተናገረ

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ፣ የአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዝደንት ከስራ መታገዳቸው ለተጀመረው የእርቅና የሰላም ጉዞ የማይበጅ መሆኑን ተናገረ፡፡ ኮሚቴው ዛሬ አጠቃላይ የስራ አፈፃፀሙን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡መግለጫውም ልዩ ልዩ ንዑሳን ኮሚቴዎችን ማቋቋሙንና ሀላፊነት መስጠቱን ተናግሯል፡፡ ወቅታዊ ችግሮችንና ቀውሶችን ለመፍታት በቂ ጥረት አድርጌያለሁ ብሏል፡፡ ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ከሚገኙ የአለም ሙስሊም ማህበረሰቦች ጋር የልምድ ልውውጥ ማድረጉን ተናግሯል፡፡

ኮሚቴው በአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዝዳንት በሼህ መሀመድ ሸሪፍ ላይ የተደረገው የስራ እገዳ ከወቅቱ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ያልተዛመደና አንድን ግለሰብ ነጥሎ ተጠያቂ ያደረገ ነው፤ ስለሆነም ለጀመርነው የእርቅና የሰላም ጉዞ የማይበጅ መሆኑን ተገንዝበው የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትና የፌዴራል እስልምና ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ሂደቱን በጥሞና እንዲያስቡበት መክሯል፡፡ የጋራ ኮሚቴው የኢትዮጵያን ሙስሊሞችን ሁሉ ያለ ልዩነት የሚያሳትፍና የጋራ የሆነ መጅሊስን ለማዋቀር ውጥን መያዙን ተናግሯል፡፡ 

ቴዎድሮስ ብርሃኑ – sheger Radio

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0