“Our true nationality is mankind.”H.G.

በወቅታዊ የራያ ሁኔታ በሰሜን አሜሪካና ካናዳ አካባቢ በሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች የተሰጠ የአቋም መግለጫ!

እኛ በሰሜን አሜሪካና ካናዳ አካባቢ የምንኖር የራያ ተወላጆች ከሐምሌ ወር ጀምሮ በአላማጣ፤ዋጃ- ጥሙጋ እንዲሁም በአጠቃላይ በራያ ማህበረሰብ ላይ የትግራይ ልዩ ሀይል ባደረሰው ሞት፤ የአካል ጉዳት እንዲሁም መፈናቅል የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እንገልጻለን።የፈሰሰው የወገኖቻችን ደም የኛም ደም ነው፤ የነሱ ህመም የኛም ህመም ነው።ምንም እንኳ ማህበረሰቡ ጥያቄውን ያነሳው ሰላማዊ እና ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት ቢኖንም በወገኖቻችን ላይ በትግራይ ልዩ ሃይል የደረሰው በደል እጂግ አሰቃቂ በሆነ መልኩ   ነው። የልዩ ሀይል በወሰደው እርምጃ በዋጃ- ጥሙጋ ከአምስት በላይ ሰዎች እንደሞቱ ይታወቃል። ከሃያ በማያንሱ ሰዎች ላይ ደግሞ ከቀላል እስከ ከባድ የአካል ጉዳት  እንደደረሰ ይታወቃል። ሁለቱ የዪንቨርስቲ ተማሪዎች የነበሩ ሲሆን ወላጆቸው ብቻ ሳይሆን ማህበረሰቡ ዘንድ ትልቅ ተስፋ የነበራቸው ወጣቶች ነበሩ። በትሕነግ ልዩ ሐይል ተስፋቸው ጨልሟል። ወላጆች ያለጧሪ ቀርተዋል፤ ልጆች ያለአሳዳጊ ቀርተዋል። ብዙ ቤተሰብ ተበትኗል።

በተመሳሳይ መልኩ በጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ  ጀምሮ እስከአሁን ድረስ በአላማጣ ከተማና አካባቢዋ የራያ ማንነት ጥያቄ ባነሱ ወጣቶች ላይ ከባድ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ከዘጠኝ ሰዎች በላይ ተገላዋል። ከሰላሳ ሰዎች በላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሦባቸዋል። የእካባቢው ሽማግሌዎች፤ ታዋቂ ባለሃብቶች ፤ የመንግስት ሰራተኞች ፤ አስተማሪዎች ከአምስት መቶ በላይ ወጣቶች ታስረዋል። አንዳንዶቹ ወደየት እንደተወሰዱ እስክአሁን አይታወቅም። ብዙ ሰዎች እካባቢያቸውን ለቀው ተሰደዋል። በዋጃና ጥሙጋ የ ሁለተኛ ደረጃ እና የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ከተቋረጠ ወራትን አስቆጥሯል። በአካባቢው የሰላም ና የደህንነት ስጋት እሁንም እንደቀጠለ ይገኛል። የትግራይ ክልል መንግስት በጠቃላይ በራያ በተለይ ደግሞ በአላማጣ ላይ ልዩ ሐይል በማስገባት ከባቢው የደህነንት ስጋት ውስጥ እንዲጋባ አድርጎታል። የኢኮኖሚ እንቅስቃሤ በእጂጉ  ቀንሷል። የትግራይ ክልል መንግስት የማህበራሰቡን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አሁንም የተዘጋጀ አይደለም።  ችግሩ አሳሳቢ ደረጃ ከመድረሱ በፊት የሚመለከታቸው አካላት የማህበረሰቡን የማንነት ጥያቄ ሰላማዊ በሆነ መልኩ አንዲፈቱት እንጠየቃለን: ስለዚህ እኛ በሰሜን አሜሪካና ካናዳ የምንኖር የአካባቢው ተወላጆች ፤

 1. የራያ ማህበረሰብ የራሱ ባህል፤ ወግ፤ ታሪክ፤ ስነልቦና እና ቋንቋ ያለው ህዝብ ነው። ይህን አክብሮ ፤ተንከባክቦ ለመጭው ትውልድ ማሰተላለፍ ይፈልጋል። ነገር ግን አሁን ባለው የትግራይ ክልል መንግስት በተደጋጋሚ በማህበረስቡ በሚያደርሰው ጭቆና ይህን ለማድረግ እንደማይቻል፤ ይልቁንም የትሕነግ ልዩ ሃይል ማህበረስቡን በማስፈራራት እና በማፈን ጥያቄውን ህጋዊ በሆነ መልኩ እንዳያቀርብ የተለያየ ጫና እየፈጠረ ነው። ስለሆነም፣የትግራይ ክልል ልዩ ሀይል ከአካባቢው በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣና በምትኩ የፈደራል መንግስት የመከላከያ ሰራዊቱን በማሰማራት የማህበራሰቡን ደህንነት እንዲጠብቅ እንጠይቃለን።
 2. የራያ ህዝብ ያነሳቸው የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎች ሳይሆኑ የማንነት ጥያቄዎች ናቸው። ስለሆነም የማህበረሰቡን ጥያቄዎች ወደ መልካም  አስተዳደርና ወደልማት አውርዶ መመልከት ዘላቂ መፍትሔ ያመጣል የሚል እምነት የለንም። የማህበረሰቡ የማንንት ጥያቄ ህጋዊ በሆነ መልኩ ካልተመለሰ አካባቢዊን ወደአልተፈለገ ግጭት ይወስደዋል ብለን እናምናለን።   ስለዚህም በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ የሚትኖሩ የራያ ተወላጆች በሙሉ ዛሬ ከሌላው ግዜ በተለየ ከህዝባችሁ ጋር በመቆም የማንነት አስመላሽ ኮሚቴ በመደገፍ አብሮ በመስራት የተጀመረውን የማንነት ጥያቄዎቻችን ከግብ ለማድረስ ለምናደርገው ትግል እንድትቀላቀሉን ጥሪ እናስተላልፋለን፤
 3. የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው ብቻ የተገደሉ፤ የታሰሩ ሽማግሌዎች፤ ታዋቂ ባለሃብቶች፤ አስተማሪዎች፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በተላያዩ የትግራይ እስር ቤቶች እየተሰቃዩ እንዳለ ይታወቃል። አንዳንዶች ወደየት እንድተወሰዱ ቤተሰቦቻቸው ማወቅ አልቻሉም። ስለዚህ የትግራይ ክልል መንግስት እነዚህን ያለ አግባብ ያሰራቸውን የራያ አባቶች፤ አስተማሪዎች፤ ታዋቂ ባለህብቶች፤ ወጣቶችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ  እንጠይቃለን።
 4. በመሆኒ፤ጨርጨር ባላ እና አካባቢው ባሉ ወጣቶች ገናለገና ህዝቡን ይቀሰቅሳሉ፤ ያደራጃሉ ብለው ያሰቡትን ያዋክቧቸዋል፤ የስነልቦና ተጽኖ በትግራይ ልዩ ሃይል እየደረሰባቸው ነው። ይህ ህጋዊ ያለሆነ ድርጊተ በማህበረሰባችን ላይ ከፍተኛ ቀውስ እየፈጠረ ሰለሆነ ባስቸኳይ እንዲቆም;
 5. በማህበረሰባችን ላይ ከፍተኛ በደል በማድረስ የሰው ህይወት እንዲጠፋ ያደረጉ፤ ከፍተኛ የሆነ የአካል ጉዳት እንዲደርስ ትዕዛዝ የሰጡ የትግራይ ልዩ ሃይል መሪዎች ጉዳያቸው በገለልተኛ አካል ተጣርቶ በህግ እንድጠየቁ እንጠይቃለን።
 6. የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው ምክኒያት ብቻ ከቀያቸው የተፈናቀሉ የ አላማጣ ፤ የዋጃ ጥሙጋ ነዋሪዎች ወደቦታቸው በአስቸኳይ እንዲመለሱ፤ ነገር ግን የትግራይ ልዩ ሃይል የሰጋታቸው ምንጭ ሰለሆነ ይህ ሃይል ደግሞ በተደጋጋሚ በተለይ ወጣቶችን እያሰደደ እና የሰነልቦና ጫና እያሰደረ ሰለሆነ ይህ እንዳይሆን ዋስትና እንዲሰጣቸው፤
 7. የራያ ህዝብ የራሱን እድል በራሱ እንዲወስን ህገ መንግስቱ በሚፈቅደ መሰረት  እንዲፈቀድለት፤ ይህን ለማድረግ ደግሞ የማህበረሰቡን ንቃተ ህሊና ለመጨመርና ፤ ከህብረተሰቡ ጋር በመገናኘት ህዝቡን ለማደራጀት የራያን ማንነት ለማስመለስ የተቋቋመው ኮሚቴ ወደ እካባቢው ሂዶ ለመስራት የደህነንት ሰጋት ስላለበት ዋስትና ተሰጥቷቸው ህዝባቸውን እንዲያስተምሩ፤ እንዲያደራጁ።
 8. በማህበረሰባችን ላይ በተደጋጋሚ የሚደርሰው ወከባና እንግልት የቀጠለ ቢሆንም ማህበረሰባችን ግን እያሳየው ያለውን ታጋሽነትና አርቆ አስተዋይነት ይበል የሚያስብል ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ነው። ስለሆነም አሁንም ቢሆን ነገሮችን በንቃትና በአንክሮ በማጤን በትሕነግ እና ተላላኪውቹ የሚደርስብህን ትንኮሳዎች ሆነ እንግልት  በመታገስ የጀመርከውን የማንነት የትግል ጉዞ አጠናክረህ የማንነት ጥያቄዎህን ሰላማዊና ህጋዊ በሆነ መልኩ ፤በሰከነና ብልሃት በተሞላበት ማቅረብ፤
 9. የፈደሬሽን ምክር ቤት አጣሪ ኮሚቴ አቋቁሞ የራያን ማንነት ለማጠራት የሄደበት ግልፅነት የጎደለው ከመሆኑም በተጨማሪ አስታራቂ ሽማግሌዎች በታሰሩበት፤ ታዋቂ ግለሰቦች  እና ባለሃብቶች እስር ቤት እየተሰቃዩ ባለበት፤ ብዙ ወጣቶች ከአካባቢያቸው ተሰደው ባሉበት፤ የትግራይ ልዩ ሃይል ማህበረሰባችን በነጻነት እንዳይንቀሳቀስ ትልቅ እንቅፋት እየፈጠረ ባለበት፤ ማህበረሰቡ በትልቅ ፍራትና ስነ ልቦና ተጽኖ ውስጥ ሁኖ፤ የራያ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ በነጻ እንዳይንቀሳቀስ በታፈነበት ሁኔታ ሁኖ የማህበረሰቡ ጥያቄ ይመለሳል ብለን አናምነም። በዚህ ሁሉ ጫና ውስጥ ሁኖ ማህበረሰባችን የሚወስነው ውሳኔ ተቀባይነት አይኖረውም።
 10. የራያ ህዝብ በዘር ጨፍጫፊው ትሕነግ  ለህልፈት፤ እንግልት እና መፈናቀል በደረለባቸው የቀን ጨለማ ግዜ አለንላችሁ ብላችሁ በሁሉም የአማራ ክልል ከተሞች በነቂስ በመውጣት  አጋርነታችሁን ለገለፃችሁልን ፤ በስደት ላይ ለሚገኙት በገንዘብም በቁሳቁስም ለረዳችሁን የ አማራ ህዝብ ወገናችን  ከልብ የመነጨ  ምስጋናችንን እናቀርባለን። አሁንም የ ማንነት ትግሉ  ገና ጀመርነው እንጂ አልተቋጨም  እናም በገባችሁልን ቃል  መሰረት እስከመጨረሻው ከራያ ህዝብ ጎን እንድትቆሙ በድጋሜ እናሳስባለን፤
 11. ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ የራያዎች ጥያቄ የማንነት እንጂ ምንም አይነት የፖሊቲካ ይዘት እንደሌለው ከማንኛውም የፖሊቲካ ፓርቲ ወይንም ቡድን ጋር  ምንም አይነት ግንኙነት የለሌው መሆኑን ተረድቶ፤ በማንኛውም የሰላማዊ እና ህጋዊ የማንነት የማስከበር ሂደት ከራያ ህዝብ ጎን እንድትቆም እንጠይቃለን።
 12. እኛ በሰሜን አሜሪካና ካናዳ የምንኖር የራያ ተወላጆች የራያ ህዝብ የማንነት ጥያቄ ለዘመናት እየተንከባለለ የመጣ፤ ጥያቄውም እንዲመለስ ብዙ ሰዎች የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉበት፤ የታሰሩበት ከአገር የተባረሩበት ሁኔታ እንደነበርና ዛሬም በተለያየና በአስከፊ ሁኔታ እየቀጠለ እንደሆነ እንገነዘባለን። የራያ ህዝብ የማንነት ጥያቄ ተፈጥሮአዊ፤ ህገ መንግስታዊ  በመሆኑ ጥያቄአችሁ እስኪመለስ ድረስ እናንተ በምታደርጉት ህጋዊና ሰላማዊ እንቅስቃሴ እኛም ከጎናችሁ በመቆም የትግላሁ አጋር መሆናችንን አንገልጻለን።

በሰሜን እሜሪካ ና ካናዳ የሚኖሩ የ ራያ ተወላጆች

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ‹‹የህዳሴው ግድብ ለሱዳን ከፍተኛ ጥቅም አለው፤ የቀጠናውን የኢኮኖሚ ትስስር ያጠነክራል››
0Shares
0