በማያውቀው የፈጠራ ታሪክ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ሲካሄድበትና በተለይ ግንባር ተደርጎ በፈረጃ መከራ የደረሰበት የአማራ ሕዝብ በመንግስት ደረጃ በይፋ ይቅርታ ሊጠይቅ እንደሚገባ የደብረማርቆስና አካባቢው ነዋሪዎች ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ። በርካታ ጥያቄዎችን አንስተዋል። የሚከተለውን ያንብቡ

ጌታቸው ሽፈራው

የደብረ ማርቆስ እና የአካባቢው የአማራ ሕዝብ በዛሬው ሰልፍ የሚከተለውን ባለአምስት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ፍላጎት እና አቋሙን ማሳወቅ ይሻል፡፡

1)በአማራ ላይ የተሰነዘሩ አሉታዊ ትርክቶች በፖለቲካ ፕሮግራሞች፣ በትምህርት መፅሐፍት እና በሚዲያዎች እንዲታረም እንጠይቃለን፡፡

2) የአማራው ብሎም የኢትዮጵያ መኩሪያ ቅርሶቻችንን መንግሥት በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ አንጠይቃለን፡፡ ጣና እና ላሊበላ የፌዴራሉን መንግስት እጅ ይሻሉ፡፡ 
.
3) ያለፍላጎታቸው ባይተዋር ማንነት የተጫነባቸው መተከል፣ የወልቃይትና የራያ ህዝብ ነፃነት እንዲረጋገጥ አጥብቀን እንጠይቃለን!

4) በኢትዮጵያ ውስጥ አማራ የድርሻውን ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱ እንዲረጋገጥልን እየጠየቀን አማራ ከዚህ በኋላ ኢ ፍትሃዊነትን የሚሸከም ትክሻ እንደሌለው እናስገነዝባለን፡፡

5) በአፋር እና በሌሎች ኢትዮጵያዊያን የሚደርሰው ግፍ እና በደል በአስቸኳይ እንዲቆም እየጠየቅን፣መንግስት የመንግስትነት ድርሻውን እንዲወጣም እናሳስባለን፡፡

ሰላም ለመላው የአማራ ህዝብ
ሰላም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች!

እርግጥ ነው በተቋም ደረጃ፣ መንግስት ነኝ በሚለው ትህነግ/ኢህአዴግ ደረጃ አማራ ጨቋኝና ገዥ ነው ተብሏል። እርግጥ ነው አማራው ከሚከፍለው ግብር የውሎ አበል ተከፍሎ “አማራ ጨቋኝ ነው” እየተባለ ስልጠና ተሰጥቷል። አማራው በከፈለው ግብር “አማራ ገዥ ነው” ተብሎ ሰነድ ተዘጋጅቷል፣ መፅሐፍ ታትሟል።

መንግስት በይፋ አማራውን ይቅርታ መጠየቅ አለበት!

የአየሁ እርሻ ልማትና ብርሸለቆ ለአማራ ህዝብ ይመለሱ!!

አማራው በከፈለው ግብር “አማራ ገዥ ነው” ተብሎ ሰነድ ተዘጋጅቷል፣ መፅሐፍ ታትሟል

“አማራነት ደም እንጅ በላጲስ የሚጠፋ እርሳስ አይደለም”

“በፖለቲካ ውሳኔ የተወሰደ በኮሚቴ ውሳኔ አይመለስም። ወልቃይት፣ ራያ፣ መተከል የአማራ ርስቶች ናቸው።”

በኮሚቴ የሰጠነው ሕዝብና መሬት የለም። በኮሚቴ የምናስመልሰው ሕዝብና መሬትም የለም

አማራን ማፈናቀልና ማሳደድ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መቆም አለበት

የአየር ኃይልና አየር መንገድ ከዘረኝነት ይፅዱ

የአፋር ደም የእኛም ደም ነው

ደብረማርቆስ ለኮ/ል በዛብህ ጴጥሮስ ፍትሕን ጠይቃለች!

ወልቃይትና ራያ ትግራይ አልነበሩም። አይደሉምም

መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ እና ዘመነ ካሴ ታድመዋል!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *